• 0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጀመሪያ ደረጃና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም የሚመራበት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ነው።

    በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በመማር ማስተማር ላይ የሚያደርስውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በመጀመሪያና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራም እንዲታቀፉ ተደርገዋል።

    የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም መንግስት በ198 ሚሊየን ብር የአስቸኳይ ጊዜ የምገባ ስርዓት ተግባራዊ እያደረገ ነው ብለዋል።

    ከአስቸኳይ ጊዜ የምገባ ፕሮግራም ውጪ በመጀመሪያ ደረጃና በቅደመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን መጠነ ማጠናቀቅ ለማሳደግ መደበኛና አስቸኳይ የምገባ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

    ይህም ህብረተሰቡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች በምገባ ስርዓቱ በተቀናጀ መልኩ አስተዋፅኦችን እንዲያበረክቱ ያስችላል ተብሏል።

    በበላይ ተስፋዬ
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጀመሪያ ደረጃና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም የሚመራበት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ነው። በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ በመማር ማስተማር ላይ የሚያደርስውን ተጽዕኖ ለመቀነስ በመጀመሪያና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራም እንዲታቀፉ ተደርገዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም መንግስት በ198 ሚሊየን ብር የአስቸኳይ ጊዜ የምገባ ስርዓት ተግባራዊ እያደረገ ነው ብለዋል። ከአስቸኳይ ጊዜ የምገባ ፕሮግራም ውጪ በመጀመሪያ ደረጃና በቅደመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን መጠነ ማጠናቀቅ ለማሳደግ መደበኛና አስቸኳይ የምገባ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል። ይህም ህብረተሰቡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች በምገባ ስርዓቱ በተቀናጀ መልኩ አስተዋፅኦችን እንዲያበረክቱ ያስችላል ተብሏል። በበላይ ተስፋዬ
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ለማጠናከር ፣ህገወጥ ስደትን ለመግታት እና መፈናቀልን ለመቀነስ የሚያግዘው 59 ሚሊየን ዮሮ መመደቡን አስታውቋል፡፡

    የአውሮፓ ህብረት በላከው መግለጫ ፥ ህብረቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የመደበው ገንዘብ ለሁሉም የቀጠናው ሀገራት ሰላም እና ልማት ፕሮጅክቶች የሚውል እንደሆነ ገልጿል፡፡

    የገንዘብ ድጋፉ በቀጠናው የሰላም ግንባታ፣የጸጥታና የመረጋጋት ስራዎችን ማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ልማትን ማሻሻልን ያለመ ነው፡፡

    ከተጠቀሰው ገንዘብ ውስጥ 40 ሚሊየን ዩሮ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ እና ለቀጠናው ሀገራት ሰላምን ለማስፈን ለሚረዱ ቁልፍ ተግባራት የሚውል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

    የኬኒያ ብሄራዊ ጸረ- ሽብር እንቅስቃሴ ስትራቴጂ ለመደገፍ በህብረቱ እና የኬኒያ ትብብር ማዕቀፍ 5 ሚሊየን ዩሮ ይውላል ተብሏል፡፡

    ለሰሜናዊ ደርፉር 10 ሚሊየን ዩሮ የተመደበ ሲሆን ፥በዚህ ገንዘብ 80ሺህ አነስተኛ አምራቾች በቀጥታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እና ወደ 700 ሺህ ሰዎች በተዘዋዋሪ የሚደግፍ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

    የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እና ልማት በመፍጠር የሰዎች ስደትን ለመከላከል ብርቱ እገዛ እንደሚኖረው ተዘግቧል፡፡

    አብዛኛው ገንዘብ የሚውለው ለስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት በተለይ ወጣቶችን እና ሴቶችን የሙያ ስልጠናዎች በመስጠት የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲጠናከሩ ይሆናል፡፡

