0 Comments
0 Shares
Directory
-
Please log in to like, share and comment!
-
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት ደረጃ ኢትዮጵያ በነበረችበት 124ኛ ላይ ተቀመጠች።
ወርሃዊው የፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ባላፈው ወር 20 ደረጃዎችን ማሽቆልቆሏ የሚታወስ ነው፡፡
ፊፋ ባወጣው የወሩ ደረጃም ብራዚል፣ አርጀንቲና እና ጀርመን ካለፈው ወር የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ ባሉበት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
ከአፍሪካ ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
የአፍካ መሪዎቹ ሀገራት ከዓለም በደረጃቸው ቅደም ተከተል መሰረት 19ኛ፣ 30ኛ፣ 33ኛ ላይ ይገኛሉ፡፡
በወሩ ማላዊ 14 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚዋ ስትሆን 114ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ከፍተኛ የደረጃ ማሻሻል ያሳዩ ሀገራት ደግሞ ማዳጋስካር 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 7 ደረጃዎችን በማሻሻል 146ኛ ደረጃን መያዛቸው በመረጃው ተጠቅሷል።
በደረጃው ግርጌ ላይ ደግሞ አንጉይላ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጂብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ያለምንም ነጥብ 206ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን ከፊፋ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት ደረጃ ኢትዮጵያ በነበረችበት 124ኛ ላይ ተቀመጠች። ወርሃዊው የፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል። ኢትዮጵያ ባላፈው ወር 20 ደረጃዎችን ማሽቆልቆሏ የሚታወስ ነው፡፡ ፊፋ ባወጣው የወሩ ደረጃም ብራዚል፣ አርጀንቲና እና ጀርመን ካለፈው ወር የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ ባሉበት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ከአፍሪካ ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። የአፍካ መሪዎቹ ሀገራት ከዓለም በደረጃቸው ቅደም ተከተል መሰረት 19ኛ፣ 30ኛ፣ 33ኛ ላይ ይገኛሉ፡፡ በወሩ ማላዊ 14 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚዋ ስትሆን 114ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከፍተኛ የደረጃ ማሻሻል ያሳዩ ሀገራት ደግሞ ማዳጋስካር 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 7 ደረጃዎችን በማሻሻል 146ኛ ደረጃን መያዛቸው በመረጃው ተጠቅሷል። በደረጃው ግርጌ ላይ ደግሞ አንጉይላ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጂብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ያለምንም ነጥብ 206ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን ከፊፋ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።0 Comments 0 Shares -
በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ አሸንፏል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ አንድ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ባለድል ሆኗል።
በባላይዶስ ስታዲየም የስፔኑ ሴልታቪጎ ከማንቼስተር ዩናይትድ ተጫውተዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ባደረጉት ጨዋታ፥ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን አሳርፈው ወደ ሜዳ የገቡት ሴልታቪጎዎች ያሰቡትን አላሳኩም።
ማንቼስተር ዩናይትዶች በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ መንቀሳቀስ እና የጎል እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻሉ።
በዚህ የጨዋታ ጊዜ ወጣቱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከሳጥን ውጭ የግቡ ማዕዘን ላይ የመታት ኳስ በእለቱ ኮከብ በነበረው ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ አልቫሬዝ ጥረት ከሽፋለች።
ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ሄንሪክ ሚኪታሪያን እና ጀሴ ሌንጋርድ ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ወደ ጎል መቀየር አልቻሉም።
