• በሳዑዲ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የትናንቱ እንዳይደገም

    አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአረብ ሀገራት ኢትዮጵያውያን በብዛት ከሚኖሩባቸው ሀገራት አንዷ ሳዑዲ አረቢያ ናት።

    በሀገሪቱ በየአመቱ የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ስነስርአቶችን ጨምሮ በልዩ ልዩ መንገዶች ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ዜጎች በህጋዊም ሆነ የሀገሪቱን ህግ ተላልፈው ለአመታት ሲኖሩባት የቆችው ይህቺ ሀገር፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገራት ዜጎች ዙሪያ ጠንካራ ህጎችን በማውጣት እርምጃ እየወሰደች የምትገኝ ሀገር ሆናለች። እንደ ሌሎች ሀገራት የውጭ ዜጎች በልዩ ልዩ የስደት ሰበቦች በሀገሪቱ ለመኖር ቢፈልጉ ይህንን የሚያስተናግድ ህግ የላትም። በአብዛኛው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ የገቡ የውጭ ዜጎች ይኖሩባታል።

    ኢኮኖሚዋ ከነዳጅ በሚገኝ ገቢ ላይ የተመሰረተው ይህች አገር የምርቱ በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው እየወረደ መምጣት ፈተና ሆኖባታል። ይህንን ተፅእኖ ለመቋቋም የመንግስት የወጪ ቅነሳን የሚያበረታቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አዘጋጅታ በመተግበር ላይ የምትገኝ ሲሆን፥ ስራ አጥ ለሆኑ የአገሬው ሰዎች የስራ እድልን ያመጣሉ ያለቻቸውን እርምጃዎችንም ስትወስድ ቆይታለች። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል በተለይም በአገልግሎት ዘርፎች ላይ የሚገኙ ስራዎች ያለ አግባብ በውጭ አገራት ዜጎች ተይዘዋልና እነዚህን የስራ እድሎች ለሳዑዲ ዜጎች ክፍት ሊደረጉ ይገባል ይላሉ ፖለቲከኞቿ። ይህ እንዲሆን ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን የተለያዩ አገራት ዜጎች ከግዛቷ ማስወጣትን እንደ አንድ አማራጭ በመያዝ በተለያዩ ጊዜ በዘመቻ ስታስወጣ ቆይታለች።

    በዚሁ ዙሪያ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ አንድ ጠንከር ያለ ህግ ደነገገ። በዚህም ህግ በሀገሪቱ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች ከሀገሪቱ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲወጡ አዛለች። ዘንድሮም መሰል ህግን አገሪቱ አውጥታለች። በቅርቡ የወጣው የምህረት አዋጅ ደግሞ በዚያች አገር ለመኖር የሚያስችላቸው ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የሌሎች አገራት ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያዛል።

    በአውሮፓውያኑ 2013 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሰጠው የሰባት ወራት የይቅርታ ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው የማይወጡ ከሆነ በሃይል እንደሚያስወጣ መንግስት በተደጋጋሚ አስታውቆ ነበር። በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ክስተት በዜጎች ህይወት እና በባዕድ ሀገር ያፈሩት ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት በማድረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሰላም እንዲመለሱ አድርጓል።

    በርካታ ዜጎች ግን የምህረት አዋጁን ባለመጠቀማቸው የሳዑዲ መንግስት የቀሩትን ቤት ለቤት አሰሳ ባማካሄድ ህጋዊ ሰነድ አልባ ዜጎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከአገር እንዲወጡ አደርጓል። በዚሁ ሂደት በኢትዮጵያውያኑ እና በሀገሪቱ ፖሊሶች መካከል በተደረጉ ግጭቶች ብዙዎቹ ለሃይል ጥቃት የተዳረጉ እና ሶስት ሰዎችም በእነዚሁ ግጭቶች ሳቢያ ለሞት መዳረጋቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ ነበር።

    እንደ ሚድል ኢስት ዘገባ ከአራት አመት በፊት ሳዑዲያ አረቢያ ባወጣችው የምህረት አዋጅ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰቃቂ ድርጊቶች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ ተፈፅመዋል። በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ላይ ይደርስ የነበረው እንግልት፣ የአካል ቅጣት እና ሞት መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት እንዳይደርስባቸው ማድረግ ቢቻልም ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት ቸል ባሉ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ደግሞ ከፍተኛ ችግር እንዲደርስባቸው መሆኑ አሳዛኝ ክስተት እንደነበር ማስታወስ ይገባናል።