    ምንጭ፦አውሮፓ ህብረት
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ለማጠናከር ፣ህገወጥ ስደትን ለመግታት እና መፈናቀልን ለመቀነስ የሚያግዘው 59 ሚሊየን ዮሮ መመደቡን አስታውቋል፡፡ የአውሮፓ ህብረት በላከው መግለጫ ፥ ህብረቱ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የመደበው ገንዘብ ለሁሉም የቀጠናው ሀገራት ሰላም እና ልማት ፕሮጅክቶች የሚውል እንደሆነ ገልጿል፡፡ የገንዘብ ድጋፉ በቀጠናው የሰላም ግንባታ፣የጸጥታና የመረጋጋት ስራዎችን ማጠናከር ብሎም ኢኮኖሚያዊ ትስስር እና ልማትን ማሻሻልን ያለመ ነው፡፡ ከተጠቀሰው ገንዘብ ውስጥ 40 ሚሊየን ዩሮ ለምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ እና ለቀጠናው ሀገራት ሰላምን ለማስፈን ለሚረዱ ቁልፍ ተግባራት የሚውል መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የኬኒያ ብሄራዊ ጸረ- ሽብር እንቅስቃሴ ስትራቴጂ ለመደገፍ በህብረቱ እና የኬኒያ ትብብር ማዕቀፍ 5 ሚሊየን ዩሮ ይውላል ተብሏል፡፡ ለሰሜናዊ ደርፉር 10 ሚሊየን ዩሮ የተመደበ ሲሆን ፥በዚህ ገንዘብ 80ሺህ አነስተኛ አምራቾች በቀጥታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እና ወደ 700 ሺህ ሰዎች በተዘዋዋሪ የሚደግፍ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም እና ልማት በመፍጠር የሰዎች ስደትን ለመከላከል ብርቱ እገዛ እንደሚኖረው ተዘግቧል፡፡ አብዛኛው ገንዘብ የሚውለው ለስራ ፈጠራ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት በተለይ ወጣቶችን እና ሴቶችን የሙያ ስልጠናዎች በመስጠት የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲጠናከሩ ይሆናል፡፡ ምንጭ፦አውሮፓ ህብረት
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጅማ ከተማ መንቲና ቀበሌ ማሪያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የቀበሌ አስተዳደሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተደርምሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

    አደጋው የደረሰው ትናንት ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ሲሆን፥ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎችም አዳራሹ ውስጥ ይኖሩ ነበር ተብሏል።

    በመደርመስ አደጋውም የሶስት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች ህይተው ነው ያለፈው።

    በተጨማሪም ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ያካል ጉዳት ደርሶባቸው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡

    በአዳራሹ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች አቅመ ደካማ አዛውንቶች ናቸው፡፡

    በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ አንድ የወንጀል ምርመራ እና ፍትህ አሰጪ ቡድን መሪ ረዳት ሳጅን ግዛቸው ገረመው አዳራሹ ላይ ከዚህ ቀደም የእሳት ቃጠሎ ደርሶ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር ብለዋል።

    ትናንት ሌሊት ለደረሰው አደጋ የእሳት አደጋው እና ቤቱ ያረጀ መሆኑ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

    በተመስገን አለባቸው
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጅማ ከተማ መንቲና ቀበሌ ማሪያም ሰፈር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የሚገኝ የቀበሌ አስተዳደሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተደርምሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ። አደጋው የደረሰው ትናንት ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ሲሆን፥ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎችም አዳራሹ ውስጥ ይኖሩ ነበር ተብሏል። በመደርመስ አደጋውም የሶስት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች ህይተው ነው ያለፈው። በተጨማሪም ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ያካል ጉዳት ደርሶባቸው በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው፡፡ በአዳራሹ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች አቅመ ደካማ አዛውንቶች ናቸው፡፡ በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ አንድ የወንጀል ምርመራ እና ፍትህ አሰጪ ቡድን መሪ ረዳት ሳጅን ግዛቸው ገረመው አዳራሹ ላይ ከዚህ ቀደም የእሳት ቃጠሎ ደርሶ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር ብለዋል። ትናንት ሌሊት ለደረሰው አደጋ የእሳት አደጋው እና ቤቱ ያረጀ መሆኑ ምክንያት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተመስገን አለባቸው
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

    ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

    ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

    በተለይም ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም መስፈንና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዋ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ላይ ይወያያሉ።

    እንዲሁም ሶማሊያን ወደ መረጋጋት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ተግባር በጋራ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው የሚመክሩ ይሆናል።

    የፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ጉብኝትም ለሁለት ቀናት የሚቆይ ነው።
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። በተለይም ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላም መስፈንና በሰላም ማስከበር ተልዕኮዋ ያበረከተችው አስተዋጽኦ ላይ ይወያያሉ። እንዲሁም ሶማሊያን ወደ መረጋጋት ለማምጣት እየተከናወነ ባለው ተግባር በጋራ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው የሚመክሩ ይሆናል። የፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ጉብኝትም ለሁለት ቀናት የሚቆይ ነው።
    0 Comments 0 Shares
  • በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ
    በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ በ170 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና ማቆሚያ ስፍራው ዘመናዊ ነው የተባለ ሲሆን 15 ፎቆች ላይ እንዲሁም በምድር ላይ መኪኖችን ያሳርፋል ተብሏል፡፡

    የመኪና ማቆሚያው በፎቆቹ ላይ 90 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሲሆን የምድሩ ደግሞ 50 መኪኖችን ማቆም እንደሚያስችል ወይዘሮ ታፈሱ አባይ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ለመኪና ማቆሚያዎቹ ሥፍራ ግንባታ በመንግሥት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ሰምተናል፡፡

    የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የሙከራ ሥራ የጀመሩት የመገናኛ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥፍራው በምን ያህል ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ግን ተመን አልወጣለትም ተብሏል፡፡

