መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ኮሚሽኑ ጠየቀ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የ2016 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን፣ ዛሬ ዐርብ፣ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ጠይቋል፡፡
በስካይ ላይት ሆቴል ለምክር ቤቱ አባላት በቀረበው የኮሚሽኑ ዓመታዊ ሪፖርት፣ በ2016 ዓ.ም. የገጠሙት ተግዳሮቶች እና ቀጣይ የሥራ ዕቅዶቹ ያካተተ ነው፡፡
ሪፖርቱን ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን አርኣያ፣ ኮሚሽኑ...