አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻሸመኔ ሪፈራል ሆስፒታል በሕዝብ ስም በእገዛ ከውጪ የመጡ የሕክምና መሳሪያዎች ያለ አገልግሎት ከስድስት አመታት በላይ ተቀምጠዋል፡፡
በከፍተኛ ወጪ ወደ ሆስፒታሉ የገቡ መሳሪያዎችን በተመለከተ የሻሸመኔ ፋና ኤፍ ኤም ባልደረባችን በስፍራው ባደረገው ቅኝት ያለ ምንም አገልግሎት መቀመጣቸውን ታዝቧል።
አምቡላንስን ጨምሮ እንደ ሲ ቲ ስካን እና ማሞ ግራፊ የመሳሰሉ የሕክምና መሳሪያዎችም ያለ አገልግሎት ግቢ ውስጥ ተቀምጠዋል።
አንድ አምቡላንስ፣ አንድ ተንቀሳቃሽ የህክምና አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪ እና አንድ የዳቦ መጋገሪያም ለፀሃይና ዝናብ በተጋለጠ መልኩ ተቀምጠዋል።
መሳሪያዎቹ ያለ አገልግሎት መቀመጣቸው ደግሞ የአካባቢው ነዋሪዎች የተሻለ ህክምና ለማግኘት ወደ ሃዋሳ እና አዲስ አበባ እንዲጓዙ አድርጓቸዋል።
ይህ መሆኑም ለተጨማሪ ወጪ እና ጊዜ እየዳረጋቸው መሆኑንም ይናገራሉ።
የሆስፒታሉ የፋይናንስ አስተዳደር ሃላፊ አቶ ሺፈራው ቶሌራ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ምላሽ፥ ለሲ ቲ ስካንና ለማሞ ግራፊው ማስቀመጫ የሚሆን አመች ክፍል ባለመኖሩ አገልግሎቱን መስጠት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
ችግሩን ለመቅረፍም ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር ለመሳሪያዎቹ የሚመጥንና አመች የህንጻ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
አምቡላንሱ እና ሌሎች የህክምና መሳሪያዎች በመለዋወጫ እጥረት ሳቢያ አገልግሎት መስጠት አለመቻላቸውንም አንስተዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ ፈይሳ ሳፈው በበኩላቸው፥ ለመሳሪያዎቹ የሚመጥን ክፍል እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው አጠቃላይ ችግሩን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ለዳቦ መጋገሪያው ስራ አለመጀመር ምክንያት የሆነውን የመብራት አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ ትራንስፎርመር እየተተከለ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለተሽከርካሪዎቹ የሚሆን መለዋወጫ በማቅረብም ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋልም ነው ያሉት፤ አጠቃላይ ችግሩ ተፈቶ በቀጣዩ አመት መሳሪያዎቹ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡም አስረድተዋል።

0 Comments
0 Shares