የእስላማዊ ቡድን ማንሰራራት ያሰጋት ሶማሊያ ለቀው የሚወጡት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ፍጥነት እንዲቀንሱ ጠየቀች
በሀገሯ የጸጥታ ክፍተት ሊፈጠር ይችላል ስትል ያስጠነቀቀችው ሶማሊያ፣ የአፍሪካ ሰላም አሰከባሪ ኃይሎች ከሶማሊያ ለቀው የሚወጡበትን ፍጥነት እንዲቀንሱ ጠይቃለች። ሮይተርስ የተመለከታቸው ሰነዶች እንደሚያሳዩት፣ ከሶማሊያ ጋር ድንበር የሚዋሰኑ አጎራባች ሀገሮች፣ ዳግም እያንሰራራ የሚገኘው የአል-ሻባብ ቡድን ስልጣን ሊቆጣጠር ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።
በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ሰላም አስከባሪ ኃይል እ.አ.አ በታህሳስ...