    በወቅቱ የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ባወጡት ሪፖርቶች የምህረት አዋጁ ከተጠናቀቀ በኋላ የምህረት ጊዜውን ያላከበሩ የሁሉም ሀገር ዜጎች ለእንግልት፣ ለእስር፣ ለድብደባ እና ለሞት መዳረጋቸውን ያነሳሉ።

    የሳዑዲ አረቢያ ፖሊሶች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ የሀገሪቱን ህግ የተላለፉ እና በህገወጥ መንገድ ያለምንም የጎዙ ሰነድ እና የስራ ፍቃድ በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ሃይል በተቀላቀለበት ድርጊት በካምፕ በማሰር እና ከፍተኛ የአካል እና የስነልቦና ጥቃቶች ማድረሳቸው አይዘነጋም። የምህረት ጊዜው እንደቀላል አይተውት ያለፉት ኢትዮጵያውያን በሃይል ከሀገሪቱ መውጣት አልቀረላቸውም። ለፍተው ያፈሩት ጥሪትም በልዩ ልዩ መንገዶች ባክነዋል። የምህረት ጊዜውን ሳይጠቀሙ በመቅረታቸው በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ተይዘው ያፈረቱን ሀብት በአግባቡ ሳይዙ ተዋክበው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ100 ሺህ ይልቃል።

    ሳዑዲ አረቢያ እንደ አደጉ ሀገራት የስደተኛ መብት የሚያስጠብቅ ስርአት ባለመኖሩ፥ በፍርድ ቤት ተከራክሮ መብትን ማስከበር የማይታሰብ ነው። የምህረት አዋጅ ጊዜ ካበቃ በኋላ ደግሞ ለህግ አስከባሪዎች የሚሠጠው ስልጣን ገደብ የሌለው በመሆኑ የሰብአዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ መጠበቅም የዋህነት ነው። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ የሰጠችውን የምህረት ጊዜ በልተጠቀመ የየትኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ላይ እርምጃ እወስደላሁ እያለች ነው። ይህንን ተፈጻሚ እንደምታደረግ ከዚህ በፊት ያደረገችው ድረጊት ማስታወስ ይበቃል። የአሁኑ ደግሞ የባሰ እንደሚሆን መገመት አይከብድም።

    እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከህዳር 4/2013 ጀምሮ የሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ እና የሰራተኞች ሚኒስቴር ባለስልጣናት ሀገር አቀፍ ዘመቻ በማካሄድ ሰደተኞችን በማሰስ፣ በማሰር እና ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ሰራተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። በሚያዚያ 2013 ደግሞ የሰራተኛ ህግ አንቀጾች ህጉን በማሻሻል ሰነድ አልባ የውጭ ሀገር ሰራተኞች በማሰር እና በሃይል ከሀገር የማስወጣት ተግባር ጠንካራ እንዲሆን አድርገው ነበር።

    በወቅቱ በሳዑዲ አረቢያ የተካሄደው ዘመቻ በየሰፈሩ እና በገበያ ስፍራዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ የፍተሸ ጣቢያዎች መታወቂያ በመጠየቅ ሲሆን፥ በሁለት ቀናት ብቻ 20 ሺህ ሰራተኞችን እንዳሰረች መረጃዎች ያስረዳሉ። በ2104 ከመላው ሀገሪቱ 427 ሺህ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ከሀገር ማስወጣቷን ሪፖርቶች ይገልፃሉ። በውቅቱ የአረብ ኒውስ እንደዘገበው፥ 108 ሺህ 345 ሰደተኛ ሰራተኞችን በማሰር 90 ሺህ 450 የሚሆኑትን በ40 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው በግዴታ መልሳለች። እ.ኤ.አ በ2017 መጋቢት ወር ጀምሮ ባሉት አምስት ወራት ደግሞ 300 ሺህ የውጭ ሰራተኞችን ያባረረች ሲሆን፥ ይህም በአማካይ በቀን 2 ሺህ ሰዎችን በሃይል ወደ መጡበት መልሳለች ማለት ነው።

    የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ሀገራቸውም በምንም ሁኔታ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደማትታገስ እና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሀገሯ የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን በምንም ምክንያት በሀገሯ እንደማይኖሩ በጽኑ ተናግረዋል። ይህን አቋሟም በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሯል።

