ቻይና እና ፈረንሳይ በጋራ ሳተላይት አመጠቁ
የፈረንሳይ-ቻይና የጋራ ሳተላይት በህዋ ውስጥ ሊፈጠር የሚችል ከፍተኛ ፍንዳታን ለማጥናት ዛሬ ቅዳሜ ወደ ህዋ መጥቃለች። ይህ ጥረትም በአውሮፓ እና በእስያ ኃይሎች መካከል ሊደረግ የሚችል የኃይል ትብብር ጉልህ ተምሳሌት ተደርጎ ታይቷል።
በሁለቱ ሀገራት መሃንዲሶች የተሰራችው ሳተላይት በህዋ ውስጥ ያሉ የጋማ ጨረር አፍላቂዎችን ለመፈለግ ከመሬት በቢሊዮን የሚቆጠሩ የብርሃን ዓመታትን ርቃ እንደምትጓዝ ተገልጿል።
ሁለት የፈረንሳይ እና ሁለት የቻይና ሮኬቶችን...