የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሊሠሩ የሚችሉበትን ድንጋጌ የያዘ የዐዋጅ ረቂቅ ይፋ ኾነ
የውጭ ባንኮች፣ በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ የሚሳተፉበትን አግባብ የሚዘረዝር “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” ተዘጋጅቶ ይፋ ኾኗል።
የዐዋጅ ረቂቁ፣ የውጭ ባንኮች፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚይዙትን ተቀጥላ ወይም ቅርንጫፍ ለመክፈት ፈቃድ እንደሚያገኙ ይደነግጋል።
ይኸው ረቂቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዛሬ ኀሙስ ስብሰባው ላይ ውይይት ከሚያደርግባቸው የዐዋጆች ረቂቆች መካከል አንዱ እንደኾነ ተጠቅሶ የነበረ ቢኾንም ውይይት አልተደረገበትም።...