• የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ካፒታል እንዲስተካከል ወሰነ
    -
    የካፒታል ማስተካከያው የተደረገው ለኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊል ኮርፖሬሽን፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ አሰላ ብቅል ፋብሪካና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ነው
    የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ካፒታል እንዲስተካከል ወሰነ - የካፒታል ማስተካከያው የተደረገው ለኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮፊል ኮርፖሬሽን፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ አሰላ ብቅል ፋብሪካና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ነው
    0 Comments 0 Shares
  • ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እንቅስቃሴ መጠንሰስ እና መጎልበት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫዎቱት አቶ ኃብተ ሥላሴ ታፈሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትናንት በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡
    ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እንቅስቃሴ መጠንሰስ እና መጎልበት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫዎቱት አቶ ኃብተ ሥላሴ ታፈሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትናንት በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • ኢትዮጵያን በመወከል እንዲሰሩ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት
    ይፋ ሆኑ
    አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ
    የሾሟቸው አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ይፋ ሆኑ።
    በዚህም መሰረት፡-
    1. አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን - አሜሪካ ዋሽንግተን
    2. አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ - ቻይና ቤጂንግ
    3. አምባሳደር አስቴር ማሞ - ካናዳ ኦታዋ
    4. አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም - ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ
    5. አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና - ስዊድን ስቶኮልም
    6. አምባሳደር ተበጀ በርኼ - የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አቡ ዳቢ
    7. አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ - ኳታር ዶሃ
    8. አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ - ኢንዶኔዥያ ጃካርታ
    9. አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ - ሩዋንዳ ኪጋሊ
    10. አምባሳደር ዓሊ ሱሌይማን - ፈረንሳይ ፓሪስ
    11. አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ - ሱዳን ካርቱም
    12. አምባሳደር አቶ እውነቱ ብላታ - ቤልጂዬም ብራስልስ እንዲሰሩ
    መመደባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