    ከሶስት አመት በፊት ሳዑዲ አረቢያ ያወጣችውን ህግ ያላከበሩ ስደተኞች ባከሄደቸው ዘመቻ ሰነድ አልባ የሆኑ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን ሀይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ወደ እስር ቤት ካምፖች እንዲገቡ ማድረጓን ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት ባደረጉት ፍተሸ ኢትዮጵውያንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ የሃይል ጥቃት መድረሱን ይገልጻሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያው በብዛት የሚኖሩበት ደቡባዊ ሪያድ በሚገኘው ማንፉሃ በተሰኘ መንደር በፖሊስ እና በኢትዮጵውያን መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፥ በርካቶች ደግሞ አካላቸው ላይ ጉዳት እና ያፈሩት ጥሪት እንዲያጡ ሆኗል።

    የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የሀገሪቱን ህግ የተላለፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ያለምንም እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዲስ የምህረት አዋጅ ማውጣቱ ይታወቃል። የምህረት አዋጁ ከመጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ እና ለ90 ቀናት የሚቆይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

    በህግ የሚፈለጉ፣ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች እና በእስር ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጉዳይ በምህረት አዋጁ አልተካተተም።

    በአዲሱ የሳዑዲ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦችም

    የሳዑዲን ህግ የተላለፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ያለምንም ቅጣት በ90 ቀናት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲያስቀምጥ ህጋዊ ማዕቀፉን ተከትለው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መመለስ የሚፈልጉ የሚመለሱበትን አማራጭ አስቀምጧል።
    በህግ የሚፈለጉ፣ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች እና በእስር ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጉዳይ በ2017 የምህረት አዋጅ አልተካተተም፤ እንደነዚህ አይነት ጉዳዮች ተለይተው በሀገሪቱ ህግ እንደሚስተናገዱ ተገልጿል።
    በህግ የሚፈለጉ እና የህግ ሂደታቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች ጉዳያቸው በሚመለከታቸው የፖሊስ ተቋማት ተጣርቶ የሚቀርብ ይሆናል።
    ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) ያላቸው ዜጎች የ2017 የምህረት አዋጅ አይመለከታቸውም የሚሉት ይገኙበታል።
    የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያለ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ማሳሰቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልኡካኑ ቡድን ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንቶ ነበር።

    የኢትዮጵያ መንግስት የሳዑዲ አረቢያን ህግ ተላልፈው በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይጉላሉ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር የሚመክር እና አቅጠጫ የሚያስቀምጥ የልኡካን ቡድን ወደ ሪያድ በመሄድ በሁኔታው ዙሪያ ወይይት አድርጓል። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ያለመጉላላት ወደ ሃገራቸው በሰላም እንዲመለሱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።

    በአሁን ወቅትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አስተባባሪ ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ ሲሆን፥ በሀገር አቀፍ ደረጃም ስራውን የሚመራ ግብረ ሃይል መቋቋሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየገለጸ ይገኛል።

    በዚህ መልኩም በሪያድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ጅዳ ባለው ቆንጽላ ጽህፈት ቤት አማካኘነት ለዜጎች አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ ድጋፍ በማድረግ ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እደረገ ነው። ይህንኑ የመንግስት ማሳሰቢያ ሰምተው ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ቢሆንም፥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በዚያች አገር ከሚኖሩ አስከ 300 ሺህ የሚደርስ ኢትዮጵያውያን መካከል በይቅርታ ጊዜው ለመጠቀም የጉዞ ሰነድ የወሰዱት ዜጎች ቁጥር 23 ሺህ ገደማ ብቻ መሆኑ እንዳሳሰበው መንግስት በተደጋጋሚ በመግለፅ ላይ ይገኛል።

    ሚኒስቴሩ በመንግስት በኩል እስከ 90 ቀናት ወደ ሃገራቸው ለሚመለሱ ዜጎች ወደ የመጡበት አካባቢ የሚመለሱበትና ቀጣይ ህይወታቸውን የሚመሩበት ሁኔታ ላይ ከዚህ ቀደም እንደተደረገው መንግስት አስፈላጊውን ሁኔታ እንደሚመቻች አስታወቋል።

    በባእድ ሀገር ለፈተው ያፈሯቸው ንብረቶቻቸው በቀረጥ ሳቢያ ችግር እንዳይገጥማቸውም መንግስት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ የፈቀደ ሲሆን፥ መንግስታዊ እና መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተመላሾቹን በሚገባ ለማደራጀት እና ቀጣይ ህይወታቸውን የሚመሩበት ብርቱ ድጋፍ እንደሚያደረጉ ቃል ገብተዋል።

    በዚህ ሁሉ ጥረት መሃል በሳዑዲ አረቢያ መንግስት የተሰጠው የምህረት አዋጅ እና ቀነ ገደብ ግን በዚያች ሃገር በሚገኙ እና ወደ ሃገራቸው በተመለሱ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት መኖሩን ሰሞኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባናገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ተስተውሏል።

    ከአመታት ቆይታ በኋላ በአዋጁ ምክንያት ወደ ሃገሯ የተመለሰችው ወጣት መስተዋት ሃገሯ ብትገባም የሌሎችን መመለስ ግን አትደግፍም ።

    እንደ እርሷ ገለጻ ዓረብ ሃገር ፈተናው የበዛ ቢሆንም ሄዶ ስራ መስራት ያስፈልጋልና ዛሬ ብትመለስም ወደዛው ስለመመለስ እንደምታስብ ትናገራለች።

    ከመስታወት ጋር ወደ ሃገሯ የተመለሰችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ ከጓደኛዋ በተቃራኒው በዚያች ሃገር መቆየት ካለው ፈተና አንጻር የማይመከር ነው ትላለች።

    ከአራት ዓመት በፊት በሳዑዲ እስር ቤት ከርሞ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሃብቶም ደግሞ፥ ዓመታት ለፍቶ ያፈራውን ንብረት እዚያው ትቶ ወደ ሃገሩ መግባቱን ያስታውሳል።
    ይህ የእርሱ እጣ ፋንታ በሌሎች የሃገሩ ልጆች ላይ እንዳይደርስም አዋጁን ተጠቅመው እንዲወጡ ይመክራል።

    የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብሰባ ላይ የመኖሪያ ፈቃድ አልባ የሌሎች አገራት ዜጎችን በለማስወጣት ያለውን ጽኑ አቋሙ ይፋ አድርጓል። በመሆኑም በአውሮፓውያኑ 2013 ላይ የይቅርታ ጊዜውን ተጠቅመው ባልወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ዘንድሮ እንዳይደገም ሁሉም ወገን የበኩሉን ሚና እንዲጫወት መንግስት መጎትጎቱን ቀጥሏል። የከፋ ሁኔታ ሲፈጠር የዜጎችን ጉዳት ለማህበራዊ ገፆች ፍጆታ ከመጠቀም ይልቅ አሁን ላይ እነዚህን ገፆችንም ሆነ ሌሎች መንገዶችን ተጠቅሞ ኢትዮጵያውያኑ የይቅርታ ጊዜውን እንዲጠቀሙ እና ሊመጣ ከሚችለው ጥቃት እንዲድኑ ማሳሰብ ለሁሉም ይበጃል።

