AMHARIC.VOANEWS.COM
የካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያው “የመብት ጥሰትን ያስከትላል” ሲል ኢሰመኮ ተቸ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ትላንት ማክሰኞ የጸደቀው፣ የመሬት ይዞታ ካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያ፣ የመብት ጥሰትን ያስከትላል፤ ሲል ተችቷል፡፡ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹኔታ የሚወስነው የዐዋጁ ማሻሻያ፥ የካሳ ክፍያን፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ወደ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ማሸጋገርን ጨምሮ ከዳኝነት ጉዳዮች ጋራ የተገናኙ ለውጦችንም ደንግጓል፡፡...
0 Comments 0 Shares