በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያ ሳምንት በርካቶች በጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጡ
በአሜሪካ የበጋው የመጀመሪያው ሳምንት መጨረሻ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በመሣሪያ በተፈጸመ የጅምላ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በአላባማ ግዛት በተዘጋጀ ፌስታ፣ በኦሃዮ የመዝናኛ መንደር እንዲሁም በአርካንሶ አንድ የሸቀጥ መደብር በተከፈተ ተኩስ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል አልያም ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአሜሪካ በበጋው ወቅት የመሣሪያ ጥቃቶች በብዛት ይስተዋላሉ።
ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተከታታይ የደረሱት የጅምላ መሣሪያ...