• 0 Comments 0 Shares
  • ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡
    ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡

    ጊዜው ቢያልፍና የሳውዲ መንግሥት ዜጎችን በግዴታ ወደ መመለስ ተግባር ቢገባ በሚል እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች መኖራቸውንም አመልክቷል፡፡

    የሳውዲ አረቢያ የውጭ ዜጎች ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠችው የጊዜ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር ተራዝሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎች እድሉን እንዲጠቀሙ፣ ጥሪ ያቀረበውም ይሄንኑ መነሻ በማድረግ ነው፡፡

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ያብራራሉ፡፡

    https://amharic.voanews.com/z/3167
    ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡ ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡ ጊዜው ቢያልፍና የሳውዲ መንግሥት ዜጎችን በግዴታ ወደ መመለስ ተግባር ቢገባ በሚል እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች መኖራቸውንም አመልክቷል፡፡ የሳውዲ አረቢያ የውጭ ዜጎች ሀገሯን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠችው የጊዜ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ወር ተራዝሟል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎች እድሉን እንዲጠቀሙ፣ ጥሪ ያቀረበውም ይሄንኑ መነሻ በማድረግ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ያብራራሉ፡፡ https://amharic.voanews.com/z/3167
    0 Comments 0 Shares
  • WWW.FANABC.COM
    FBC - በለንደን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ተሸኙ
    አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 24፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በለንደን በሚካሄደው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት በአራራት ሆቴል ሽኝት ተደርጎለታል። በስነ ስርዓቱ ላይ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚ...
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

    አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 16 ዓ.ም ከአባታቸው ኤጀርሳ በዳኔ እና ከእናታቸው ዮንዢ ወርቅ በለጤ ተወለዱ።

    በ14 አመታቸውም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

    ከዚያም በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር በመቀጠር በተዋናይት፥ የተለያዩ ተውኔቶችን ተጫውተዋል።

    በወቅቱም የሴት ተዋናዮች ባለመኖራቸው የሴት ገጸ ባህሪ ተላብሰው ይጫወቱ ነበር።

    የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆኑት አርቲስት ተስፋዬ መድረክ መሪ፣ ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ ትርኢት አቅራቢ፣ ድምፃዊ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲና ተረት ነጋሪ ነበሩ።

    በገና፣ ክራር፣ መሰንቆ፣ አኮርድዮንና ትራምፔት ከሚጫወቷቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

    በድምጻዊነት ደግሞ “ዓለም እንደምን ነሽ ደህና ሰነበትሽ ወይ” እና “ፀሃይ” የተሰኙ ዘፈኖቻቸውን አድርሰዋል።

    ከአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ በኋላም በብሄራዊ ቲያትር አገልግለዋል።

    ሀ ሁ በስድስት ወር፣ ኤዲፐስ ንጉስ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ ዳዊትና ኦርዮን፣ ኦቴሎ፣ አስቀያሚዋ ልጃገረድ እና ስነ ስቅለት ደግሞ አባባ ተስፋዬ የተወኑባቸው ተውኔቶች ናቸው።

    ብጥልህሳ፣ ነው ለካ እና ጠላ ሻጯ የተሰኙ ተውኔቶችን ደግሞ በድርሰት አቅርበዋል።

    ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የልጆች የተረት መጽሃፍትን ጽፈዋል።

    አርቲስት ተስፋዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ድርጅት ውስጥ፥ የልጆች ጊዜ የሚል ፕሮግራም በመቅረጽ ለልጆች በሚጠቅም መልኩ አባታዊ ምክራቸውን ለልጆች ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

    በዚህም አባባ ተስፋዬ የሚል መጠሪያን ማግኘት ችለዋል፤ ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስም ተወዳጅ ዝግጅታቸውን ከአባታዊ ምክራቸው ጋር አድርሰዋል።

    ፕሮግራማቸውን ሲጀምሩ “ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች” የሚለው አባባላቸው በበርካቶች ዘንድ የሚታወስና የማይረሳ ነው።

    አባባ ተስፋዬ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሳምንቱ መጨረሻ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክብር ዶክትሬት አግኝተው ነበር።

    አባባ ተስፋዬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው በተወለዱ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
    አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 16 ዓ.ም ከአባታቸው ኤጀርሳ በዳኔ እና ከእናታቸው ዮንዢ ወርቅ በለጤ ተወለዱ። በ14 አመታቸውም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር በመቀጠር በተዋናይት፥ የተለያዩ ተውኔቶችን ተጫውተዋል። በወቅቱም የሴት ተዋናዮች ባለመኖራቸው የሴት ገጸ ባህሪ ተላብሰው ይጫወቱ ነበር። የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆኑት አርቲስት ተስፋዬ መድረክ መሪ፣ ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ ትርኢት አቅራቢ፣ ድምፃዊ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲና ተረት ነጋሪ ነበሩ። በገና፣ ክራር፣ መሰንቆ፣ አኮርድዮንና ትራምፔት ከሚጫወቷቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ይጠቀሳሉ። በድምጻዊነት ደግሞ “ዓለም እንደምን ነሽ ደህና ሰነበትሽ ወይ” እና “ፀሃይ” የተሰኙ ዘፈኖቻቸውን አድርሰዋል። ከአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ በኋላም በብሄራዊ ቲያትር አገልግለዋል። ሀ ሁ በስድስት ወር፣ ኤዲፐስ ንጉስ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ ዳዊትና ኦርዮን፣ ኦቴሎ፣ አስቀያሚዋ ልጃገረድ እና ስነ ስቅለት ደግሞ አባባ ተስፋዬ የተወኑባቸው ተውኔቶች ናቸው። ብጥልህሳ፣ ነው ለካ እና ጠላ ሻጯ የተሰኙ ተውኔቶችን ደግሞ በድርሰት አቅርበዋል። ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የልጆች የተረት መጽሃፍትን ጽፈዋል። አርቲስት ተስፋዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ድርጅት ውስጥ፥ የልጆች ጊዜ የሚል ፕሮግራም በመቅረጽ ለልጆች በሚጠቅም መልኩ አባታዊ ምክራቸውን ለልጆች ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህም አባባ ተስፋዬ የሚል መጠሪያን ማግኘት ችለዋል፤ ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስም ተወዳጅ ዝግጅታቸውን ከአባታዊ ምክራቸው ጋር አድርሰዋል። ፕሮግራማቸውን ሲጀምሩ “ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች” የሚለው አባባላቸው በበርካቶች ዘንድ የሚታወስና የማይረሳ ነው። አባባ ተስፋዬ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሳምንቱ መጨረሻ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክብር ዶክትሬት አግኝተው ነበር። አባባ ተስፋዬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው በተወለዱ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
    WWW.FANABC.COM
    FBC - አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
    አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 1...
    0 Comments 0 Shares
  • WWW.FANABC.COM
    FBC - አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
    አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 1...
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው

    “በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው ፤ በዚህ ፍጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድን ህንፃ ገንብቶ ሲጠናቀቅ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፤ እኛም ተሳስተን ግን እንጨርሳለን ብለናችሁ ነበር…”የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 ቤቶች በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጣቢዎች ይሰጣሉ መባሉ በስህተት የተናገርነው ነው አለ…

    እየተገነቡ ነው የተባሉት ከ38 ሺ በላይ የ40/60 ቤቶች መቼ እንደሚጠናቀቁ አይታወቅም፡፡መስተዳደሩ ይህን ያለው ዛሬ በ40/60 ቤቶች የ2009 ዓ.ም አፈፃፀምና የ2010 ዓ.ም የሥራ ዕድቅ ላይ ከኮንትራክተሮች፣ ከአማካሪዎችና ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ባደረገ ጊዜ ነው፡፡የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሣቢና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 መኖሪያ ቤቶች ከውል ውጭ ሰፋፊ ሆነው በስህተት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

    በዚህም ሳቢያ ባለ1 መኝታ ቤት የሚባለው ቀርቶ ያልታሰበው ባለ 4 መኝታ ቤት ተገንብቶ እጣ ወጥቶበታል ነው ያሉት፡፡ይሁን እንጂ ቤቶቹ አንዳንድ ክፍል የተጨመረባቸው ለሠራተኛ ተብሎ የተገነቡት ክፍሎች ተጨምረው ነውና ይህ አግባብ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ምክትል ከንቲባው የቤቶቹ ስፋት ጋር አያይዘው ብቻ መልስ ሰጥተዋል፡፡ይህ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥምና ወደፊትም በዲዛይን ለውጥ ሳቢያ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳ ቤቶቹ በህዝብ ገንዘብ ጭምር ቢገነቡም ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ አንጠይቅም ብለዋል፡፡
    በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው “በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው ፤ በዚህ ፍጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድን ህንፃ ገንብቶ ሲጠናቀቅ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፤ እኛም ተሳስተን ግን እንጨርሳለን ብለናችሁ ነበር…”የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 ቤቶች በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጣቢዎች ይሰጣሉ መባሉ በስህተት የተናገርነው ነው አለ… እየተገነቡ ነው የተባሉት ከ38 ሺ በላይ የ40/60 ቤቶች መቼ እንደሚጠናቀቁ አይታወቅም፡፡መስተዳደሩ ይህን ያለው ዛሬ በ40/60 ቤቶች የ2009 ዓ.ም አፈፃፀምና የ2010 ዓ.ም የሥራ ዕድቅ ላይ ከኮንትራክተሮች፣ ከአማካሪዎችና ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ባደረገ ጊዜ ነው፡፡የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሣቢና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 መኖሪያ ቤቶች ከውል ውጭ ሰፋፊ ሆነው በስህተት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ባለ1 መኝታ ቤት የሚባለው ቀርቶ ያልታሰበው ባለ 4 መኝታ ቤት ተገንብቶ እጣ ወጥቶበታል ነው ያሉት፡፡ይሁን እንጂ ቤቶቹ አንዳንድ ክፍል የተጨመረባቸው ለሠራተኛ ተብሎ የተገነቡት ክፍሎች ተጨምረው ነውና ይህ አግባብ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ምክትል ከንቲባው የቤቶቹ ስፋት ጋር አያይዘው ብቻ መልስ ሰጥተዋል፡፡ይህ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥምና ወደፊትም በዲዛይን ለውጥ ሳቢያ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳ ቤቶቹ በህዝብ ገንዘብ ጭምር ቢገነቡም ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ አንጠይቅም ብለዋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ለልማት የሚነሱ ኤርትራውያን እንዴት ምትክ ቦታና ካሣ ይሰጣቸው የሚለው እስካሁን ውሣኔ አላገኘም ተባለ

    በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ለልማት የሚነሱ ኤርትራውያን እንዴት ምትክ ቦታና ካሣ ይሰጣቸው የሚለው እስካሁን ውሣኔ አላገኘም ተባለ፡፡ስለ ጉዳዩ ጥናት ተደርጎ ለመሬት ማኔጅመንት መቅረቡንም የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡ለሀገር ደህንነት ሥጋት አይደሉም የተባሉና ከኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በፊት ሀብት ንብረት አፍርተው በአዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን በከተማዋ ይኖራሉ፡፡

    በመልሶ ማልማት ክልል ውስጥ ቤት ያላቸው ኤርትራውያን እንዴት ካሣና ምትክ ቦታ ማግኘት እንዳለባቸው ራሱን የቻለ ሕግ ስለሌለ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ሲቸገር መቆየቱን ሰምተናል፡፡ለጉዳዩ እልባት ለመስጠትም ከፍትህ ቢሮ ጋር ጥናት አካሂዶ ለመሬት ማኔጅመንት ማቅረቡን የኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ብርሃኑ ለሸገር ተናግረዋል፡፡እስካሁን ግን ውሣኔ ያላገኘ ጉዳይ እንደሆነም ነግረውናል፡፡

    ለመልሶ ማልማት ቤቶች ሲፈርሱ በየክፍለ ከተማው አንድም፣ ሁለትም የኤርትራውያን ጉዳይ ያጋጥመናል ያሉት አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም ቤታቸው የፈረሰባቸው ምትክ ቦታና ካሣ አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡ይሁንና የቤታቸውን ሁኔታና የቦታ ልኬታቸውን ሙሉ መረጃ ይዘናል በጥናቱ መሠረትም የከተማዋ ካቢኔ በሚያሣልፈው የውሣኔ ኃሣብ መሠረት ይስተናገዳሉ ብለዋል፡፡አሁን ግን ለጊዜው ቤታቸው ያልፈረሰባቸው ኤርትራውያን አካባቢው ለመልሶ ማልማት ቢፈለግም ጉዳዩ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ እንዳይፈርስባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

    ትዕግስት ዘሪሁን
    በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ለልማት የሚነሱ ኤርትራውያን እንዴት ምትክ ቦታና ካሣ ይሰጣቸው የሚለው እስካሁን ውሣኔ አላገኘም ተባለ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና ለልማት የሚነሱ ኤርትራውያን እንዴት ምትክ ቦታና ካሣ ይሰጣቸው የሚለው እስካሁን ውሣኔ አላገኘም ተባለ፡፡ስለ ጉዳዩ ጥናት ተደርጎ ለመሬት ማኔጅመንት መቅረቡንም የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ለሸገር ተናግሯል፡፡ለሀገር ደህንነት ሥጋት አይደሉም የተባሉና ከኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በፊት ሀብት ንብረት አፍርተው በአዲስ አበባ ይኖሩ የነበሩ ኤርትራውያን በከተማዋ ይኖራሉ፡፡ በመልሶ ማልማት ክልል ውስጥ ቤት ያላቸው ኤርትራውያን እንዴት ካሣና ምትክ ቦታ ማግኘት እንዳለባቸው ራሱን የቻለ ሕግ ስለሌለ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ሲቸገር መቆየቱን ሰምተናል፡፡ለጉዳዩ እልባት ለመስጠትም ከፍትህ ቢሮ ጋር ጥናት አካሂዶ ለመሬት ማኔጅመንት ማቅረቡን የኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ብርሃኑ ለሸገር ተናግረዋል፡፡እስካሁን ግን ውሣኔ ያላገኘ ጉዳይ እንደሆነም ነግረውናል፡፡ ለመልሶ ማልማት ቤቶች ሲፈርሱ በየክፍለ ከተማው አንድም፣ ሁለትም የኤርትራውያን ጉዳይ ያጋጥመናል ያሉት አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም ቤታቸው የፈረሰባቸው ምትክ ቦታና ካሣ አልተሰጣቸውም ብለዋል፡፡ይሁንና የቤታቸውን ሁኔታና የቦታ ልኬታቸውን ሙሉ መረጃ ይዘናል በጥናቱ መሠረትም የከተማዋ ካቢኔ በሚያሣልፈው የውሣኔ ኃሣብ መሠረት ይስተናገዳሉ ብለዋል፡፡አሁን ግን ለጊዜው ቤታቸው ያልፈረሰባቸው ኤርትራውያን አካባቢው ለመልሶ ማልማት ቢፈለግም ጉዳዩ ውሣኔ እስኪያገኝ ድረስ እንዳይፈርስባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን
    0 Comments 0 Shares