    የመኪና ማቆሚያ ሥፍራው ለ20 ዜጐች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድና ወሎ ሰፈር አካባቢዎች ላይም የተጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ የተባለ ቢሆንም መዘግየት አላጋጠመም ወይ ብለን የጠየቅናቸው ወይዘሮ ታፈሱ የወሎ ሰፈሩና የአንዋር ወስጊዱ በቅርቡ ይጠናቀቃል አልዘገየም ያሉ ሲሆን በቸርችል ጐዳና የሚገነባው ደግሞ ከመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ትንሽ ውዝግብ ተነስቶ ነበረ አሁን ችግሩ ስለተፈታ በቅርቡ ሥራው ይጀመራል ብለዋል፡፡

    በከተማዋ 60 የተመረጡ ቦታዎች ላይም ሌሎች የመኪና ማቆሚያዎች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
    በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ በ170 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና ማቆሚያ ስፍራው ዘመናዊ ነው የተባለ ሲሆን 15 ፎቆች ላይ እንዲሁም በምድር ላይ መኪኖችን ያሳርፋል ተብሏል፡፡ የመኪና ማቆሚያው በፎቆቹ ላይ 90 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሲሆን የምድሩ ደግሞ 50 መኪኖችን ማቆም እንደሚያስችል ወይዘሮ ታፈሱ አባይ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ለመኪና ማቆሚያዎቹ ሥፍራ ግንባታ በመንግሥት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ሰምተናል፡፡ የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የሙከራ ሥራ የጀመሩት የመገናኛ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥፍራው በምን ያህል ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ግን ተመን አልወጣለትም ተብሏል፡፡ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራው ለ20 ዜጐች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድና ወሎ ሰፈር አካባቢዎች ላይም የተጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ የተባለ ቢሆንም መዘግየት አላጋጠመም ወይ ብለን የጠየቅናቸው ወይዘሮ ታፈሱ የወሎ ሰፈሩና የአንዋር ወስጊዱ በቅርቡ ይጠናቀቃል አልዘገየም ያሉ ሲሆን በቸርችል ጐዳና የሚገነባው ደግሞ ከመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ትንሽ ውዝግብ ተነስቶ ነበረ አሁን ችግሩ ስለተፈታ በቅርቡ ሥራው ይጀመራል ብለዋል፡፡ በከተማዋ 60 የተመረጡ ቦታዎች ላይም ሌሎች የመኪና ማቆሚያዎች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ
    ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው መቀመጫቸውን በሪያድ ካደረጉት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ባለሥልጣን አንባሣደር አሚን አቡዱላሂ ነው፡፡

    የመከላከያ ሠራዊትን የጨመረው የሳውዲ መንግሥት የህገ-ወጥ የአሰሳ ግብረ-ሃይልን ጨምሮ በገጠር በእርሻ ቦታዎች የሚሰሩ የውጭ ዜጐችን አድኖ የሚይዝና በየቤቱም የተሰማራ ኃይል መቋቋሙን አምባሣደሩ ነግረውናል፡፡የሳውዲ ዜጐች ወረቀት የሌላቸውን የውጭ ሰዎች የሚቀጥሩ ከሆነ ከባድ ቅጣት የሚጥልባቸው አዋጅ ከማውጣቱም በላይ ማረሚያ ቤቱንም እያስፋፋ ነው ተብሏል፡፡

    የፖሊስና የማረሚያ ቤት የመከላከያ ሠራዊት አባላቱን ቁጥር ማብዛቱንም አምባሣደር አሚን ነግረውናል፡፡ሳውዲ አረቢያ በቅርቡ ከውጭ ሀገር ዜጐች የፀዳች ሳውዲ የሚለውን ኃሣባቸውን በፓርላማቸው በማፅደቃቸው ወረቀት አልባ ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ሳይዘናጉ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ብለዋል፡፡
    ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው መቀመጫቸውን በሪያድ ካደረጉት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ባለሥልጣን አንባሣደር አሚን አቡዱላሂ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊትን የጨመረው የሳውዲ መንግሥት የህገ-ወጥ የአሰሳ ግብረ-ሃይልን ጨምሮ በገጠር በእርሻ ቦታዎች የሚሰሩ የውጭ ዜጐችን አድኖ የሚይዝና በየቤቱም የተሰማራ ኃይል መቋቋሙን አምባሣደሩ ነግረውናል፡፡የሳውዲ ዜጐች ወረቀት የሌላቸውን የውጭ ሰዎች የሚቀጥሩ ከሆነ ከባድ ቅጣት የሚጥልባቸው አዋጅ ከማውጣቱም በላይ ማረሚያ ቤቱንም እያስፋፋ ነው ተብሏል፡፡ የፖሊስና የማረሚያ ቤት የመከላከያ ሠራዊት አባላቱን ቁጥር ማብዛቱንም አምባሣደር አሚን ነግረውናል፡፡ሳውዲ አረቢያ በቅርቡ ከውጭ ሀገር ዜጐች የፀዳች ሳውዲ የሚለውን ኃሣባቸውን በፓርላማቸው በማፅደቃቸው ወረቀት አልባ ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ሳይዘናጉ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ብለዋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares