የኔዘርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር የኔቶ ዋና ፀሃፊ ሆነው ተመረጡ
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዓባል ሃገራት የኔዘርላንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ ቀጣዩ የቃል ኪዳኑ ዋና ጸሃፊ አድርገው መርጠዋል።
ድርጅቱ ምርጫውን ያደረገው በዩክሬን ያለው ጦርነት ተፋፍሞ በቀጠለበት እንዲሁም አሜሪካ ቃል ኪዳኑን በተመለከተ ወደፊት የሚኖራት አመለካከት በእርግጠኝነት ባልታወቀበት ሁኔታ ነው። ማርክ ሩተ በመጪው ጥቅምት ሥልጣኑን ይረከባሉ።
የወቅቱ የቃል ኪዳኑ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን የቀድሞው የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር...