• ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበርና አንቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ህገ-ወጥ የውህደት ድርጊትና የውህደት ቅንብር ፈፅመዋል በሚል...

    ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበርና አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ህገ-ወጥ የውህደት ድርጊትና የውህደት ቅንብር ፈፅመዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ ዛሬ መልስ ሰተዋል፡፡ሁለቱ አክሲዮን ማህበራት ህገ-ወጥ ውህደት በመፈፀም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ፈጥረዋል በማለት የከሰሳቸው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡ባለሥልጣኑ እንዳለው የአክሲዮን ማህበራቱ ኃላፊዎች ካለፈው ጥር ወር አንስቶ ውህደት መፈፀማቸውን በቃል ተናግረዋል፡፡

    በአከፋፋዮች ላይም የሁለታችንንም ምርቶች ነው መያዝ ያለባችሁ የሚል ግዴታ አስቀምጠዋል፡፡አንዱ የሌላውን አርማና የንግድ ምልክት መጠቀሙንም ባለሥልጣኑ በክሱ ላይ አስፍሯል፡፡ሁለቱ አክሲዮን ማህበራት በጋራ የሥራ አመራር አቅጣጫ ነድፈዋልም ብሏል፡፡የአንዱን አክሲዮን ማህበር ሠራተኛ ወደ ሌላው የማዘዋወር ተግባር ፈፅመዋል ሲልም ባለሥልጣኑ በክሱ ላይ አስፍሯል፡፡

    እነዚህ ተግባሮች በሁለቱ አክሲዮን ማህበራት መካከል ውህደት ወይም መቀላቀል መፈጠሩን የሚያረጋግጡ ናቸው ብሏል፡፡ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግና አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበራት በቃል ተዋህደናል ብላችኋል ተብሎ የተነገረው ስህተት ነው፣ ብንል እንኳ ውህደት የሚፈፀመው ብዙ ሂደት አልፎ በሰነድ ነው እንጂ በቃል አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አከፋፋዮች የሁለታችንንም ምርቶች እንዲይዙ ግዴታ አስቀምጣችኋል መባላችንም ስህተት ነው ሲሉም መልሰዋል፡፡አንዱ የሌላውን አርማ ተጠቅሟል በሚል የቀረበው ክስም ትክክል እንዳልሆነ በመቃወሚያቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

    በድርጅቶች መካከል ሰራተኛ መዋዋስ በኢትዮጵያ የተለመደ አሰራር መሆኑን በመጥቀስ ይህንን የሚከለክል ህግ የለም ሲሉም ተከራክረዋል፡፡በአጠቃላይ በሁለቱ አክሲዮን ማህበራት መካከል የተፈጠረ ውህደት የለም፤ ይህንን የሚያሣይ ማስረጃም በከሣሾቹ በኩል አልቀረበም ብለዋል፡፡ጉዳዩን እያየ ያለው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዳኝነት ችሎትን ብይን ለመስጠት ለነሐሴ 17፣2009 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡

    ንጋቱ ረጋሳ
    ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበርና አንቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ህገ-ወጥ የውህደት ድርጊትና የውህደት ቅንብር ፈፅመዋል በሚል... ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበርና አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበር ህገ-ወጥ የውህደት ድርጊትና የውህደት ቅንብር ፈፅመዋል በሚል ለቀረበባቸው ክስ ዛሬ መልስ ሰተዋል፡፡ሁለቱ አክሲዮን ማህበራት ህገ-ወጥ ውህደት በመፈፀም ተገቢ ያልሆነ ውድድር ፈጥረዋል በማለት የከሰሳቸው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ነው፡፡ባለሥልጣኑ እንዳለው የአክሲዮን ማህበራቱ ኃላፊዎች ካለፈው ጥር ወር አንስቶ ውህደት መፈፀማቸውን በቃል ተናግረዋል፡፡ በአከፋፋዮች ላይም የሁለታችንንም ምርቶች ነው መያዝ ያለባችሁ የሚል ግዴታ አስቀምጠዋል፡፡አንዱ የሌላውን አርማና የንግድ ምልክት መጠቀሙንም ባለሥልጣኑ በክሱ ላይ አስፍሯል፡፡ሁለቱ አክሲዮን ማህበራት በጋራ የሥራ አመራር አቅጣጫ ነድፈዋልም ብሏል፡፡የአንዱን አክሲዮን ማህበር ሠራተኛ ወደ ሌላው የማዘዋወር ተግባር ፈፅመዋል ሲልም ባለሥልጣኑ በክሱ ላይ አስፍሯል፡፡ እነዚህ ተግባሮች በሁለቱ አክሲዮን ማህበራት መካከል ውህደት ወይም መቀላቀል መፈጠሩን የሚያረጋግጡ ናቸው ብሏል፡፡ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግና አምቦ ማዕድን ውሃ አክሲዮን ማህበራት በቃል ተዋህደናል ብላችኋል ተብሎ የተነገረው ስህተት ነው፣ ብንል እንኳ ውህደት የሚፈፀመው ብዙ ሂደት አልፎ በሰነድ ነው እንጂ በቃል አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አከፋፋዮች የሁለታችንንም ምርቶች እንዲይዙ ግዴታ አስቀምጣችኋል መባላችንም ስህተት ነው ሲሉም መልሰዋል፡፡አንዱ የሌላውን አርማ ተጠቅሟል በሚል የቀረበው ክስም ትክክል እንዳልሆነ በመቃወሚያቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ በድርጅቶች መካከል ሰራተኛ መዋዋስ በኢትዮጵያ የተለመደ አሰራር መሆኑን በመጥቀስ ይህንን የሚከለክል ህግ የለም ሲሉም ተከራክረዋል፡፡በአጠቃላይ በሁለቱ አክሲዮን ማህበራት መካከል የተፈጠረ ውህደት የለም፤ ይህንን የሚያሣይ ማስረጃም በከሣሾቹ በኩል አልቀረበም ብለዋል፡፡ጉዳዩን እያየ ያለው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን የዳኝነት ችሎትን ብይን ለመስጠት ለነሐሴ 17፣2009 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡ ንጋቱ ረጋሳ
    0 Comments 0 Shares
  • በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ

    በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ፡፡ከአንድ ዙር ቅበላው እግድ በተጨማሪ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሰምተናል፡፡የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ፍሬው ተሻለ ለሸገር እንደተናገሩት በአዲስ አበባ 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡

    ተቋማቱ የሚሰጡትን የስልጠና አሰጣጥ ለመገምገም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የማሰልጠኛ ተቋማት ህብረትና የሚገመገሙ ማሰልጠኛ ተቋማት ተወካይ በሚገኙበት ግምገማ ሲካሄድ መክረሙን ነግረውናል፡፡በ66 የአሽከርካሪ ተቋማት ላይ በተደረገው ግምገማም 18ቱ ያለባቸውን ችግሮች እስካስተካከሉ ድረስ የአንድ ዙር ቅበላ እግድና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

    ሌሎች አራት ተቋማት ደግሞ የሁለት ዙር ቅበላ እንዳያካሄዱና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ፍሬው ተሻለ ነግረውናል፡፡የአንድና የሁለት ዙር ቅበላ እገዳው በየሥልጠና መስኩ እንደሚለያይም ነግረውናል፡፡ግምገማ ከተደረገላቸው ውስጥ 13ቱ ተቋማት ከአነስተኛ ጉድለት ውጪ ጥሩ ናችሁ ተብለዋል፡፡17 ተቋማት ደግሞ የመጀመሪያ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አቶ ፍሬው ነግረውናል፡፡

    በተደረገው ግምገማ ለጊዜው የተዘጋ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም የለም ያሉት አቶ ፍሬው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋማት ጉድለታቸውን ካላስተካከሉ ወደ መዝጋት እርምጃ ይገባል ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ባሉት 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተደረገው ግምገማ የ4 ወር ጊዜ የፈጀ መሆኑንም አቶ ፍሬው ተሻለ ተናግረዋል፡፡

