አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው።

ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጥናትና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሪፖርት ይቀርባል።

በጉባኤው በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ምክክር እንደሚካሄድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አመልክቷል።

ከዚህ ባለፈም በአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያም ምክክር ይካሄዳል ነው የተባለው።

በጉባኤው ህግ አውጭዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ተሳታፊዎቹን ጨምሮ ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ለቢዝነስ ሰዎችና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል።

ጉባኤው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጋር በመሆን በቅንጅት ያዘጋጁት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም በርካታ አባል ሃገራት ያሉት ሲሆን፥ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊ ጥናት እያደረገ የጥናቱን ግኝት ይፋ ያደርጋል።
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው። ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከተ ጥናትና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሪፖርት ይቀርባል። በጉባኤው በአለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ ምክክር እንደሚካሄድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አመልክቷል። ከዚህ ባለፈም በአየር ንብረት ለውጥ ፈተናዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያም ምክክር ይካሄዳል ነው የተባለው። በጉባኤው ህግ አውጭዎች፣ የሲቪል ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃንና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ተሳታፊዎቹን ጨምሮ ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ ለቢዝነስ ሰዎችና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይሰጣልም ተብሏል። ጉባኤው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጋር በመሆን በቅንጅት ያዘጋጁት ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም በርካታ አባል ሃገራት ያሉት ሲሆን፥ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ሳይንሳዊ ጥናት እያደረገ የጥናቱን ግኝት ይፋ ያደርጋል።
WWW.FANABC.COM
FBC - የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም ጉባኤ በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 20 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ተቋም መደበኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ሊያካሂድ ነው። ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የአየር ንብረት ለውጥን የተመለከ...
0 Comments 0 Shares