    ኢትዮጵያን በመወከል እንዲሰሩ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ይፋ ሆኑ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የሾሟቸው አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ይፋ ሆኑ። በዚህም መሰረት፡- 1. አምባሳደር ካሳ ተክለ ብርሃን - አሜሪካ ዋሽንግተን 2. አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ - ቻይና ቤጂንግ 3. አምባሳደር አስቴር ማሞ - ካናዳ ኦታዋ 4. አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም - ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ 5. አምባሳደር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና - ስዊድን ስቶኮልም 6. አምባሳደር ተበጀ በርኼ - የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አቡ ዳቢ 7. አምባሳደር መታሰቢያ ታደሰ - ኳታር ዶሃ 8. አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ - ኢንዶኔዥያ ጃካርታ 9. አምባሳደር ሉሊት ዘውዴ - ሩዋንዳ ኪጋሊ 10. አምባሳደር ዓሊ ሱሌይማን - ፈረንሳይ ፓሪስ 11. አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ - ሱዳን ካርቱም 12. አምባሳደር አቶ እውነቱ ብላታ - ቤልጂዬም ብራስልስ እንዲሰሩ መመደባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
    0 Comments 0 Shares

  • በብዛት የተለመደው እንድ ሰው በወጣትነት የአድሜ ክልል ወስጥ ሲገባ ትዳር ይመሰርታል።
    አልፎ አልፎ ግን በስራ ምክንያትም ይሁን በሌሎች የኑሮ ምክንያቶች አንዳንዶች እድሜያቸው ገፋ ካለ በኋላ በስተርጅና ትዳር ሲመሰትሩም ያጋጥማል።
    በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ግን የተከሰተው ከዚህም ለየት የሚል ሲሆን፥ የ107 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት አዛውንት ባሳለፍነው እሁድ ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ነው የተሰማው።
    ሙሽራው አዛውንት ሃጂ አብዱልቃድር ዴከማ ዲዶ ይባላሉ፤ የሻሸመኔ ወረዳ የዳኒሳ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፥ በ1902 ዓ.ም እንደተወለዱም ይናገራሉ።
    የተለያዩ ሀይማኖታዊ ትምህርት ላይ ከቆዩ በኋላ የመጀመሪያ ባለቤታቸውን በ1942 ዓ.ም ማግባታቸውን የሚናገሩ ሲሆን፥ ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ጋርም ዘጠኝ ልጆችን አፍርተዋል።
    ሀጂ አብዱልቃድር ሁተኛ ባለቤታቸውንም በ1956 አግበት አርበው መኖር እንደጀመሩም ይናገራሉ።
    ከሁለቱ የትዳር አጋሮቻቸው በርካታ ልጆችን መውለዳቸውን የሚናገሩት ሀጂ አብዲልቃድር፥ በአሁኑ ጊዜ 9 ሴት እና 10 ወንድ ልጆቻቸው በህይወት እንዳሉም ተናግረዋል።
    በአሁኑ ጊዜም የበኩር ልጃቸው የ60 ዓመት አዛውንት ነው።

    ሀጂ አብዱልቃድር ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ እስካሁን 108 የቤተሰብ አባላት አፍርተዋል።

    ታዲያ ሁለተኛዋ ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ሀጂ አብዱልቃድር የመጀመሪያ ባለቤታቸውም ድካም ስለተጫጫናቸው የሚንከባከበኝ አጣሁ ይላሉ።

    የሚንከባከባቸው ከማጣት እና አዲስ ሚስት ለማግባት ካላቸው ፍላጎት የተነሳም ሶስተኛ ሚስት ማግባት እንዳላቸው ከውሳኔ የደረሱት ሀጂ አብዱልቃድር፥ ይህንን ሀሳባቸውንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመወያየት ተቀባይነት ያገኝላቸዋል።

    በአካባቢው የጋብቻ ባህል መሰረትም ለጋብቻ የፈለጓት ሴት ቤተስብ ጋር ሽማግሌ ልከው ያስጠየቁ ሲሆን፥ ጥያቄያቸውም እሺ የሚል መልስ ያገኛል።

    በዚህም መሰረት የ107 ዓመቱ አዛውንት ሀጂ አብዱልቃድር ባሳለፍነው እሁድ ነሃሴ 7 2009 ፉሮ ጉዬ የተባለች የ33 ዓመት ሴት ዘመድ አዝማድ በተገኘበት ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ተነግሯል።

    “በዚህ እድሜዬ በሰርግ ማግባቴ በጣም አስደስቶኛል” የሚሉት ሀጂ አብዱልቃድር፥ 3ኛ ባለቤታቸውን በልዩ አይን እንደሚያይዋት እና “የእድሜ ልዩነት እንዳለው ሰው ሳይሆን እንደማንኛወም ሰው አብራኝ እድትኖር እፈልጋለው” ብለዋል

    ፈጣሪ ከፈቀደም ከሶስተኛ ባለቤታቸው ጋር ልጆች የመውለድ ሀሳብ እንዳላቸውም ሀጂ አብዱልቃድር ተናግረዋል።

    ከዚህ በተጨማሪም በፍቅር እና በደስታ አብረዋት መኖር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል።

    በቢቂላ ቱፋ
    በብዛት የተለመደው እንድ ሰው በወጣትነት የአድሜ ክልል ወስጥ ሲገባ ትዳር ይመሰርታል። አልፎ አልፎ ግን በስራ ምክንያትም ይሁን በሌሎች የኑሮ ምክንያቶች አንዳንዶች እድሜያቸው ገፋ ካለ በኋላ በስተርጅና ትዳር ሲመሰትሩም ያጋጥማል። በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ግን የተከሰተው ከዚህም ለየት የሚል ሲሆን፥ የ107 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት አዛውንት ባሳለፍነው እሁድ ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ነው የተሰማው። ሙሽራው አዛውንት ሃጂ አብዱልቃድር ዴከማ ዲዶ ይባላሉ፤ የሻሸመኔ ወረዳ የዳኒሳ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፥ በ1902 ዓ.ም እንደተወለዱም ይናገራሉ። የተለያዩ ሀይማኖታዊ ትምህርት ላይ ከቆዩ በኋላ የመጀመሪያ ባለቤታቸውን በ1942 ዓ.ም ማግባታቸውን የሚናገሩ ሲሆን፥ ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ጋርም ዘጠኝ ልጆችን አፍርተዋል። ሀጂ አብዱልቃድር ሁተኛ ባለቤታቸውንም በ1956 አግበት አርበው መኖር እንደጀመሩም ይናገራሉ። ከሁለቱ የትዳር አጋሮቻቸው በርካታ ልጆችን መውለዳቸውን የሚናገሩት ሀጂ አብዲልቃድር፥ በአሁኑ ጊዜ 9 ሴት እና 10 ወንድ ልጆቻቸው በህይወት እንዳሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ጊዜም የበኩር ልጃቸው የ60 ዓመት አዛውንት ነው። ሀጂ አብዱልቃድር ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ እስካሁን 108 የቤተሰብ አባላት አፍርተዋል። ታዲያ ሁለተኛዋ ባለቤታቸውን በሞት ያጡት ሀጂ አብዱልቃድር የመጀመሪያ ባለቤታቸውም ድካም ስለተጫጫናቸው የሚንከባከበኝ አጣሁ ይላሉ። የሚንከባከባቸው ከማጣት እና አዲስ ሚስት ለማግባት ካላቸው ፍላጎት የተነሳም ሶስተኛ ሚስት ማግባት እንዳላቸው ከውሳኔ የደረሱት ሀጂ አብዱልቃድር፥ ይህንን ሀሳባቸውንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመወያየት ተቀባይነት ያገኝላቸዋል። በአካባቢው የጋብቻ ባህል መሰረትም ለጋብቻ የፈለጓት ሴት ቤተስብ ጋር ሽማግሌ ልከው ያስጠየቁ ሲሆን፥ ጥያቄያቸውም እሺ የሚል መልስ ያገኛል። በዚህም መሰረት የ107 ዓመቱ አዛውንት ሀጂ አብዱልቃድር ባሳለፍነው እሁድ ነሃሴ 7 2009 ፉሮ ጉዬ የተባለች የ33 ዓመት ሴት ዘመድ አዝማድ በተገኘበት ድል ባለ ሰርግ ማግባታቸው ተነግሯል። “በዚህ እድሜዬ በሰርግ ማግባቴ በጣም አስደስቶኛል” የሚሉት ሀጂ አብዱልቃድር፥ 3ኛ ባለቤታቸውን በልዩ አይን እንደሚያይዋት እና “የእድሜ ልዩነት እንዳለው ሰው ሳይሆን እንደማንኛወም ሰው አብራኝ እድትኖር እፈልጋለው” ብለዋል ፈጣሪ ከፈቀደም ከሶስተኛ ባለቤታቸው ጋር ልጆች የመውለድ ሀሳብ እንዳላቸውም ሀጂ አብዱልቃድር ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በፍቅር እና በደስታ አብረዋት መኖር እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። በቢቂላ ቱፋ
    0 Comments 0 Shares
  • Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

    ያገሬ ልጆች፤ (የኢትዮጵያ ጀግኖች)
    ♦♦♦
    በዘንድሮ የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ መመዘኛ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ዝምተኛ ጀግኖች
    ♦♦♦
    1. ዮፍታሄ ባይሳ ~ 633 ~ ከአዲስ አበባ
    2. ዮሴፍ እናውጋው ~ 626 ~ ከደብረማርቆስ
    3. ዮናታን ወሰንየለህ ~ 623 ~ ከደሴ
    ♦♦♦
    የአሜሪካ የትምህርት ተቋም በዓለም ባለብሩህ አዕምሮ 1.6 ሚሊየን ተማሪዎችን አወዳድሯል፡፡ ከነዚህ ተወዳዳሪዎች መካከል ዮሴፍ እናውጋው ነው፡፡
    በአንድ ሰዓት ውስጥ በሚሰጠው የልዕለ አዕምሮ መለኪያ (IQ) ፈተና ሂሳብ ከመቶው መቶ ፣ፊዚክስ ከመቶው 97%፣ አፕቲትዮድ ከ1600 ጥያቄ 1400 ውን በመመለስ ከዓለም ባለልዮ አዕምሮ ወጣቶች የመጀመሪያው ሆኗል፡፡
    ባለ ልዮ አዕምሮው ዮሴፍ እናውጋው፣ አራት የአሜሪካ ግዙፍ ዮኒቨርስቲዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥተውታል።
    ሀርቫርድ፣ ኮሎምቢያ፣ ፕሪንስ እና በዓለም በምህድስናው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነው MIT ዮኒቨርስቲዎች ናቸው፡፡
    ተማሪ ዮሴፍ እናውጋው ከቀረቡት አራት ወርቃማ አማራጮች መካከል MIT ዮኒቨርስቲን መርጧል፡፡
    ተማሪ ዮሴፍ አሁን በረራውን ወደ አሜሪካ አድርጓል፡፡
    Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) ያገሬ ልጆች፤ (የኢትዮጵያ ጀግኖች) ♦♦♦ በዘንድሮ የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ መመዘኛ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ዝምተኛ ጀግኖች ♦♦♦ 1. ዮፍታሄ ባይሳ ~ 633 ~ ከአዲስ አበባ 2. ዮሴፍ እናውጋው ~ 626 ~ ከደብረማርቆስ 3. ዮናታን ወሰንየለህ ~ 623 ~ ከደሴ ♦♦♦ የአሜሪካ የትምህርት ተቋም በዓለም ባለብሩህ አዕምሮ 1.6 ሚሊየን ተማሪዎችን አወዳድሯል፡፡ ከነዚህ ተወዳዳሪዎች መካከል ዮሴፍ እናውጋው ነው፡፡ በአንድ ሰዓት ውስጥ በሚሰጠው የልዕለ አዕምሮ መለኪያ (IQ) ፈተና ሂሳብ ከመቶው መቶ ፣ፊዚክስ ከመቶው 97%፣ አፕቲትዮድ ከ1600 ጥያቄ 1400 ውን በመመለስ ከዓለም ባለልዮ አዕምሮ ወጣቶች የመጀመሪያው ሆኗል፡፡ ባለ ልዮ አዕምሮው ዮሴፍ እናውጋው፣ አራት የአሜሪካ ግዙፍ ዮኒቨርስቲዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥተውታል። ሀርቫርድ፣ ኮሎምቢያ፣ ፕሪንስ እና በዓለም በምህድስናው ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነው MIT ዮኒቨርስቲዎች ናቸው፡፡ ተማሪ ዮሴፍ እናውጋው ከቀረቡት አራት ወርቃማ አማራጮች መካከል MIT ዮኒቨርስቲን መርጧል፡፡ ተማሪ ዮሴፍ አሁን በረራውን ወደ አሜሪካ አድርጓል፡፡
    Like
    2
    0 Comments 1 Shares
  • በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መቶ ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ መግባታቸውን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለጸ
    -
    በሌላ በኩል በዚሁ በጀት ዓመት ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።
    .
    በኢትዮጵያ ከተሽከርካሪ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑም ተነግሯል ...
    በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መቶ ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ መግባታቸውን የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገለጸ - በሌላ በኩል በዚሁ በጀት ዓመት ከ4 ሺህ 500 በላይ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። . በኢትዮጵያ ከተሽከርካሪ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑም ተነግሯል ...
    0 Comments 0 Shares
  • ጫት በአማራ ክልል ከሳምንታት በፊት ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የአፍሪካ የጥናት ተቋምን እና ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የምርምር ተቋም ባጠናቀረው መረጃ ግማሽ ያህሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ጫት ጋር እንደተላመዱ ገልጧል፡፡
    ከብዙ የዓለም ሀገራት የሚበልጠው መሬትም የጫት ማሳ ሆኗል፡፡በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው አሁን የሀገሪቱ ከአንድ ሚሊየን በላይ መሬት በጫት ተሸፍኗል፡፡ ጫት ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛው የውጭ ምንዛሪ አስገኝ ተክል እንደሆነም ተገልጧል፡፡የጫት ተፈላጊነት እስከበዛ ድረስ ፣ጫት የጤፍ ማሳዎችን ሁሉ መያዙ አይቀርም፡፡
    ጫት እንደ አማራ ክልል!!
