ግጥም ግጥም ግጥም ግጥም ብቻ
Recent Updates
-
‹እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ፤ ልንፈጥረው ግድ ይለን ነበር፡፡›› (ቮልቴር)
(እ.ብ.ይ.)
ወዳጆች ሩሲያዊው ደራሲ ዶስቶቭስኪ ‹‹እግዚአብሔር ከሌለ ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፡፡›› ይለናል፡፡ ዶስቶቭስኪ ይሄንን ያለው የእግዚአብሔርን በሠው ሕይወት ላይ ያለውን አስፈላጊነት ሲያሠምርበት ነው፡፡
አባትና እናቱን ያጣ ልጅ ምን ያህል የስብዕና ችግር ተጋላጭ እንደሆነ የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሠው ደግሞ ራሱን የሚገነባበት የሞራል ማገር ስነ-ምግባር የለሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖት ስነምግባር ያለውን ህብረተሠብ የሚያመርት ተቋም ነውና፡፡ እዚህ ላይ እግዚአብሔርን እያመነ ምግባረ ብልሹ የሆነ ሠው የለም እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ ኢ-አማኝም ሆኖ መልካም ስብዕናን የገነባ ጠንካራ ሠው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከአዕምሮው በላይ ያስቀመጠው አንድ ፈራጅ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ አምላክ ያለው ሠው ግን በሕይወቱ ለሚያደርጋት ለእያንዳንዷ ድርጊቱ ተጠያቂ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ሕይወቱን አምላክ በሠጠው ነፃ ፍቃድ እየተመራ በትክክለኛው ምርጫው በህይወት መንገድ ለመመላለስ ይጥራል፡፡ ከመንገዱ ቢያፈነግጥም እንኳን በህሊናው ጅራፍ ይገረፋል፡፡
የሠው ልጅ አክብሮ የሚፈራው ፈጣሪ ካለው በዓለም ሕይወቱ ላይ ዘላን እና ልቅ እንዳይሆን እምነቱ ይጠብቀዋል፡፡ አካሄዱን ያስተካክለዋል፡፡ በደመነፍስ ስሜቱ እንዳይነዳ ሃይማኖቱ ልጓም ሆኖ ያገለግለዋል፡፡ አስቡት እስቲ የዓለም ህብረተሠብን የሚያስተዳድረው ህግ ባይኖር ኖሮ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ምን ያህል ትርምሶችና እልቂት ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ሕጉ እንኳን እያለ ህገወጡ በዝቶ ምን ያህል የእርስበርስ ጦርነት ዓለማችን እያስተናገደች እንዳለች የዓለማችንን የታሪክ ዶሴ ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ የሠው ልጅን የስሜት ግልቢያ መግራት የሚቻለው በህግ ነውና፡፡ ያ ህግ ደግሞ ዓለማዊ ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሠማያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እስራኤላውያን ነብዩ ሳሙኤልን ንጉስ አንግስብን እያሉ ሲማፀኑት የነበረው አንድ የሚፈሩት ንጉስ በመፈለግ ነው፡፡ ስለዚህም ነብዩ ሳሙኤል ሳዖልን አንግሶባቸዋል፡፡ ሳዖልም የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉስ ሆኖ በመፅሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፡፡
ቮልቴር እግዚዘብሄር ባይኖር ኖሮ እንደእግዚአብሔር ያለ የምንፈራውና የምናከብረው አካል ልንፈጥር ሕይወት ግድ ይለናል ይላል፡፡ ምክንያቱም የሠው ልጅን በዚህ ዓይነት መንገድ ስሜቱን መግራት ካልቻልን ዓለም የሠው አውሬዎች መፈንጪያ ትሆን ነበር ሲለን ነው፡፡
እናንተስ እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል??? ሃሳብና አስተያየታችሁን በነፃነት ታስቀምጡ ዘንድ መድረኩ ክፍት ነው፡፡
ቸር ጊዜ!
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!
