በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ጠየቁ
በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች፣ ከአገልግሎት አቅርቦት እና ከጸጥታ ጋራ የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጥሪ አቀረቡ።
በሰሜን ጎንደር ዞን በዓለምዋጭ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ በአካባቢያቸው፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውጥ ተደርጎ፣ አንድ ስደተኛ በበራሪ ጥይት መቁሰሉን ገልጸው፣ በኹኔታው ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል፡፡
በምዕራብ ጎንደር ዞን ያሉት...