    ያማራው ክልል ሰፊ የለም መሬት እና የውሃማ አካላት ባለቤት ነው፡፡በዚህ በግብርና ምርት የሀገሪቱን ከፍተኛውን ምርት ይሸፍናል፡፡ አሁን አሁን አርሶአደሩ ፊቱን ክፉኛ ወደ ጫት ምርት አዙሯል፡፡ የጣና ዳርን ተከትሎ የባህርዳር ዙሪያ፣የደራ ፣የፎገራ ወዘተ አርሶአደሮች ጫትን የጓሮ አትክልታቸውን እየተው እያለሙት ነው፡፡የጎጃም ለምለም መሬቶችም በጫት ተሸፍነዋል፡፡በአዴት የጫት ገበያው ደርቷል፡፡
    በሞጣ የጫት ገበያው ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት፣ጫት በየቦታው እንዳይቃም ተከልክሏል፡፡በምስራቁ የአማራው ክፍል ጫት ሲበዛ ይቃማል፡፡ ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፣ጫት በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር እና በባህርዳር ባልተለመደ ሁኔታ ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ ከክርስትና እና ከእስልምና ሀይማኖት አባቶች ባገኘሁት መረጃ ጫት እንዲቃም የሚደግፍ አንድም የእምነት አስተምህሮ የለም ብለውኛል፡፡
    በእርግጥ ጫት መቃም በዓለም የጤና ድርጅት ከ 1980 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ጎጂ ዕፅ ከተፈረጀ በኋላ የዓለም ገበያ እየተዘጋበት ነው፡፡በሳውዲ ጫት መቃም አደገኛ እፅ የመጠቀም ያህል ያስቀጣል፡፡በአሜሪካ እንደዚሁ፡፡እንግሊዝም ከሶስት ዓመት በፊት ጫት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ ከልክላለች፡፡ የመን፣ጂቡቲ፣ሶማሊያ እና ኬኒያ ጫት በመቃም ይታወቃሉ፡፡ የየመን 90 በመቶ ወንድ ጫት ቃሚ ነው፡፡ጫት ለእነዚህ ሀገራት ውድቀት ሚናው የጎላ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡የመን ለመከልከል ብትሞክርም አልቻለችም፡፡
    የኢትዮጲያ ጫት መዳረሻው ወደነዚህ አካባቢዎች ነው፡፡ግን እነዚህ ሀገራትም ቢሆንም ገባያቸውን ለመዝጋት እየተቃረቡ ስለሆነ የጫት ንግድ በሀገር ውስጥ መገደቡ አይቀርም፡፡ አማራ ክልል ከጫት ገቢ ምን ያህል ያገኛል? የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን እንደሚለው በአማራ ክልል ከሚመረተው ጫት 80% ለሀገር ውስጥ እና ለአካባቢ ፍጆታ ይውላል፡፡20% ብቻ ለውጭ ገበያ ይውላል፡፡ያ ሆኖም መደበኛ የገበያ ስርዓት ስለሌለው ከጫት በዓመት 10 ሚሊየን ብር እንኳ በቅጡ ማግኘት አይችልም፡፡
    በ 2004 ዓ/ም የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ጫት መቃም እንዳይበረታታ በጫት ላይ ተጨማሪ ታክስ 5% (excise tax) እንዲጣል ወስኗል፡፡ ነገር ግን ክልሉ ይህን ተግባራዊ እንኳ ማድረግ አልቻለም ከሰሞኑ ከመሞከሩ በስተቅር እርግጥ ሙከራው ጥሩ ነው፡፡ጫት በክልሉ ቃሚ እንጂ በጥፋቱ ልክ የስራ ዕድል አልፈጠረም፡፡ የጫት ገበያ በዘፈቀደ መሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ጫት ላይ ተጨማሪ ታክሱን ከመተግበር ባለፈ፣ጫት በየቦታው እንዳይሸጥ እገድባለሁ ብሎ በ 2008 ዓ/ም ለአማራ ቴሌቪዝን ተናግሮ ነበር፡፡ግን እስካሁን ያለውን አላደረገም፡፡ጫት በየቦታው ተመርቶ፣በየቦታው እየተሸጠ ነው፡፡