_________________________
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ረቡዕ ታህሳስ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም‹እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ፤ ልንፈጥረው ግድ ይለን ነበር፡፡›› (ቮልቴር) (እ.ብ.ይ.) ወዳጆች ሩሲያዊው ደራሲ ዶስቶቭስኪ ‹‹እግዚአብሔር ከሌለ ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፡፡›› ይለናል፡፡ ዶስቶቭስኪ ይሄንን ያለው የእግዚአብሔርን በሠው ሕይወት ላይ ያለውን አስፈላጊነት ሲያሠምርበት ነው፡፡ አባትና እናቱን ያጣ ልጅ ምን ያህል የስብዕና ችግር ተጋላጭ እንደሆነ የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሔር የሌለው ሠው ደግሞ ራሱን የሚገነባበት የሞራል ማገር ስነ-ምግባር የለሽ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ሃይማኖት ስነምግባር ያለውን ህብረተሠብ የሚያመርት ተቋም ነውና፡፡ እዚህ ላይ እግዚአብሔርን እያመነ ምግባረ ብልሹ የሆነ ሠው የለም እያልኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፡፡ ኢ-አማኝም ሆኖ መልካም ስብዕናን የገነባ ጠንካራ ሠው ይኖራል፡፡ ነገር ግን ከአዕምሮው በላይ ያስቀመጠው አንድ ፈራጅ ልዕለ-ተፈጥሮ የሆነ አምላክ ያለው ሠው ግን በሕይወቱ ለሚያደርጋት ለእያንዳንዷ ድርጊቱ ተጠያቂ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ሕይወቱን አምላክ በሠጠው ነፃ ፍቃድ እየተመራ በትክክለኛው ምርጫው በህይወት መንገድ ለመመላለስ ይጥራል፡፡ ከመንገዱ ቢያፈነግጥም እንኳን በህሊናው ጅራፍ ይገረፋል፡፡ የሠው ልጅ አክብሮ የሚፈራው ፈጣሪ ካለው በዓለም ሕይወቱ ላይ ዘላን እና ልቅ እንዳይሆን እምነቱ ይጠብቀዋል፡፡ አካሄዱን ያስተካክለዋል፡፡ በደመነፍስ ስሜቱ እንዳይነዳ ሃይማኖቱ ልጓም ሆኖ ያገለግለዋል፡፡ አስቡት እስቲ የዓለም ህብረተሠብን የሚያስተዳድረው ህግ ባይኖር ኖሮ አሁን ካለው በባሰ ሁኔታ ምን ያህል ትርምሶችና እልቂት ሊፈጠር እንደሚችል ለመገመት ቀላል ነው፡፡ ሕጉ እንኳን እያለ ህገወጡ በዝቶ ምን ያህል የእርስበርስ ጦርነት ዓለማችን እያስተናገደች እንዳለች የዓለማችንን የታሪክ ዶሴ ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ የሠው ልጅን የስሜት ግልቢያ መግራት የሚቻለው በህግ ነውና፡፡ ያ ህግ ደግሞ ዓለማዊ ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሠማያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እስራኤላውያን ነብዩ ሳሙኤልን ንጉስ አንግስብን እያሉ ሲማፀኑት የነበረው አንድ የሚፈሩት ንጉስ በመፈለግ ነው፡፡ ስለዚህም ነብዩ ሳሙኤል ሳዖልን አንግሶባቸዋል፡፡ ሳዖልም የእስራኤል የመጀመሪያው ንጉስ ሆኖ በመፅሐፍ ቅዱስ ተመዝግቧል፡፡ ቮልቴር እግዚዘብሄር ባይኖር ኖሮ እንደእግዚአብሔር ያለ የምንፈራውና የምናከብረው አካል ልንፈጥር ሕይወት ግድ ይለናል ይላል፡፡ ምክንያቱም የሠው ልጅን በዚህ ዓይነት መንገድ ስሜቱን መግራት ካልቻልን ዓለም የሠው አውሬዎች መፈንጪያ ትሆን ነበር ሲለን ነው፡፡ እናንተስ እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል??? ሃሳብና አስተያየታችሁን በነፃነት ታስቀምጡ ዘንድ መድረኩ ክፍት ነው፡፡ ቸር ጊዜ! ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ! _________________________ እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.) ረቡዕ ታህሳስ ፳፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ምPlease log in to like, share and comment! -
ወንድ ብቻውን ነው የሚያለቅስ
===============
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ፥
ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡.....
