• አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ3 ቢሊየን ብር ወጪ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው።

    “ህዳሴ ግራንድ ሞል” በሚል ስያሜ የሚጠራው የገበያ ማዕከል ግንባታው በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በተቋቋመው ህዳሴ አክሲዮን ማህበር ይከናወናል ነው የተባለው።

    ይህ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል በ125 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የሚያርፍ ሲሆን፥ ጠቅላላ የግቢው ስፋት 250 ሺህ ካሬ ሜትር ይሸፍናል።

    የህዳሴ ግራንድ ሞል ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ መኮንን በሰጡት መግለጫ፥ የገበያ ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ከሚገኙት በስፋቱና በዘመናዊነቱ የላቀ ይሆናል።

    ግንባታው የከተማ አስተዳደሩ ለአክሲዮን ማህበሩ ካመቻቻቸው ዘጠኝ ቦታዎች በአንዱ ላይ ይከናወናል።

    የገበያ ማዕከሉ በውስጡ 5 ሺህ ሱቆች፣ 2 ዘመናዊ ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች፣ ባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም ካፌና ሬስቶራንቶችን የሚይዝ ነው።

    ማዕከሉ በአንድ ጊዜ 8 ሺህ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጫ፥ እንዲሁም የመኖሪያ አፓርታማዎች እንደሚኖሩትም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

    ግንባታው ሲጠናቀቅ ለ35 ሺህ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥር ለኢዜአ የገለጹት አቶ ደረጀ፥ ነጋዴውና ሸማቹ ግብይታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

    ግንባታውን ለማስጀመር ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

    የገበያ ማዕከሉ ግንባታ በሶስት ዓመት ጊዜ ተጠናቆ ስራ እንደሚጀምርም አቶ ደረጀ ጠቁመዋል።
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ3 ቢሊየን ብር ወጪ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው። “ህዳሴ ግራንድ ሞል” በሚል ስያሜ የሚጠራው የገበያ ማዕከል ግንባታው በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በተቋቋመው ህዳሴ አክሲዮን ማህበር ይከናወናል ነው የተባለው። ይህ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል በ125 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የሚያርፍ ሲሆን፥ ጠቅላላ የግቢው ስፋት 250 ሺህ ካሬ ሜትር ይሸፍናል። የህዳሴ ግራንድ ሞል ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ መኮንን በሰጡት መግለጫ፥ የገበያ ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ከሚገኙት በስፋቱና በዘመናዊነቱ የላቀ ይሆናል። ግንባታው የከተማ አስተዳደሩ ለአክሲዮን ማህበሩ ካመቻቻቸው ዘጠኝ ቦታዎች በአንዱ ላይ ይከናወናል። የገበያ ማዕከሉ በውስጡ 5 ሺህ ሱቆች፣ 2 ዘመናዊ ባለ አራት ኮከብ ሆቴሎች፣ ባንክና ኢንሹራንስ እንዲሁም ካፌና ሬስቶራንቶችን የሚይዝ ነው። ማዕከሉ በአንድ ጊዜ 8 ሺህ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጫ፥ እንዲሁም የመኖሪያ አፓርታማዎች እንደሚኖሩትም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል። ግንባታው ሲጠናቀቅ ለ35 ሺህ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥር ለኢዜአ የገለጹት አቶ ደረጀ፥ ነጋዴውና ሸማቹ ግብይታቸውን በአንድ ቦታ እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል። ግንባታውን ለማስጀመር ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል። የገበያ ማዕከሉ ግንባታ በሶስት ዓመት ጊዜ ተጠናቆ ስራ እንደሚጀምርም አቶ ደረጀ ጠቁመዋል።
    WWW.FANABC.COM
    FBC - በአዲስ አበባ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በ3 ቢሊየን ብር ሊገነባ ነው
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ3 ቢሊየን ብር ወጪ ግዙፍ የገበያ ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው። “ህዳሴ ግራንድ ሞል” በሚል ስያሜ የሚጠራው የገበያ ማዕከል ግንባታው በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች በተቋቋመው ህዳሴ አ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው።

    ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጥናትና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሪፖርት ይቀርባል።

    በጉባኤው በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ምክክር እንደሚካሄድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አመልክቷል።

    ከዚህ ባለፈም በአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያም ምክክር ይካሄዳል ነው የተባለው።