    ንጋቱ ሙሉ
    በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ፡፡ከአንድ ዙር ቅበላው እግድ በተጨማሪ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሰምተናል፡፡የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ፍሬው ተሻለ ለሸገር እንደተናገሩት በአዲስ አበባ 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ተቋማቱ የሚሰጡትን የስልጠና አሰጣጥ ለመገምገም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የማሰልጠኛ ተቋማት ህብረትና የሚገመገሙ ማሰልጠኛ ተቋማት ተወካይ በሚገኙበት ግምገማ ሲካሄድ መክረሙን ነግረውናል፡፡በ66 የአሽከርካሪ ተቋማት ላይ በተደረገው ግምገማም 18ቱ ያለባቸውን ችግሮች እስካስተካከሉ ድረስ የአንድ ዙር ቅበላ እግድና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሌሎች አራት ተቋማት ደግሞ የሁለት ዙር ቅበላ እንዳያካሄዱና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ፍሬው ተሻለ ነግረውናል፡፡የአንድና የሁለት ዙር ቅበላ እገዳው በየሥልጠና መስኩ እንደሚለያይም ነግረውናል፡፡ግምገማ ከተደረገላቸው ውስጥ 13ቱ ተቋማት ከአነስተኛ ጉድለት ውጪ ጥሩ ናችሁ ተብለዋል፡፡17 ተቋማት ደግሞ የመጀመሪያ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አቶ ፍሬው ነግረውናል፡፡ በተደረገው ግምገማ ለጊዜው የተዘጋ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም የለም ያሉት አቶ ፍሬው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋማት ጉድለታቸውን ካላስተካከሉ ወደ መዝጋት እርምጃ ይገባል ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ባሉት 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተደረገው ግምገማ የ4 ወር ጊዜ የፈጀ መሆኑንም አቶ ፍሬው ተሻለ ተናግረዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ
    0 Comments 0 Shares
  • ሐምሌ 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን

    Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

    የኮሪያ አለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የልብ ታማሚ ህፃናት ህክምና ሊያደርጉ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
    በአቃቂ የሚገኘው ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጭ ሆነ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
    በቅርቡ ከአደጋ መዝገብ በተፋቀው በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የብርቅዬ የዱር እንስሣት ብዛቱ እየጨመረ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)
    በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከተሰማሩ ተቋራጮች 7ቱ ውላቸው መቋረጡ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
    በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረው ተከሣሽ የፖሊስ አባል በእሥር ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም)
    ለኢትዮጵያ ባለውለታ የውጭ አገር ሰዎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት ሊሰጣቸው ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
    በዚህ አመት ከቆዳና የቆዳ ግብዓቶች የወጭ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው ገቢ የተሳካው 42 በመቶው ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
    ዘንድሮ በእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች 82 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
    ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስጋ፣ የማርና ሰም የእንስሣት መኖና የወተት ምርቶችን ወደ ውጭ ልካ 104 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
    የስዊድን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችና በድህነት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን መደገፊያ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ (ምህረት ስዩም)
    መንግሥት በ2009 በጀት ዓመት የፈፀመው ግዢ ከቀዳሚው ዓመት በግማሽ ያነሰ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
    የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር የታለመ መርሐ-ግብር ይፋ ተደረገ፡፡ (ምሥክር አወል)
    ሐምሌ 20፣2009 የሸገር ወሬዎቻችን Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser. የኮሪያ አለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የልብ ታማሚ ህፃናት ህክምና ሊያደርጉ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም) በአቃቂ የሚገኘው ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጭ ሆነ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ) በቅርቡ ከአደጋ መዝገብ በተፋቀው በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የብርቅዬ የዱር እንስሣት ብዛቱ እየጨመረ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ) በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከተሰማሩ ተቋራጮች 7ቱ ውላቸው መቋረጡ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ) በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረው ተከሣሽ የፖሊስ አባል በእሥር ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም) ለኢትዮጵያ ባለውለታ የውጭ አገር ሰዎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት ሊሰጣቸው ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ) በዚህ አመት ከቆዳና የቆዳ ግብዓቶች የወጭ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው ገቢ የተሳካው 42 በመቶው ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን) ዘንድሮ በእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች 82 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ) ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስጋ፣ የማርና ሰም የእንስሣት መኖና የወተት ምርቶችን ወደ ውጭ ልካ 104 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ) የስዊድን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችና በድህነት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን መደገፊያ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ (ምህረት ስዩም) መንግሥት በ2009 በጀት ዓመት የፈፀመው ግዢ ከቀዳሚው ዓመት በግማሽ ያነሰ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን) የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር የታለመ መርሐ-ግብር ይፋ ተደረገ፡፡ (ምሥክር አወል)
    0 Comments 0 Shares
  • በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ

    በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥዑማይ ወልደገብርኤል ለሸገር ሲናገሩ በአቃቂ ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በመዘጋቱ ሚኒባስ ታክሲዎችና በስፍራው ያሉ ፋብሪካዎች ሰርቪሶች መተላለፊያ አጥተው ስፍራው መጨናነቅ ገጥሞታል ብለዋል፡፡

    በተሰበረው ድልድይ አቅራቢያ ተለዋጭ ድልድይ ለመሥራት የሚመች አይደለም ያሉት አቶ ጥዑማይ ከቶታል በኩል የሚመጡ መኪኖች በኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን አድርገው ወደ ገላን በተቃራኒው የሚመጡ ደግሞ የቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድን በተለዋጭነት ይጠቀሙ ብለዋል፡፡እነዚህ ተለዋጭ መንገዶች ረጅም ቢሆኑም የተሰበረው ድልድይ እስኪጠገን ብቸኛው አማራጭ ይኸው ነው ተብሏል፡፡

    አሮጌውና ትልቁ የአቃቂ ድልድይም መሰነጣጠቅ እየገጠመው ስለሆነ ከ3 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው መኪኖች እንዳይጓጓዙበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ማስጠንቀቁን ነግረናችሁ ነበር፡፡

    ወንድሙ ሀይሉ
    በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥዑማይ ወልደገብርኤል ለሸገር ሲናገሩ በአቃቂ ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በመዘጋቱ ሚኒባስ ታክሲዎችና በስፍራው ያሉ ፋብሪካዎች ሰርቪሶች መተላለፊያ አጥተው ስፍራው መጨናነቅ ገጥሞታል ብለዋል፡፡ በተሰበረው ድልድይ አቅራቢያ ተለዋጭ ድልድይ ለመሥራት የሚመች አይደለም ያሉት አቶ ጥዑማይ ከቶታል በኩል የሚመጡ መኪኖች በኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን አድርገው ወደ ገላን በተቃራኒው የሚመጡ ደግሞ የቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድን በተለዋጭነት ይጠቀሙ ብለዋል፡፡እነዚህ ተለዋጭ መንገዶች ረጅም ቢሆኑም የተሰበረው ድልድይ እስኪጠገን ብቸኛው አማራጭ ይኸው ነው ተብሏል፡፡ አሮጌውና ትልቁ የአቃቂ ድልድይም መሰነጣጠቅ እየገጠመው ስለሆነ ከ3 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው መኪኖች እንዳይጓጓዙበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ማስጠንቀቁን ነግረናችሁ ነበር፡፡ ወንድሙ ሀይሉ
    0 Comments 0 Shares
  • የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ

    የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ከ3 ትውልድ በላይ በማሣለፍ እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ሀገሪቱን ለጠቀሙ ወገኖች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲያገኙ በተወሰነው መሠረት ቤተ-እሥራኤላውያን፣ የራስ-ተፈሪያን እምነት ተከታዮችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች ይህን መብት እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡

    የውጭ ሀገር ዜጎቹ የኢትዮጵያን ፓስፓርት ሲያገኙ ያለምንም የመኖሪያ ፈቃድና ቪዛ እንደልባቸው መመላለስ ይችላሉ፡፡በመዋዕለ-ነዋይ በኩልም ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት ወቅታዊ መግለጫቸው ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው የምህረት አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው ከቅድመ ሁኔታ ጋር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ቤት በአፋጣኝ ካልተመለሱ የተሰጠው የምህረት ጊዜ ሊታጠፍ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ፓስፓርት እንዲያገኙ የፈቀደላቸው ወገኖችን በተመለከተ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብ አዘጋጅቷል መባሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡በሳውዲ አረቢያ የሚገኖሩና ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ አዲስ አበባ ሲደርሱ ከቀይ-መስቀል፣ ከፖሊስ፣ ከአይ.ኦ.ኤም እንደዚሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራውን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን አባላትን ቦሌ አየር ማረፊያ በመውሰድ አሳይቷቸዋል፡፡
    የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ከ3 ትውልድ በላይ በማሣለፍ እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ሀገሪቱን ለጠቀሙ ወገኖች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲያገኙ በተወሰነው መሠረት ቤተ-እሥራኤላውያን፣ የራስ-ተፈሪያን እምነት ተከታዮችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች ይህን መብት እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡ የውጭ ሀገር ዜጎቹ የኢትዮጵያን ፓስፓርት ሲያገኙ ያለምንም የመኖሪያ ፈቃድና ቪዛ እንደልባቸው መመላለስ ይችላሉ፡፡በመዋዕለ-ነዋይ በኩልም ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት ወቅታዊ መግለጫቸው ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው የምህረት አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው ከቅድመ ሁኔታ ጋር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ቤት በአፋጣኝ ካልተመለሱ የተሰጠው የምህረት ጊዜ ሊታጠፍ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ፓስፓርት እንዲያገኙ የፈቀደላቸው ወገኖችን በተመለከተ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብ አዘጋጅቷል መባሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡በሳውዲ አረቢያ የሚገኖሩና ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ አዲስ አበባ ሲደርሱ ከቀይ-መስቀል፣ ከፖሊስ፣ ከአይ.ኦ.ኤም እንደዚሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራውን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን አባላትን ቦሌ አየር ማረፊያ በመውሰድ አሳይቷቸዋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • አሸናፊ በቀለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የመልቀቅያ ደብዳቤ አስገባ፡፡ | ፌደሬሽኑ በበኩሉ አልደረሰኝም እያለ ነው፡፡ መንስኤው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ የሁሉአዲስ ምንጮች እንዳረጋገጡት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን...
    አሸናፊ በቀለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የመልቀቅያ ደብዳቤ አስገባ፡፡ | ፌደሬሽኑ በበኩሉ አልደረሰኝም እያለ ነው፡፡ መንስኤው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ የሁሉአዲስ ምንጮች እንዳረጋገጡት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን...
    0 Comments 0 Shares
  • ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተዎች ኤጄንሲ የ12ኛ እና 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን አስታውቋል። ኤጀንሲው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት...
    ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተዎች ኤጄንሲ የ12ኛ እና 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን አስታውቋል። ኤጀንሲው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት...
    0 Comments 0 Shares
  • ነገና ከነገ ወዲያ ቡናና ሌጦ እየሸጡ መቀጠል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል - ‹ማግኖሊያ› የሚለውን ብራንድ ወደ ውጭ ይዘን የመውጣት ዕቅድ አለን - ባንኮች ማበረታታት ያለባቸው አገር በቀል...
    ነገና ከነገ ወዲያ ቡናና ሌጦ እየሸጡ መቀጠል አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል - ‹ማግኖሊያ› የሚለውን ብራንድ ወደ ውጭ ይዘን የመውጣት ዕቅድ አለን - ባንኮች ማበረታታት ያለባቸው አገር በቀል...
    0 Comments 0 Shares