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡......
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደደመና ተቋጥሮ
ውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ......
መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር......
የኋላ የኋላ፥ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ፥ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡
ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው......
የእንባ ጭለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበው፡፡
ዕጣውን ለብቻው ቆርሶ
ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ
ብቻውን ጭለማ ለብሶ
ገበናውን ሣግ ሸፍኖ
ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ
ሌሊት፥ የማታ ማታ ነው
ሕቅ እንቁን እሚነጥበው
ኤሎሄውን እሚረግፈው.....
ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ
ደም አልሞ ፍም አምጦ
ከአፅመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ
ከአንጀቱ ሲቃ ቆርጦ
እንደጠፍር-ብራቅ እምብርት
እንደእሳተ ገሞራ ግት
‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው
ደም ነው፥ ፍም ነው እሚያነባው፤
ንጥረ ሕዋስ ነው ሰቆቃው
ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፥__ብቻውን ነው የሚፈታው፥
ብቻውን ነው የሚረታው፡፡
ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥
ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ፥
እንደደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ፥.....
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤተ-ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፥
ተሸሽጎ ተከናንቦ፥
ተሸማቆ ተሸምቆ......
የብቻ ብቸኝነቱ፥
የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ-ሌት፥ ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ፡፡
( ጸጋዬ ገብረ መድኅን )
ወንድ ብቻውን ነው የሚያለቅስ =============== ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ ተሸሽጎ ተገልሎ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ ከቤተ-ሰው ተደብቆ መሽቶ፥ የማታ ማታ ነው፥ ሌት ነው የወንድ ልጅ እንባው ብቻውን ነው የሚፈታው፡፡..... ብቻውን ነው የሚረታው፡፡...... ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ተማምጦ ተጣጥሮ በሲቃ ግት ተወጥሮ እንደደመና ተቋጥሮ ውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ...... መሽቶ፥ ረፍዶ፥ ጀምበር ጠልቆ የጨለማ ድባብ ወድቆ በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ፥ በዝምታ ሲዋጥ አገር ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር...... የኋላ የኋላ፥ማታ ምድር አገሩ በእፎይታ ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ፥ ብቸኝነት ብቻ ሲቀርብ ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ የብቻ፥ እንባ ወዙ እሚነጥብ፡፡ ብቻውን ነው፥ ብቻውን ነው...... የእንባ ጭለማ ለብሶ ነው ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥበው፡፡ ዕጣውን ለብቻው ቆርሶ ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ ብቻውን ጭለማ ለብሶ ገበናውን ሣግ ሸፍኖ ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ ሌሊት፥ የማታ ማታ ነው ሕቅ እንቁን እሚነጥበው ኤሎሄውን እሚረግፈው..... ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ ደም አልሞ ፍም አምጦ ከአፅመ-ወዙ እቶን ተፈልጦ ከአንጀቱ ሲቃ ቆርጦ እንደጠፍር-ብራቅ እምብርት እንደእሳተ ገሞራ ግት ‘ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው ደም ነው፥ ፍም ነው እሚያነባው፤ ንጥረ ሕዋስ ነው ሰቆቃው ረቂቅ ነው ምሥጢር ነው ጣሩ፥__ብቻውን ነው የሚፈታው፥ ብቻውን ነው የሚረታው፡፡ ችሎ፥ ውጦ፥ ተጨብጦ፥ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ በአንጀቱ ገበና ቀብሮ ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ፥ እንደደመና ተቋጥሮ ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ በሲቃ ግት ተሰትሮ፥..... ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ ከቤተ-ሰው ተደብቆ አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ፥ ተሸሽጎ ተከናንቦ፥ ተሸማቆ ተሸምቆ...... የብቻ ብቸኝነቱ፥ የጭለማ ልብሱ እስኪደርስ በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ ተገልሎ በእኩለ-ሌት፥ ወንድ ብቻውን ነው እሚያለቅስ፡፡ ( ጸጋዬ ገብረ መድኅን ) -
More Stories