አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ9 ልምዶች
1- ልንተኛ ስንል መመገብ
(ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡)

2- ያልተመጠነ እንቅልፍ
(ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡)

3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ
(በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ )
4- ጭንቀት እና ውጥረት
(አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡)
5- በፍጥነት መመገብ
(በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ )

6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት)
(የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ )

7- ቁርስን መዝለል
(የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡)

8- የበዛ ጨው መጠቀም
(ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ )

9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ
(የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው፡፡ ) ሼር ያድርጉ
አላስፈላጊ ስብ እንዲኖረን ምክኒያት የሚሆኑ9 ልምዶች 1- ልንተኛ ስንል መመገብ (ከምናዳብራቸው አላስፈላጊ ልምዶች መኀከል አንዱ እና ዋነኛው ልንተኛ አከባቢ የመቀማመስ ባህላችን ነው፡፡ ሰውነት በዛ ሰዓት በተገቢው መልኩ የሰጠነውን ነገር መፍጨት ስልማይችል በእንቅልፋችን እና በ መጨረሻው ምግባችን መሀል የሚኖረውን ልዩነትማስፋት ይኖርብናል፡፡) 2- ያልተመጠነ እንቅልፍ (ለሰውነታችን ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ካላበጀንለት ሰውነታችን ለ ሆረሞን መዛባት ይጋለጣል ፡፡ይህ ደግሞ የፍላጎት መዘበራረቅን ስለሚያስከትል የእንቅልፍ እጥረትን እንደምግብ እጥረት እንዲረዳው በማድረግ የምግብ አወሳሰዳችን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡) 3- ከልብ ሳይሆኑ መመገብ (በ ቲቪ፣ በ ሞባይልም ሆነ በተለያዩ ነገሮች ውስጥ ተውጠን የምንመገብ ሲሆን ከ ሌላው ጊዜ በ 50% የበለጠ ካሎሪ እንደምንወስድ የአሜሪካን ጆረናል ኦፍ ኒውትሪሽን ያደረገው ጥናት ያመለክታል፡፡ ) 4- ጭንቀት እና ውጥረት (አሜሪካን ውስጥ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው እንደዚህ ያለ የስሜት መረበሽ ከፍተኛ የሆነ የስሜት ረሀብን ስለሚያስከትል አብኛው ሰው በመመገብ ከዚህ ስሜት ለመሸሽ ይሞክራል ይህ ደግሞ ለአላስፈላጊ ውፍረት ያጋልጣል፡፡) 5- በፍጥነት መመገብ (በችኮላ መመገብ እየተመገብን ያለነውን ምግብ በተገቢው መንገድ ማላመጥ እንዳንችል ያደርጋል ይህ ደግሞ ያለመጥገብ ስሜትን ስለሚፈጥር ብዙ እንድንመገብ ምክኒያት ይሆናል፡፡ ሳይንስ እንደሚያመለክትው የሰው ልጅ በተረጋጋ መልኩ ከተመገበ እስከ 20 ደቂቃ ሊፈጅበት ይችላል ይህ ደግሞ በተገቢው መንገድ እንድናላምጥ እና እየበላን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያረግ ቶሎ የመጥገብን ስሜት ይፈጥራል፡፡ ) 6- እንቅስቃሴ አለማረግ(እረፍት ማብዛት) (የአካል እንቅስቃሴ ለጤና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ሁሉ አላስፈላጊ ስቦችንም ያጠፋል፡፡ ሰዎች አንድ ቦታ ላይ ሲቆዩ ያለምክኒያት የመመገብ በሀሪያቸው ይዳብራል፡፡ ) 7- ቁርስን መዝለል (የጤና ባለሞያዎች የቁርስ ሰዓት ለሰው ልጅ ወሳኙ የምግብ ሰዓት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቀኑ የሜታቦሊዝም ስርዓታችንን ለሰውነታችን የሚወስንለት ከመሆኑም ባሻገር በቀን ውስጥ የምንመገበውን ካሎሪም በተገቢው መንገድ መሰባባር እንዲችል ይረዳዋል፡፡) 8- የበዛ ጨው መጠቀም (ከመጠን ያለፈ የጨው አጠቃቀም አላስፈላጊ የፈሳሽ ክምችት እንዲኖረን በማድረግ ለ ደም ግፊት የሚያጋልጠን ከመሆኑም በላይ ለአላስፈላጊ ውፍረትም ይዳርገናል፡ ) 9- በቂ ፈሳሽ አለመውሰድ (የሰው ልጅ በ አማካኝ በ ቀን 2 ሊትር ውሃ መውሰድ የሚኖርበት እደሆነ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ፈሳሽ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ከሰውነታችን ውስጥ እንድናስወግድ ከማድረጉም በላይ የሰውነታችንን ስብ የመቀነስም አቅም አለው፡፡ ) ሼር ያድርጉ
Like
1
0 Comments 0 Shares