ኢማኑኤል አዴባዮር በህይወቱ ፀፀት የሆነበትን ውሳኔ ይፋ አደረገ

ሪያል ማድሪድን ጨምሮ በአርሰናል ፣ በማንችስተር ሲቲና ቶተንሐም ቆይታ ማድረግ የቻለው ቶጎአዊ የፊት አጥቂ ኢማኑኤል አዴባዮር በእግር ኳስ ህይወቱ ከሚያስፀፅቱት ውሳኔዎች ዋነኛው በ2016 ለክሪስታል ፓላስ ለመጫወት መስማማቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ . ተጫዋቹ በወቅቱ ክለብ አልባ የነበረ በመሆኑ የቀረበለትን የፈርምልን ጥያቄ ሳያቅማማ የተቀበለ ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ 15 ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ካስቆጠረ በኋላ ወደተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ውሉን ለመጨረስ ተገዷል፡፡. ተጫዋቹ ለ ለኪፕ እንደተናገረው “በእንግሊዝ ከታላላቅ ክለቦች ጋር መልካም ጊዜያትን አሳልፌአለሁ ፤ እኔና ቤተሰቤ ደስተኛ ነበርን፡፡ የሰራሁት ብቸኛ ስህተት ለፓላስ ለመጫወት መስማማቴ ነው፡፡ ይህን ያደረኩት ለኔ ሰዎች ስል ነው፡፡ ሁሌም ‘ወደሜዳ ተመለስ እንጂ!’ ይሉኝ ነበር፡፡ የጨዋታ ዘመኔ መጥፎ ውሳኔ ነበር”ብሏል፡፡ ተጫዋቹ ወደቱርክ በማቅናት ለባሳክሺር ከፈረመ በኋላ ወደቀድሞ ብቃቱ የተመለሰ ሲሆን ክለቡን ለቱርክ ዋንጫ ፍፃሜ ማድረስ ችሏል፡፡ አዴባዮር ጨምሮም የቱርክ ቆይታው እንደተመቸውና ወደሌላ ክለብ የመዘዋወር ዕቅድ እንደሌለው አሳውቋል፡፡
ኢማኑኤል አዴባዮር በህይወቱ ፀፀት የሆነበትን ውሳኔ ይፋ አደረገ ሪያል ማድሪድን ጨምሮ በአርሰናል ፣ በማንችስተር ሲቲና ቶተንሐም ቆይታ ማድረግ የቻለው ቶጎአዊ የፊት አጥቂ ኢማኑኤል አዴባዮር በእግር ኳስ ህይወቱ ከሚያስፀፅቱት ውሳኔዎች ዋነኛው በ2016 ለክሪስታል ፓላስ ለመጫወት መስማማቱ መሆኑን ገልጿል፡፡ . ተጫዋቹ በወቅቱ ክለብ አልባ የነበረ በመሆኑ የቀረበለትን የፈርምልን ጥያቄ ሳያቅማማ የተቀበለ ቢሆንም በመጀመሪያዎቹ 15 ጨዋታዎች አንድ ጎል ብቻ ካስቆጠረ በኋላ ወደተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ውሉን ለመጨረስ ተገዷል፡፡. ተጫዋቹ ለ ለኪፕ እንደተናገረው “በእንግሊዝ ከታላላቅ ክለቦች ጋር መልካም ጊዜያትን አሳልፌአለሁ ፤ እኔና ቤተሰቤ ደስተኛ ነበርን፡፡ የሰራሁት ብቸኛ ስህተት ለፓላስ ለመጫወት መስማማቴ ነው፡፡ ይህን ያደረኩት ለኔ ሰዎች ስል ነው፡፡ ሁሌም ‘ወደሜዳ ተመለስ እንጂ!’ ይሉኝ ነበር፡፡ የጨዋታ ዘመኔ መጥፎ ውሳኔ ነበር”ብሏል፡፡ ተጫዋቹ ወደቱርክ በማቅናት ለባሳክሺር ከፈረመ በኋላ ወደቀድሞ ብቃቱ የተመለሰ ሲሆን ክለቡን ለቱርክ ዋንጫ ፍፃሜ ማድረስ ችሏል፡፡ አዴባዮር ጨምሮም የቱርክ ቆይታው እንደተመቸውና ወደሌላ ክለብ የመዘዋወር ዕቅድ እንደሌለው አሳውቋል፡፡
0 Comments 0 Shares