ሴኔጋል ከ50 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ኮኬይን ያዘች
የሴኔጋል ጉምሩክ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ በድምሩ ከ50 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ሦስት የኮኬይን ጭነቶች መያዙን ትላንት ማክሰኞ ዕለት አስታወቀ።
የጉምሩክ ባለስልጣናት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአጎራባች ሀገሮች፣ በተለይም በላቲን አሜሪካ እየተመረተ ወደ አውሮፓ የሚጓዘውን አደንዛዥ ዕፅ ማስተላለፊያ ከሆኑት ጊኒ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ-ቢሳው እና ማሊ የሚገባውን ኮኬይን በብዛት እየያዙ ይገኛሉ።
ፖሊስ ትላንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ከማሊ ጋር በሚያዋስነው...