‹እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ፤ ልንፈጥረው ግድ ይለን ነበር፡፡›› (ቮልቴር)
(እ.ብ.ይ.)

ወዳጆች ሩሲያዊው ደራሲ ዶስቶቭስኪ ‹‹እግዚአብሔር ከሌለ ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፡፡›› ይለናል፡፡ ዶስቶቭስኪ ይሄንን ያለው የእግዚአብሔርን በሠው ሕይወት ላይ ያለውን አስፈላጊነት ሲያሠምርበት ነው፡፡

አባትና እናቱን ያጣ ልጅ ምን ያህል የስብዕና ችግር ተጋላጭ እንደሆነ የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሠው ደግሞ ራሱን የሚገነባበት የሞራል ማገር ስነ-ምግባር የለሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖት ስነምግባር ያለውን ህብረተሠብ የሚያመርት ተቋም ነውና፡፡ እዚህ ላይ እግዚአብሔርን እያመነ ምግባረ ብልሹ የሆነ ሠው የለም እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ ኢ-አማኝም ሆኖ መልካም ስብዕናን የገነባ ጠንካራ ሠው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከአዕምሮው በላይ ያስቀመጠው አንድ ፈራጅ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ አምላክ ያለው ሠው ግን በሕይወቱ ለሚያደርጋት ለእያንዳንዷ ድርጊቱ ተጠያቂ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ሕይወቱን አምላክ በሠጠው ነፃ ፍቃድ እየተመራ በትክክለኛው ምርጫው በህይወት መንገድ ለመመላለስ ይጥራል፡፡ ከመንገዱ ቢያፈነግጥም እንኳን በህሊናው ጅራፍ ይገረፋል፡፡

የሠው ልጅ አክብሮ የሚፈራው ፈጣሪ ካለው በዓለም ሕይወቱ ላይ ዘላን እና ልቅ እንዳይሆን እምነቱ ይጠብቀዋል፡፡ አካሄዱን ያስተካክለዋል፡፡ በደመነፍስ ስሜቱ እንዳይነዳ ሃይማኖቱ ልጓም ሆኖ ያገለግለዋል፡፡ አስቡት እስቲ የዓለም ህብረተሠብን የሚያስተዳድረው ህግ ባይኖር ኖሮ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ምን ያህል ትርምሶችና እልቂት ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ሕጉ እንኳን እያለ ህገወጡ በዝቶ ምን ያህል የእርስበርስ ጦርነት ዓለማችን እያስተናገደች እንዳለች የዓለማችንን የታሪክ ዶሴ ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ የሠው ልጅን የስሜት ግልቢያ መግራት የሚቻለው በህግ ነውና፡፡ ያ ህግ ደግሞ ዓለማዊ ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሠማያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እስራኤላውያን ነብዩ ሳሙኤልን ንጉስ አንግስብን እያሉ ሲማፀኑት የነበረው አንድ የሚፈሩት ንጉስ በመፈለግ ነው፡፡ ስለዚህም ነብዩ ሳሙኤል ሳዖልን አንግሶባቸዋል፡፡ ሳዖልም የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉስ ሆኖ በመፅሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፡፡

ቮልቴር እግዚዘብሄር ባይኖር ኖሮ እንደእግዚአብሔር ያለ የምንፈራውና የምናከብረው አካል ልንፈጥር ሕይወት ግድ ይለናል ይላል፡፡ ምክንያቱም የሠው ልጅን በዚህ ዓይነት መንገድ ስሜቱን መግራት ካልቻልን ዓለም የሠው አውሬዎች መፈንጪያ ትሆን ነበር ሲለን ነው፡፡

እናንተስ እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል??? ሃሳብና አስተያየታችሁን በነፃነት ታስቀምጡ ዘንድ መድረኩ ክፍት ነው፡፡

ቸር ጊዜ!

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!

_________________________
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ረቡዕ ታህሳስ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
‹እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ፤ ልንፈጥረው ግድ ይለን ነበር፡፡›› (ቮልቴር) (እ.ብ.ይ.) ወዳጆች ሩሲያዊው ደራሲ ዶስቶቭስኪ ‹‹እግዚአብሔር ከሌለ ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፡፡›› ይለናል፡፡ ዶስቶቭስኪ ይሄንን ያለው የእግዚአብሔርን በሠው ሕይወት ላይ ያለውን አስፈላጊነት ሲያሠምርበት ነው፡፡ አባትና እናቱን ያጣ ልጅ ምን ያህል የስብዕና ችግር ተጋላጭ እንደሆነ የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሠው ደግሞ ራሱን የሚገነባበት የሞራል ማገር ስነ-ምግባር የለሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖት ስነምግባር ያለውን ህብረተሠብ የሚያመርት ተቋም ነውና፡፡ እዚህ ላይ እግዚአብሔርን እያመነ ምግባረ ብልሹ የሆነ ሠው የለም እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ ኢ-አማኝም ሆኖ መልካም ስብዕናን የገነባ ጠንካራ ሠው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከአዕምሮው በላይ ያስቀመጠው አንድ ፈራጅ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ አምላክ ያለው ሠው ግን በሕይወቱ ለሚያደርጋት ለእያንዳንዷ ድርጊቱ ተጠያቂ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ሕይወቱን አምላክ በሠጠው ነፃ ፍቃድ እየተመራ በትክክለኛው ምርጫው በህይወት መንገድ ለመመላለስ ይጥራል፡፡ ከመንገዱ ቢያፈነግጥም እንኳን በህሊናው ጅራፍ ይገረፋል፡፡ የሠው ልጅ አክብሮ የሚፈራው ፈጣሪ ካለው በዓለም ሕይወቱ ላይ ዘላን እና ልቅ እንዳይሆን እምነቱ ይጠብቀዋል፡፡ አካሄዱን ያስተካክለዋል፡፡ በደመነፍስ ስሜቱ እንዳይነዳ ሃይማኖቱ ልጓም ሆኖ ያገለግለዋል፡፡ አስቡት እስቲ የዓለም ህብረተሠብን የሚያስተዳድረው ህግ ባይኖር ኖሮ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ምን ያህል ትርምሶችና እልቂት ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ሕጉ እንኳን እያለ ህገወጡ በዝቶ ምን ያህል የእርስበርስ ጦርነት ዓለማችን እያስተናገደች እንዳለች የዓለማችንን የታሪክ ዶሴ ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ የሠው ልጅን የስሜት ግልቢያ መግራት የሚቻለው በህግ ነውና፡፡ ያ ህግ ደግሞ ዓለማዊ ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሠማያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እስራኤላውያን ነብዩ ሳሙኤልን ንጉስ አንግስብን እያሉ ሲማፀኑት የነበረው አንድ የሚፈሩት ንጉስ በመፈለግ ነው፡፡ ስለዚህም ነብዩ ሳሙኤል ሳዖልን አንግሶባቸዋል፡፡ ሳዖልም የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉስ ሆኖ በመፅሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፡፡ ቮልቴር እግዚዘብሄር ባይኖር ኖሮ እንደእግዚአብሔር ያለ የምንፈራውና የምናከብረው አካል ልንፈጥር ሕይወት ግድ ይለናል ይላል፡፡ ምክንያቱም የሠው ልጅን በዚህ ዓይነት መንገድ ስሜቱን መግራት ካልቻልን ዓለም የሠው አውሬዎች መፈንጪያ ትሆን ነበር ሲለን ነው፡፡ እናንተስ እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል??? ሃሳብና አስተያየታችሁን በነፃነት ታስቀምጡ ዘንድ መድረኩ ክፍት ነው፡፡ ቸር ጊዜ! ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ! _________________________ እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.) ረቡዕ ታህሳስ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
Like
1
0 Comments 0 Shares