ግብ ጠባቂው በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ኳሶችን ማዳን ችሏል።
በአንጻሩ ሴልታቪጎዎች በዚህ የጨዋታ ጊዜ የሚያስቆጭ የጎል እድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።
አማካዩ ዋስ ከመሃል የተሻገረለትን ኳስ ነጻ ሆኖ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ከእረፍት መልስ ባለሜዳዎቹ የተሻለ ወደ ጎል መቅረብ ቢችሉም ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም።
በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ የተወሰደባቸው ማንቼስተር ዩናይትዶች በራሽፎርድ የ67ኛው ደቂቃ ጎል ጨዋታውን 1 ለ 0 መምራት ችለዋል።
ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ዩናይትድ በዚህ አመት ያደረገውን 58ኛ ጨዋታ በድል መወጣት ችሏል።
የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ኦልድትራፎርድ ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ አሸናፊው በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል።
ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ አምስተርዳም አሬና ላይ አያክስ አምስተርዳም ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ አሸንፏል አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ አንድ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ባለድል ሆኗል። በባላይዶስ ስታዲየም የስፔኑ ሴልታቪጎ ከማንቼስተር ዩናይትድ ተጫውተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ባደረጉት ጨዋታ፥ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን አሳርፈው ወደ ሜዳ የገቡት ሴልታቪጎዎች ያሰቡትን አላሳኩም። ማንቼስተር ዩናይትዶች በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ መንቀሳቀስ እና የጎል እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻሉ። በዚህ የጨዋታ ጊዜ ወጣቱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከሳጥን ውጭ የግቡ ማዕዘን ላይ የመታት ኳስ በእለቱ ኮከብ በነበረው ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ አልቫሬዝ ጥረት ከሽፋለች። ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ሄንሪክ ሚኪታሪያን እና ጀሴ ሌንጋርድ ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ወደ ጎል መቀየር አልቻሉም። ግብ ጠባቂው በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ኳሶችን ማዳን ችሏል። በአንጻሩ ሴልታቪጎዎች በዚህ የጨዋታ ጊዜ የሚያስቆጭ የጎል እድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። አማካዩ ዋስ ከመሃል የተሻገረለትን ኳስ ነጻ ሆኖ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ከእረፍት መልስ ባለሜዳዎቹ የተሻለ ወደ ጎል መቅረብ ቢችሉም ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም። በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ የተወሰደባቸው ማንቼስተር ዩናይትዶች በራሽፎርድ የ67ኛው ደቂቃ ጎል ጨዋታውን 1 ለ 0 መምራት ችለዋል። ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ዩናይትድ በዚህ አመት ያደረገውን 58ኛ ጨዋታ በድል መወጣት ችሏል። የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ኦልድትራፎርድ ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ አሸናፊው በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል። ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ አምስተርዳም አሬና ላይ አያክስ አምስተርዳም ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።0 Comments 0 Shares -
27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል
አዲስ አበባ በ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል።
በርካታ ተመልካቾችን ወደ ሜዳ የሳበው የዘንድሮው አመት ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የአራት ሳምንታት መርሃ ግብሮች ብቻ ይቀሩታል።
ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፥ 8 ሰዓት ከ30 ላይ መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።
10 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በ24 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል።
ፕሪሚየር ሊጉ እሁድ ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰዓት ከ30 ደደቢት ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።
በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ 10 ሰዓት ከ30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ።
በክልል ከተሞች ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን ሲያስተናግድ፥ ሃዋሳ ከተማ ከወልዲያ ከተማ ይጫወታሉ።
ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባቡና የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማና ወላይታ ዲቻ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል።
ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊሰ በ49 ነጥብ ይመራዋል፥ ሲዳማ ቡና በ46 እንዲሁም ደደቢት በ45 ነጥቦች ይከተላሉ።
ድሬዳዋ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዲስ አበባ ከተማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።
በዘላለም ተፈሪ27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል አዲስ አበባ በ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል። በርካታ ተመልካቾችን ወደ ሜዳ የሳበው የዘንድሮው አመት ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የአራት ሳምንታት መርሃ ግብሮች ብቻ ይቀሩታል። ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፥ 8 ሰዓት ከ30 ላይ መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ። 10 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በ24 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል። ፕሪሚየር ሊጉ እሁድ ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰዓት ከ30 ደደቢት ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ። በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ 10 ሰዓት ከ30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ። በክልል ከተሞች ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን ሲያስተናግድ፥ ሃዋሳ ከተማ ከወልዲያ ከተማ ይጫወታሉ። ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባቡና የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማና ወላይታ ዲቻ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል። ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊሰ በ49 ነጥብ ይመራዋል፥ ሲዳማ ቡና በ46 እንዲሁም ደደቢት በ45 ነጥቦች ይከተላሉ። ድሬዳዋ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዲስ አበባ ከተማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ። በዘላለም ተፈሪ0 Comments 0 Shares -
ከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች ሊሰረዙ ይችላሉ መባሉ አግባብ አይደለም - አትሌት ቀነኒሳ
ከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች ሊሰረዙ ይችላሉ መባሉ አግባብ አይደለም - አትሌት ቀነኒሳ
туристический онлайн-справочник
Лучшие Андроид планшеты
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች እንዲሰረዙ ለአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
ከ2005 በፊት የተመዘገቡት ሪከርዶች የሽንትና የደም ናሙና በማይሰበሰብበት ዘመን የተሰበሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምናልባትም የአበረታች መድሃኒት ተጠቅመው በተወዳደሩ አትሌቶች የተሰበሩ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ነው የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ጥያቄውን ያቀረበው።
የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በመጪው ሰኔ ወር በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤም ይህንኑ ጥያቄ ሊያጸድቀው እንደሚችል መገመቱን ተከትሎ የተለያዩ አትሌቶች ከወዲሁ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
በ2004 የ5 ሺህ ሜትርን በ2005 ደግሞ የ10 ሺህ ሜትርን ሪከርድ ያስመዘገበው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት፥ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2005 በፊት የተሰበሩ የአለም ሪከርዶች የሽንት እና የደም ናሙና ባልተወሰደበት ጊዜ የተመዘገቡ ናቸው በሚል ሪከርዶቹ ሊሰረዙ ይገባል መባሉ አግባብ አይደለም ብሏል።
አትሌት ቀነኒሳ ችግሩ ከአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአሰራር ድክመት የመጣ እንጂ የአትሌቶች ችግር እንዳልሆነም ተናግሯል።
ቀነኒሳ በጉዳዩ ዙሪያም ተቃውሞ ለማሰማት መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው።
በ2003 የለንደን ማራቶን የአለም ሪከርድን ያስመዘገበችው እንግሊዛዊቷ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ከጋርዲያን ጋር ባደረገችው ቆይታ፥ ሪከርዶቹ ይሰረዙ የሚለው ሀሳብ ለቀድሞ አትሌቶች ክብር ከማጣት የመጣ ነው ብላለች።
የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳያገኝም የራሷን ጥረት እንደምታደርግ አስታውቃለች።
በእዩኤል ዘሪሁንከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች ሊሰረዙ ይችላሉ መባሉ አግባብ አይደለም - አትሌት ቀነኒሳ ከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች ሊሰረዙ ይችላሉ መባሉ አግባብ አይደለም - አትሌት ቀነኒሳ туристический онлайн-справочник Лучшие Андроид планшеты አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2005 በፊት የተመዘገቡ የአለም ሪከርዶች እንዲሰረዙ ለአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ከ2005 በፊት የተመዘገቡት ሪከርዶች የሽንትና የደም ናሙና በማይሰበሰብበት ዘመን የተሰበሩ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምናልባትም የአበረታች መድሃኒት ተጠቅመው በተወዳደሩ አትሌቶች የተሰበሩ ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ነው የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ጥያቄውን ያቀረበው። የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በመጪው ሰኔ ወር በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባኤም ይህንኑ ጥያቄ ሊያጸድቀው እንደሚችል መገመቱን ተከትሎ የተለያዩ አትሌቶች ከወዲሁ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በ2004 የ5 ሺህ ሜትርን በ2005 ደግሞ የ10 ሺህ ሜትርን ሪከርድ ያስመዘገበው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው አስተያየት፥ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2005 በፊት የተሰበሩ የአለም ሪከርዶች የሽንት እና የደም ናሙና ባልተወሰደበት ጊዜ የተመዘገቡ ናቸው በሚል ሪከርዶቹ ሊሰረዙ ይገባል መባሉ አግባብ አይደለም ብሏል። አትሌት ቀነኒሳ ችግሩ ከአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአሰራር ድክመት የመጣ እንጂ የአትሌቶች ችግር እንዳልሆነም ተናግሯል። ቀነኒሳ በጉዳዩ ዙሪያም ተቃውሞ ለማሰማት መዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው። በ2003 የለንደን ማራቶን የአለም ሪከርድን ያስመዘገበችው እንግሊዛዊቷ አትሌት ፓውላ ራድክሊፍ ከጋርዲያን ጋር ባደረገችው ቆይታ፥ ሪከርዶቹ ይሰረዙ የሚለው ሀሳብ ለቀድሞ አትሌቶች ክብር ከማጣት የመጣ ነው ብላለች። የአውሮፓ አትሌቲክስ ማህበር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳያገኝም የራሷን ጥረት እንደምታደርግ አስታውቃለች። በእዩኤል ዘሪሁን0 Comments 0 Shares -
በእህቴ ሰርግ ላይ እንዴት እንደዛ ብለው
ይዘፍናሉ.....?
(አሌክስ አብርሃም ላላነበቡት ብቻ)
እህቴ ስታገባ እቤታችን ሰርግ ተደግሶ
ነበር፡፡ ያውም ድል ያለ ሰርግ ፡፡ ለመጀመሪያ
ጊዜ በሰርግ የተደሰትኩት የዛን ጊዜ ነው ፡፡
እህቴን ከነኮተቷ ከቤት የሚወስድ ጅል ሲገኝ
እንዴት አልደሰትም!!
