የቀድሞው የኤሲ ሚላን ፣ ሮማ ፣ ጁቬንቱስና ሪያልማድሪድ አሰልጣኝ ውጤታማው ፋቢዮ ካፔሎ ወደክለብ ማሰልጠን ስራቸው በመመለስ የቻይናው ክለብ ጂያንሱ ሰኒንግ አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡ በ2007 ሪያል ማድሪድን ከለቀቁ በኋላ ከክለብ አሰልጣኝነት ርቀው የቆዩት ካፔሎ በበሔራዊ ቡድን ደረጃ የእንግሊዝና የሩሲያን ብሔራዊ ቡድን ሲያሰለጥኑ ቆይተዋል፡፡ በ 2015 ከሩሲያ ኃላፊነታቸው የለቀቁት አሰልጣኙ እስከአሁን ስራ ፈትተው የሰነበቱ ቢሆንም አሁን ግን በረብጣ ሚልዮን ዶላሮች የበለፀገው የቻይና ሱፐር ሊግ ማረፊያቸው ሆኗል፡፡ የጣልያናዊውን ግልጋሎት ለማግኘት የተስማማው ሰኒንግ በ2016 የውድድር ዘመን በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ መጨረስ ችሎ የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የውድድር ዘመን ግን በወራጅ ቀጠናው ውስጥ እየዳከረ ይገኛል፡፡ የስምምነት ስርአቱን ተከትሎ የክለቡ ይፋዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን”አሰልጣኝ ካፔሎን ለማስፈረም የተደረሰው ውሳኔ የክለቡ የለውጥና የዕድገት ፍላጎት እንቅስቃሴ አካል ነው” የሚል ቃል ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪም”ክለቡን ከመምራት በተጓዳኝ በክለብ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዘመናዊ አሰራርና የተሻሉ ሃሳቦችን ማስረጽ ሌላኛው ኃላፊነቱ ነው ፤ በዚህም የኛ ክለብ ላይ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላው የቻይና እግር ኳስ ላይ ለውጥ መፍጠር እንችላለን” ይላል፡፡ ጣልያናዊው ቆፍጣና በልዕልና ዘመናቸው አምስት የሴሪ አ ፣ ሁለት የላሊጋና አንድ የሻምፒዮንስ ሊግ ክብርን በማግኘት ደማቅ ታሪክን ፅፈዋል

0 Comments
0 Shares