የአሜሪካ ዜግነት ካላቸው ጋራ ትዳር የፈጸሙ ዜግነት ሊያገኙ ይችላሉ
የአሜሪካ ዜግነት የሌላቸው ነገር ግን ወደ አሜሪካ ከመጡ በኋላ ዜጋ ከሆኑት ጋራ በትዳር የተጣመዱ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ብሎም ዜግነት እንዲያገኙ የሚፈቅድ ደንብ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ዛሬ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ዋይት ሃውስ እንዳስታወቀው፣ የአሜሪካ ዜጎችን ያገቡ ነገር ግን ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሃገሪቱ የሚኖሩ ሰዎች ለመኖሪያ ፈቃድ ወይም ግሪን ካርድ ማመልከት ይችላሉ። ቀጥሎም ለዜግነት ማመልከት እንደሚችሉ...