በተመድ የሚደገፍና በኬንያ ፖሊስ የሚመራ ኃይል ሄይቲ ገባ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፍና በኬንያ ፖሊስ የሚመራ ኃይል ሄይቲን በማበጥ ላይ ያሉትን ወሮበሎች ለመጋፈጥ ትላንት ማምሻውን መዲናዋ በሆነችው ፖርት ኦ ፕሪንስ ገብቷል።
ሁለት መቶ የሚሆኑ የኬንያ ፖሊስ ኃይል ዓባላት ትላንት ሄይቲ ቢገቡም፣ የመጀመሪያ ተግባራቸው ምን እንደሆነ አለመታወቁን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። ሰማኒያ በመቶ የሚሆንውን የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ ክፍል የሚቆጣጠሩትን ወሮበሎች እንደሚፋለሙ ይጠበቃል።
ወሮበሎቹ...