    በጉባኤው ህግ አውጭዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

    ተሳታፊዎቹን ጨምሮ ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ለቢዝነስ ሰዎችና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል።

    ጉባኤው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጋር በመሆን በቅንጅት ያዘጋጁት ነው።

    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም በርካታ አባል ሃገራት ያሉት ሲሆን፥ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊ ጥናት እያደረገ የጥናቱን ግኝት ይፋ ያደርጋል።
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው። ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጥናትና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሪፖርት ይቀርባል። በጉባኤው በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ምክክር እንደሚካሄድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አመልክቷል። ከዚህ ባለፈም በአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያም ምክክር ይካሄዳል ነው የተባለው። በጉባኤው ህግ አውጭዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ተሳታፊዎቹን ጨምሮ ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ለቢዝነስ ሰዎችና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል። ጉባኤው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጋር በመሆን በቅንጅት ያዘጋጁት ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም በርካታ አባል ሃገራት ያሉት ሲሆን፥ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊ ጥናት እያደረገ የጥናቱን ግኝት ይፋ ያደርጋል።
    WWW.FANABC.COM
    FBC - የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው። ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል።

    ድጋፉ በተለይ ለአልሚ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ 277 ሺህ ህጻናት እና ሴቶች አስቸኳይ እርዳታዎችን ለመስጠት ያገዛል ተብሏል።

    በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ላ ይፋን በእርዳታ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት፥ ቻይና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር በመሆኗ የተቻላትን ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡

    “በማደግ ላይ የምንገኝ ሀገር ብንሆንም በአለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ ማደረግ አለብን” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

    የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን በተመለከተ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደሩ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቀነስ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

    በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ በበኩላቸው፥ ቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ኢትዮጵውያን እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው፥ በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ከ50 አመታት ወዲህ የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል።

    የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ አቅም ደርቁን ለመቋቋም እና ለዜጎቹ በወቅቱ አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ መሆኑን ያደነቁት ዳይሬክተሩ፥ አለም አቀፉ ማህበረሰብም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

    በዚህ ወቅት ቻይና ያደረገችው እርዳታንም በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡

    የኢትዮጵያ መንግስት የአልሚ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ቁጥርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮገራም በደረ ገጹ የጠቀሰ ሲሆን፥ 40 በመቶ ከሚሆኑ ህጻናት ውስጥ 9 በመቶው የመቀጨር ችግር ያሉባቸው በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁሟል፡፡

    ምንጭ ፦http://www.vanguardngr.com
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ በተለይ ለአልሚ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ 277 ሺህ ህጻናት እና ሴቶች አስቸኳይ እርዳታዎችን ለመስጠት ያገዛል ተብሏል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ላ ይፋን በእርዳታ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት፥ ቻይና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር በመሆኗ የተቻላትን ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡ “በማደግ ላይ የምንገኝ ሀገር ብንሆንም በአለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ ማደረግ አለብን” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን በተመለከተ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደሩ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቀነስ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ በበኩላቸው፥ ቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ኢትዮጵውያን እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው፥ በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ከ50 አመታት ወዲህ የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ አቅም ደርቁን ለመቋቋም እና ለዜጎቹ በወቅቱ አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ መሆኑን ያደነቁት ዳይሬክተሩ፥ አለም አቀፉ ማህበረሰብም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በዚህ ወቅት ቻይና ያደረገችው እርዳታንም በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የአልሚ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ቁጥርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮገራም በደረ ገጹ የጠቀሰ ሲሆን፥ 40 በመቶ ከሚሆኑ ህጻናት ውስጥ 9 በመቶው የመቀጨር ችግር ያሉባቸው በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁሟል፡፡ ምንጭ ፦http://www.vanguardngr.com
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ቻይና በኢትዮጵያ ለድርቅ ተጎጂዎች የሚውል 8 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የሰብአዊ ደጋፍ አደረገች
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ...
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ።

    የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል።

    በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል።

    ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል።

    ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል።

    በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል።

    ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ።

    ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት።

    ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል።

    የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

    በስላባት ማናዬ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል። በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል። ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል። ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል። በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል። ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ። ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት። ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል። የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል። በስላባት ማናዬ
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ከሳዑዲ ተመላሾች ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እን...
    0 Comments 0 Shares