“የአሻንቲ ህዝብ ለቡድኑ ጠንካራ ፀሎት አድርጓል ከአላህ ጋር ኢትዮጵያን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እናሸንፋለን” – ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን
የጋናዋ አሻንቲ ግዛት የእስልምና መሪ የሆኑት ሼህ ሀሩን አብዱል ሙሚን የአካባቢው የእስልምና ተከታዮች ለብሔራዊ ብድኑ ፀሎት እንዳደረጉና በፈጣሪ እርዳታ ሀገራቸው ጨዋታውን ከአምስት ጎል ባላነሰ ውጤት እንደምታሸንፍ ተናግረዋል። ሼሁ ከፀሎት በኋላ በኩማሲ መስኪድ ለተገኙት የቡድኑ ተጫዋቾች ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ለብሔራዊ ቡድኑ ተገቢው ፀሎት መደረጉንና ከፈጣሪ ጋር ሀገራቸው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተሳትፎዋን በድል እንደምትጀምር ያላቸውን በራስ መተማመን አጉልተው አሳይተዋል። በዚህ በኩማሲ መስኪድ በተደረገው የፀሎት ስነስርአት ላይ ሁለቱ ወንድማማቾች አንድሬ እና ጆርዳን አዩ፣ ረሺድ ሱማይላና አብዱል መጂድ ዋሪስ አይነት የቡድኑ ኮከቦች ተካፋይ ነበሩ። ከቡድኑ ተጫዋቾች በተጨማሪ የቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ኢብራሂም አንያራስ ታንኮ እና የህዝብ ግንኙነቱ ኢብራሂም ሳኔ ዳራ በፀሎቱ ተካፍለዋል። ከዛሬ ምሽቱ ትንቅንቅ በፊት ብዙዎች የማሸነፉን ግምት ለጥቋቁሮቹ ኮከቦች የሰጡ ቢሆንም ዋልያዎቹ በተሰጣቸው ያነሰ ግምት እንደማይደናገጡና በጨዋታው ላይ ውጤት ለማግኘት የተቻላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛል። የቡድኑ አሰልጣኝ አሸናፊ ከበደ ከአንድ የጋና ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ “እናውቃለን ጋና ጠንካራ ቡድን ነው። ነገርግን እኛ እነሱን ስንገጥም የምናስደምምበት የራሳችን እቅድ አለን።” ሲሉ ተጋጣሚያቸው ጠንካራ ቢሆንም ለጨዋታው ዝግጁ እንደሆኑ አውስተዋል። ጋና ከ 1963 የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ ዋሊያዎቹን ለሶስት ጊዜያት የገጠመች ሲሆን በሁለቱ ስታሸንፍ በአንዱ ሽንፈት ቀምሳለች። የሁለቱ ቡድኖች የመጨረሻ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት በ 2014 ጋና 1-0 ያሸነፈችበት የቻን ውድድር መሆኑ ይታወሳል።

0 Comments
0 Shares