    የክልሉ የግብርና ቢሮ ጫት እንደተስፋፋ ቢገልፅም፣በምን ያህል ሄክታር መሬት ምን ያህል አርሶአደሮች እያመረቱት እንደሆነ የተጠናከረ መረጃ የለውም፡፡ብቻ ጫት በከፍተኛ ሁኔታ ውሃም ስለሚፈልግ የመስኖ ምርትን እየተሻማው ነው፡፡
    ለአባይ ና ጣናም ጫት ስጋት ሆኗል፡፡ በጎንደር ዮኒቨርሲቲ የህክምና መምህር የሆኑት ዶክተር ብርሌው ተሾመ፣ እንደሚሉት ጫት በቅፅበት አነቃቅቶ ለድብርት ስለሚጋብዝ ለአዕምሮ ህመም መነሻ ነው ብለዋል፡፡ለሌሎች ሱሶችም ገፊ ነው፡፡ በአማኑኤል ሆስፒታል ካሉ የአዕምሮ ህሙማን ውስጥ 70% በጫት እና ተያያዥ ደባል ሱሶች እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ጫት በጊዜ ና በገንዘብ ላይ የሚያመጣው ጫናም ቀላል አይደለም፡፡
    በመሆኑም ክልሉ ጫት ላይ የንግድ ስርዓቱን መገደብ፣የሚቃምበትን እና የሚመረትበትን ቦታ መወሰን እስካልቻለ ድረስ ወጣቶች ውሏቸውን ሁሉ ጫት ማሳ ላይ ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ስራ አጥነትን ለመቀነስ፣አማራጭ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን መንግስት ቀጠሮ ሳይሰጥ ሊሰራ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ጫት ተስፋ የመቁረጥ መደበቂያ ሆኖ መዝለቁ አይቀርም፡፡የሀይማኖት አባቶችም ማህበረሰባዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሁኔታው ያስገድዳቸዋል፡፡
    በየሺሀሳብ አበራ
    ጫት በአማራ ክልል ከሳምንታት በፊት ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የአፍሪካ የጥናት ተቋምን እና ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የምርምር ተቋም ባጠናቀረው መረጃ ግማሽ ያህሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ጫት ጋር እንደተላመዱ ገልጧል፡፡ ከብዙ የዓለም ሀገራት የሚበልጠው መሬትም የጫት ማሳ ሆኗል፡፡በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው አሁን የሀገሪቱ ከአንድ ሚሊየን በላይ መሬት በጫት ተሸፍኗል፡፡ ጫት ከቡና ቀጥሎ ሁለተኛው የውጭ ምንዛሪ አስገኝ ተክል እንደሆነም ተገልጧል፡፡የጫት ተፈላጊነት እስከበዛ ድረስ ፣ጫት የጤፍ ማሳዎችን ሁሉ መያዙ አይቀርም፡፡ ጫት እንደ አማራ ክልል!! ያማራው ክልል ሰፊ የለም መሬት እና የውሃማ አካላት ባለቤት ነው፡፡በዚህ በግብርና ምርት የሀገሪቱን ከፍተኛውን ምርት ይሸፍናል፡፡ አሁን አሁን አርሶአደሩ ፊቱን ክፉኛ ወደ ጫት ምርት አዙሯል፡፡ የጣና ዳርን ተከትሎ የባህርዳር ዙሪያ፣የደራ ፣የፎገራ ወዘተ አርሶአደሮች ጫትን የጓሮ አትክልታቸውን እየተው እያለሙት ነው፡፡የጎጃም ለምለም መሬቶችም በጫት ተሸፍነዋል፡፡በአዴት የጫት ገበያው ደርቷል፡፡ በሞጣ የጫት ገበያው ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት፣ጫት በየቦታው እንዳይቃም ተከልክሏል፡፡በምስራቁ የአማራው ክፍል ጫት ሲበዛ ይቃማል፡፡ ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ፣ጫት በአማራ ክልል በተለይም በጎንደር እና በባህርዳር ባልተለመደ ሁኔታ ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ ከክርስትና እና ከእስልምና ሀይማኖት አባቶች ባገኘሁት መረጃ ጫት እንዲቃም የሚደግፍ አንድም የእምነት አስተምህሮ የለም ብለውኛል፡፡ በእርግጥ ጫት መቃም በዓለም የጤና ድርጅት ከ 1980 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ጎጂ ዕፅ ከተፈረጀ በኋላ የዓለም ገበያ እየተዘጋበት ነው፡፡በሳውዲ ጫት መቃም አደገኛ እፅ የመጠቀም ያህል ያስቀጣል፡፡በአሜሪካ እንደዚሁ፡፡እንግሊዝም ከሶስት ዓመት በፊት ጫት ወደ ሀገሯ እንዳይገባ ከልክላለች፡፡ የመን፣ጂቡቲ፣ሶማሊያ እና ኬኒያ ጫት በመቃም ይታወቃሉ፡፡ የየመን 90 በመቶ ወንድ ጫት ቃሚ ነው፡፡ጫት ለእነዚህ ሀገራት ውድቀት ሚናው የጎላ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡የመን ለመከልከል ብትሞክርም አልቻለችም፡፡ የኢትዮጲያ ጫት መዳረሻው ወደነዚህ አካባቢዎች ነው፡፡ግን እነዚህ ሀገራትም ቢሆንም ገባያቸውን ለመዝጋት እየተቃረቡ ስለሆነ የጫት ንግድ በሀገር ውስጥ መገደቡ አይቀርም፡፡ አማራ ክልል ከጫት ገቢ ምን ያህል ያገኛል? የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን እንደሚለው በአማራ ክልል ከሚመረተው ጫት 80% ለሀገር ውስጥ እና ለአካባቢ ፍጆታ ይውላል፡፡20% ብቻ ለውጭ ገበያ ይውላል፡፡ያ ሆኖም መደበኛ የገበያ ስርዓት ስለሌለው ከጫት በዓመት 10 ሚሊየን ብር እንኳ በቅጡ ማግኘት አይችልም፡፡ በ 2004 ዓ/ም የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ጫት መቃም እንዳይበረታታ በጫት ላይ ተጨማሪ ታክስ 5% (excise tax) እንዲጣል ወስኗል፡፡ ነገር ግን ክልሉ ይህን ተግባራዊ እንኳ ማድረግ አልቻለም ከሰሞኑ ከመሞከሩ በስተቅር እርግጥ ሙከራው ጥሩ ነው፡፡ጫት በክልሉ ቃሚ እንጂ በጥፋቱ ልክ የስራ ዕድል አልፈጠረም፡፡ የጫት ገበያ በዘፈቀደ መሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን ጫት ላይ ተጨማሪ ታክሱን ከመተግበር ባለፈ፣ጫት በየቦታው እንዳይሸጥ እገድባለሁ ብሎ በ 2008 ዓ/ም ለአማራ ቴሌቪዝን ተናግሮ ነበር፡፡ግን እስካሁን ያለውን አላደረገም፡፡ጫት በየቦታው ተመርቶ፣በየቦታው እየተሸጠ ነው፡፡ የክልሉ የግብርና ቢሮ ጫት እንደተስፋፋ ቢገልፅም፣በምን ያህል ሄክታር መሬት ምን ያህል አርሶአደሮች እያመረቱት እንደሆነ የተጠናከረ መረጃ የለውም፡፡ብቻ ጫት በከፍተኛ ሁኔታ ውሃም ስለሚፈልግ የመስኖ ምርትን እየተሻማው ነው፡፡ ለአባይ ና ጣናም ጫት ስጋት ሆኗል፡፡ በጎንደር ዮኒቨርሲቲ የህክምና መምህር የሆኑት ዶክተር ብርሌው ተሾመ፣ እንደሚሉት ጫት በቅፅበት አነቃቅቶ ለድብርት ስለሚጋብዝ ለአዕምሮ ህመም መነሻ ነው ብለዋል፡፡ለሌሎች ሱሶችም ገፊ ነው፡፡ በአማኑኤል ሆስፒታል ካሉ የአዕምሮ ህሙማን ውስጥ 70% በጫት እና ተያያዥ ደባል ሱሶች እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ጫት በጊዜ ና በገንዘብ ላይ የሚያመጣው ጫናም ቀላል አይደለም፡፡ በመሆኑም ክልሉ ጫት ላይ የንግድ ስርዓቱን መገደብ፣የሚቃምበትን እና የሚመረትበትን ቦታ መወሰን እስካልቻለ ድረስ ወጣቶች ውሏቸውን ሁሉ ጫት ማሳ ላይ ማድረጋቸው አይቀርም፡፡ስራ አጥነትን ለመቀነስ፣አማራጭ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን መንግስት ቀጠሮ ሳይሰጥ ሊሰራ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ጫት ተስፋ የመቁረጥ መደበቂያ ሆኖ መዝለቁ አይቀርም፡፡የሀይማኖት አባቶችም ማህበረሰባዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሁኔታው ያስገድዳቸዋል፡፡ በየሺሀሳብ አበራ
    0 Comments 0 Shares
  • ማስታወቂያ
    በ2009 ዓ/ም የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ
    ተማሪዎችና እና የመሰናዶ ት/ቤቶች በሙሉ፡-
    1. ውጤታችሁን ካያችሁ በኋላ የትምህርት መስክና
    የዩንቨርስቲ ምርጫ ማሻሻል የምትፈልጉ ተማሪዎች ለት/
    ቤታችሁ በማሳወቅ በት/ቤታችሁ ተወካይ በኩል ከነሐሴ 5
    እስከ 20/ 2009 ዓ/ም ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን
    እናሳውቃለን፡፡
    2. የትምህርት ቤት ተወካዮች የተማሪዎችን ምርጫ
    በማስተካከል እንድትተባበሯቸው እንጠይቃለን፡፡
    3. ተማሪዎች ምርጫችሁ በትክክል መተላለፉን
    እንድታረጋግጡ እና እንድትከታተሉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
    4. ለአዎንታዊ ድጋፍ የሚያግዝ መረጃ ከት/ቤት ሸኚ
    ደብዳቤ ጋር አስከ ነሐሴ 20/2009 ዓ/ም ለኤጀንሲው
    እንድታቀርቡ እንገልጻለን፡፡
    5. ከተማሪዎች ምደባ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም መረጃ
    ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
    ኤጀንሲው!
    ማስታወቂያ በ2009 ዓ/ም የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎችና እና የመሰናዶ ት/ቤቶች በሙሉ፡- 1. ውጤታችሁን ካያችሁ በኋላ የትምህርት መስክና የዩንቨርስቲ ምርጫ ማሻሻል የምትፈልጉ ተማሪዎች ለት/ ቤታችሁ በማሳወቅ በት/ቤታችሁ ተወካይ በኩል ከነሐሴ 5 እስከ 20/ 2009 ዓ/ም ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 2. የትምህርት ቤት ተወካዮች የተማሪዎችን ምርጫ በማስተካከል እንድትተባበሯቸው እንጠይቃለን፡፡ 3. ተማሪዎች ምርጫችሁ በትክክል መተላለፉን እንድታረጋግጡ እና እንድትከታተሉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ 4. ለአዎንታዊ ድጋፍ የሚያግዝ መረጃ ከት/ቤት ሸኚ ደብዳቤ ጋር አስከ ነሐሴ 20/2009 ዓ/ም ለኤጀንሲው እንድታቀርቡ እንገልጻለን፡፡ 5. ከተማሪዎች ምደባ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም መረጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡ ኤጀንሲው!
    0 Comments 0 Shares