የመንደሩ ሰው ሁሉ ..‹‹.እች ልጅ ቁማ መቅረቷ ነው?..›› እያለ ሲያማት እሷም በሙሉ ሃይሏ
እየዘነጠችና እየተቆነጃጀች (ባል አጥቸ
ሳይሆን የሚመጥነኝ ጠፍቶ ነው) አይነት ጉራ
ቀመስ መልክት እያስተላለፈች
ስትኖር ....በአንድ የተንሸዋረረ ቅዳሜ እህቴ
ባል የሚሆናትን ልጅ አገኘች (ማነው ስሙ አሜሪካንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኝ እንደሷ
አልተደሰተም)፡፡
እንዴት እንደተገኛኙ ባይገባኝም ልክ በወጥመድ
እንደተያዘ ወፍ አጣድፋ ትዳር የሚባል ትልቅ
የብረት ድስት ውስጥ ከተተችው፡፡ እንደዜጋ
ልጁ ቢያሳዝነኝም የእህቴም ችግር ይገባኛልና ‹‹ኧረ አስብበት›› ለማለት አልደፈርኩም፡፡
ሰርጉ ተደገሰ ለእህቴ ሚዜ ለመሆን የአገር
ሴቶች ተሰበሰቡ (አሁን ሚዜ መሆን ምን ያሻማል)
እና ሰርጉ ደርሶ ሚዜ ተብየወቹ ነፍሳቸውን
እስኪስቱ ዘንጠው በቀለም የጥምቀት ዱላ
መስለው .. የገናም አባት መስለው... አበባ አንከርፍፈውና ተራቁተው እግረ ሚዜነታቸውን
ለራሳቸው ከሰርገኛው መሃል ባል እየፈለጉ
እያለ ሙሽራው መጣ (እኔማ ይቀራል ብየ ነበር
የሚገርም ደፋር ነው)
ከመጣም በኋላ ካሁን አሁን ‹‹ይሄ ነገር ሳስበው
ቢቀርብኝ ይሻላል ›› ይላል እያልኩ ስሰጋ ....እነዛ ቀልቃላ ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም
ሰርገኛ›› ብለው እርፍ!!....እንዴዴዴዴዴ እች
ልጅ ሚዜ ነው ምቀኛ የሰበሰበችው ብየ የመጨረሻ
ተበሳጨሁ በአእርግጠኝነት ሙሽራው ‹‹ታዲያ የት
ልግባ ቢል›› ሁሉም ሚዜወች ላዳ ተከራይተው
እቤታቸው ነበር የሚወስዱት !! በስንት መከራ የተገኘ ባል ‹‹አናስገባም››! እኔ
ወደፊት ስሞት መላአእክት ወደገነት
‹‹አናስገባም›› ቢሉኝ እራሱ እንደዚያ ቀን
የምደነግጥ አይመስለኝም!! ይታያችሁ እህቴ ባል ለማግባት ለኪዳነ ምህረት
፣ለገብሬል ...ለማሪያም...የተሳለችው መጋረጃ
ቢቀጣጠል አንድ ክፍለ ከተማ
ይጋርዳል ....የተሳለችው ጧፍ የብዙ ደብሮችን
የአመት የጧፍ ፍጆታ ይችላል...እና ሚዜወቿ
‹‹አናስገባም›› እያሉ በእሳት ይጫወታሉ !! አባባ በሩን ለሰርጉ ብሎ ሰፋ ያስደረገው ቶሎ
ይዞልን እንዲሄድ አይደል እንዴ ! ወይ ሚዜ !
ወይ ሴቶች ! ለሞላ ዘፈን
‹‹አናስገባም›› ....ቀስ ብየ ወደዲጀው ጠጋ
አልኩና በጆሮው መፍትሄ ነገር ሹክ አልኩት
‹‹ኧረ አሌክስ ይሄማ አሁን አይከፈትም ሲወጠጡ ነው ›› አለኝ ...አትሸኟትም ወይ የሚለውን
የፀጋየ እሸቱን የሰርግ ዘፈን ነበር ክፈትልን
ያልኩትበእህቴ ሰርግ ላይ እንዴት እንደዛ ብለው ይዘፍናሉ.....? (አሌክስ አብርሃም ላላነበቡት ብቻ) እህቴ ስታገባ እቤታችን ሰርግ ተደግሶ ነበር፡፡ ያውም ድል ያለ ሰርግ ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰርግ የተደሰትኩት የዛን ጊዜ ነው ፡፡ እህቴን ከነኮተቷ ከቤት የሚወስድ ጅል ሲገኝ እንዴት አልደሰትም!! የመንደሩ ሰው ሁሉ ..‹‹.እች ልጅ ቁማ መቅረቷ ነው?..›› እያለ ሲያማት እሷም በሙሉ ሃይሏ እየዘነጠችና እየተቆነጃጀች (ባል አጥቸ ሳይሆን የሚመጥነኝ ጠፍቶ ነው) አይነት ጉራ ቀመስ መልክት እያስተላለፈች ስትኖር ....በአንድ የተንሸዋረረ ቅዳሜ እህቴ ባል የሚሆናትን ልጅ አገኘች (ማነው ስሙ አሜሪካንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኝ እንደሷ አልተደሰተም)፡፡ እንዴት እንደተገኛኙ ባይገባኝም ልክ በወጥመድ እንደተያዘ ወፍ አጣድፋ ትዳር የሚባል ትልቅ የብረት ድስት ውስጥ ከተተችው፡፡ እንደዜጋ ልጁ ቢያሳዝነኝም የእህቴም ችግር ይገባኛልና ‹‹ኧረ አስብበት›› ለማለት አልደፈርኩም፡፡ ሰርጉ ተደገሰ ለእህቴ ሚዜ ለመሆን የአገር ሴቶች ተሰበሰቡ (አሁን ሚዜ መሆን ምን ያሻማል) እና ሰርጉ ደርሶ ሚዜ ተብየወቹ ነፍሳቸውን እስኪስቱ ዘንጠው በቀለም የጥምቀት ዱላ መስለው .. የገናም አባት መስለው... አበባ አንከርፍፈውና ተራቁተው እግረ ሚዜነታቸውን ለራሳቸው ከሰርገኛው መሃል ባል እየፈለጉ እያለ ሙሽራው መጣ (እኔማ ይቀራል ብየ ነበር የሚገርም ደፋር ነው) ከመጣም በኋላ ካሁን አሁን ‹‹ይሄ ነገር ሳስበው ቢቀርብኝ ይሻላል ›› ይላል እያልኩ ስሰጋ ....እነዛ ቀልቃላ ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም ሰርገኛ›› ብለው እርፍ!!....እንዴዴዴዴዴ እች ልጅ ሚዜ ነው ምቀኛ የሰበሰበችው ብየ የመጨረሻ ተበሳጨሁ በአእርግጠኝነት ሙሽራው ‹‹ታዲያ የት ልግባ ቢል›› ሁሉም ሚዜወች ላዳ ተከራይተው እቤታቸው ነበር የሚወስዱት !! በስንት መከራ የተገኘ ባል ‹‹አናስገባም››! እኔ ወደፊት ስሞት መላአእክት ወደገነት ‹‹አናስገባም›› ቢሉኝ እራሱ እንደዚያ ቀን የምደነግጥ አይመስለኝም!! ይታያችሁ እህቴ ባል ለማግባት ለኪዳነ ምህረት ፣ለገብሬል ...ለማሪያም...የተሳለችው መጋረጃ ቢቀጣጠል አንድ ክፍለ ከተማ ይጋርዳል ....የተሳለችው ጧፍ የብዙ ደብሮችን የአመት የጧፍ ፍጆታ ይችላል...እና ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም›› እያሉ በእሳት ይጫወታሉ !! አባባ በሩን ለሰርጉ ብሎ ሰፋ ያስደረገው ቶሎ ይዞልን እንዲሄድ አይደል እንዴ ! ወይ ሚዜ ! ወይ ሴቶች ! ለሞላ ዘፈን ‹‹አናስገባም›› ....ቀስ ብየ ወደዲጀው ጠጋ አልኩና በጆሮው መፍትሄ ነገር ሹክ አልኩት ‹‹ኧረ አሌክስ ይሄማ አሁን አይከፈትም ሲወጠጡ ነው ›› አለኝ ...አትሸኟትም ወይ የሚለውን የፀጋየ እሸቱን የሰርግ ዘፈን ነበር ክፈትልን ያልኩት0 Comments 0 Shares -
ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል
የአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡
ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡
በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ ደረጃ መክፈት ባለመቻሉ፣ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ውስጥ ለማስገባት ያቀደው 136,116 ኮንቴይነሮችን ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን 131,834 ኮንቴይነሮች ገብተዋል፡፡
በገቢ ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢንተርፕራይዙ በአጠቃላይ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው ግን 11.8 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 40 ኤጀንቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የምታመነጨው የውጭ ምንዛሪ ውስን እንደመሆኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ለተመረጡ ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ አንፃር የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ በተለይ በወራት ተከፋፍሎ ሲታይ ባለፈው መጋቢት የገቢ ዕቃ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤልሲ እየተከፈተ በመሆኑ የገቢ ዕቃ ጭማሪ ይኖራል፤›› ሲሉ አቶ መስፍን በቀጣዮቹ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በተያዘው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሪ በበቂ ደረጃ አላገኘም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2010 በርካታ መርከቦች ተገንብተው አብዛኛዎቹ ወደ ሥራ በመግባታቸው የሥራ ሽሚያ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የገበያ መቀዛቀዝ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር ትራንስፖርት የመጓጓዣ ዋጋ ላይም ቅናሽ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዓለም የንግድ እቅንስቃሴ እየቀዘቀዘ በመሆኑ፣ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ሥራ እያገኙ አይደለም ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲራጅ አቡዱላሂ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢንተርፕራይዙ ባሉት 11 መርከቦችና ከውጭ በሚከራያቸው መርከቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ወሽመጦችን እያቋረጠ 309 ወደቦችን ያዳርሳል ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የንግድ መዳረሻ የሆኑት የሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣ መካከለኛው ምሥራቅና ቱርክ ዋነኛ መዳረሻዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
አቶ መስፍን እንዳሉት፣ ኢንተርፕራይዙ ካለፈው ዓመት የተሸጋገሩ ገቢ ዕቃዎች ስለነበሩ በማጓጓዝ በኩል 98 በመቶ፣ በገቢ በኩል ደግሞ ከጂቡቲ ወደብ የሚነሱ ዕቃዎች ስለነበሩ በአጠቃላይ 90 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ከባህር ጉዞ በተጨማሪ በአገሪቱ በተገነቡ ሰባት ደረቅ ወደቦች 417 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት የማጓጓዝ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡
ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል የአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡ ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡ በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ ደረጃ መክፈት ባለመቻሉ፣ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ውስጥ ለማስገባት ያቀደው 136,116 ኮንቴይነሮችን ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን 131,834 ኮንቴይነሮች ገብተዋል፡፡ በገቢ ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢንተርፕራይዙ በአጠቃላይ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው ግን 11.8 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 40 ኤጀንቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የምታመነጨው የውጭ ምንዛሪ ውስን እንደመሆኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ለተመረጡ ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ አንፃር የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ በተለይ በወራት ተከፋፍሎ ሲታይ ባለፈው መጋቢት የገቢ ዕቃ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤልሲ እየተከፈተ በመሆኑ የገቢ ዕቃ ጭማሪ ይኖራል፤›› ሲሉ አቶ መስፍን በቀጣዮቹ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በተያዘው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሪ በበቂ ደረጃ አላገኘም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2010 በርካታ መርከቦች ተገንብተው አብዛኛዎቹ ወደ ሥራ በመግባታቸው የሥራ ሽሚያ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የገበያ መቀዛቀዝ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር ትራንስፖርት የመጓጓዣ ዋጋ ላይም ቅናሽ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዓለም የንግድ እቅንስቃሴ እየቀዘቀዘ በመሆኑ፣ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ሥራ እያገኙ አይደለም ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲራጅ አቡዱላሂ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢንተርፕራይዙ ባሉት 11 መርከቦችና ከውጭ በሚከራያቸው መርከቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ወሽመጦችን እያቋረጠ 309 ወደቦችን ያዳርሳል ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የንግድ መዳረሻ የሆኑት የሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣ መካከለኛው ምሥራቅና ቱርክ ዋነኛ መዳረሻዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ አቶ መስፍን እንዳሉት፣ ኢንተርፕራይዙ ካለፈው ዓመት የተሸጋገሩ ገቢ ዕቃዎች ስለነበሩ በማጓጓዝ በኩል 98 በመቶ፣ በገቢ በኩል ደግሞ ከጂቡቲ ወደብ የሚነሱ ዕቃዎች ስለነበሩ በአጠቃላይ 90 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከባህር ጉዞ በተጨማሪ በአገሪቱ በተገነቡ ሰባት ደረቅ ወደቦች 417 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት የማጓጓዝ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡0 Comments 0 Shares -
የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉ
ነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300
ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አሟልቶ መያዙ ተገልጿል። አቶ ፍስሐ ዓባይ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተገነባው
አዲስ ሳፋየር ሆቴል ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። በምሥሉ ላይ የሚታየው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ አዲስ ሳፋየር ሆቴል ነው።የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉ ነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አሟልቶ መያዙ ተገልጿል። አቶ ፍስሐ ዓባይ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተገነባው አዲስ ሳፋየር ሆቴል ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። በምሥሉ ላይ የሚታየው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ አዲስ ሳፋየር ሆቴል ነው።WWW.ETHIOPIANREPORTER.COMአዲስ ሳፋየር ሆቴል አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነውየአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና0 Comments 0 Shares