በኒው ሜክሲኮ የተነሳው ሰደድ እሳት 7 ሺህ ሰዎችን አፈናቀለ
በደቡባዊ ኒው ሜክሲኮ ግዛት በሚገኘው 'ሩዶሶ' ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ በሚገኘው ፈጣን ሰደድ እሳት ምክንያት ነዋሪዎች ምንም አይነት ንብረታቸውን ማንሳት ሳይችሉ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።
7 ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት መንደር ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው እንዲወጡ የተነገራቸው ሰኞ እለት ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ነው።
የኒው ሜክሲክኮ ግዛት የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በእሳቱ ምክንያት የመንደሩን የተወሰነ ክፍል የኤሌክትሪክ አገልግሎት...