የሙቀት መጨመር በጅቡቲ ተመላላሽ አሽከርካሪዎች ላይ ሞት እና የጤና ጉዳት አደረሰ
ከባድ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባስከተለው ከፍተኛ ሙቀት የተነሣ፣ የጅቡቲ ተመላላሽ በኾኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ላይ የሞት እና የጤና እክል ማጋጠሙን፣ የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።
ማኅበሩ እና አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች፣ የተቀናጀ የወረፋ ሥርዓት አለመኖሩ፣ አሽከርካሪዎች፣ ከፍተኛ ሙቀት ባለበት ጅቡቲ ውስጥ ለረጅም ቀናት እንዲቆዩ እያደረጋቸው መኾኑ፣ ለአሽከርካሪዎቹ...