    በእስክንድር ከበደ
    በሳዑዲ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የትናንቱ እንዳይደገም አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአረብ ሀገራት ኢትዮጵያውያን በብዛት ከሚኖሩባቸው ሀገራት አንዷ ሳዑዲ አረቢያ ናት። በሀገሪቱ በየአመቱ የሚካሄዱ ሃይማኖታዊ ስነስርአቶችን ጨምሮ በልዩ ልዩ መንገዶች ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ዜጎች በህጋዊም ሆነ የሀገሪቱን ህግ ተላልፈው ለአመታት ሲኖሩባት የቆችው ይህቺ ሀገር፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በውጭ ሀገራት ዜጎች ዙሪያ ጠንካራ ህጎችን በማውጣት እርምጃ እየወሰደች የምትገኝ ሀገር ሆናለች። እንደ ሌሎች ሀገራት የውጭ ዜጎች በልዩ ልዩ የስደት ሰበቦች በሀገሪቱ ለመኖር ቢፈልጉ ይህንን የሚያስተናግድ ህግ የላትም። በአብዛኛው ከተለያዩ ሀገራት ወደ ሀገሪቱ የገቡ የውጭ ዜጎች ይኖሩባታል። ኢኮኖሚዋ ከነዳጅ በሚገኝ ገቢ ላይ የተመሰረተው ይህች አገር የምርቱ በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው እየወረደ መምጣት ፈተና ሆኖባታል። ይህንን ተፅእኖ ለመቋቋም የመንግስት የወጪ ቅነሳን የሚያበረታቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን አዘጋጅታ በመተግበር ላይ የምትገኝ ሲሆን፥ ስራ አጥ ለሆኑ የአገሬው ሰዎች የስራ እድልን ያመጣሉ ያለቻቸውን እርምጃዎችንም ስትወስድ ቆይታለች። ከእነዚህ እርምጃዎች መካከል በተለይም በአገልግሎት ዘርፎች ላይ የሚገኙ ስራዎች ያለ አግባብ በውጭ አገራት ዜጎች ተይዘዋልና እነዚህን የስራ እድሎች ለሳዑዲ ዜጎች ክፍት ሊደረጉ ይገባል ይላሉ ፖለቲከኞቿ። ይህ እንዲሆን ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን የተለያዩ አገራት ዜጎች ከግዛቷ ማስወጣትን እንደ አንድ አማራጭ በመያዝ በተለያዩ ጊዜ በዘመቻ ስታስወጣ ቆይታለች። በዚሁ ዙሪያ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት እ.ኤ.አ ከ2013 ጀምሮ አንድ ጠንከር ያለ ህግ ደነገገ። በዚህም ህግ በሀገሪቱ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች ከሀገሪቱ በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲወጡ አዛለች። ዘንድሮም መሰል ህግን አገሪቱ አውጥታለች። በቅርቡ የወጣው የምህረት አዋጅ ደግሞ በዚያች አገር ለመኖር የሚያስችላቸው ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የሌሎች አገራት ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያዛል። በአውሮፓውያኑ 2013 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በሰጠው የሰባት ወራት የይቅርታ ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው የማይወጡ ከሆነ በሃይል እንደሚያስወጣ መንግስት በተደጋጋሚ አስታውቆ ነበር። በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ክስተት በዜጎች ህይወት እና በባዕድ ሀገር ያፈሩት ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥረት በማድረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በሰላም እንዲመለሱ አድርጓል። በርካታ ዜጎች ግን የምህረት አዋጁን ባለመጠቀማቸው የሳዑዲ መንግስት የቀሩትን ቤት ለቤት አሰሳ ባማካሄድ ህጋዊ ሰነድ አልባ ዜጎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከአገር እንዲወጡ አደርጓል። በዚሁ ሂደት በኢትዮጵያውያኑ እና በሀገሪቱ ፖሊሶች መካከል በተደረጉ ግጭቶች ብዙዎቹ ለሃይል ጥቃት የተዳረጉ እና ሶስት ሰዎችም በእነዚሁ ግጭቶች ሳቢያ ለሞት መዳረጋቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ ነበር። እንደ ሚድል ኢስት ዘገባ ከአራት አመት በፊት ሳዑዲያ አረቢያ ባወጣችው የምህረት አዋጅ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰቃቂ ድርጊቶች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ ተፈፅመዋል። በአብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ላይ ይደርስ የነበረው እንግልት፣ የአካል ቅጣት እና ሞት መንግስት ባደረገው ከፍተኛ ጥረት እንዳይደርስባቸው ማድረግ ቢቻልም ፤ የጉዳዩን አሳሳቢነት ቸል ባሉ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ደግሞ ከፍተኛ ችግር እንዲደርስባቸው መሆኑ አሳዛኝ ክስተት እንደነበር ማስታወስ ይገባናል። በወቅቱ የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ባወጡት ሪፖርቶች የምህረት አዋጁ ከተጠናቀቀ በኋላ የምህረት ጊዜውን ያላከበሩ የሁሉም ሀገር ዜጎች ለእንግልት፣ ለእስር፣ ለድብደባ እና ለሞት መዳረጋቸውን ያነሳሉ። የሳዑዲ አረቢያ ፖሊሶች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ የሀገሪቱን ህግ የተላለፉ እና በህገወጥ መንገድ ያለምንም የጎዙ ሰነድ እና የስራ ፍቃድ በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ሃይል በተቀላቀለበት ድርጊት በካምፕ በማሰር እና ከፍተኛ የአካል እና የስነልቦና ጥቃቶች ማድረሳቸው አይዘነጋም። የምህረት ጊዜው እንደቀላል አይተውት ያለፉት ኢትዮጵያውያን በሃይል ከሀገሪቱ መውጣት አልቀረላቸውም። ለፍተው ያፈሩት ጥሪትም በልዩ ልዩ መንገዶች ባክነዋል። የምህረት ጊዜውን ሳይጠቀሙ በመቅረታቸው በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ተይዘው ያፈረቱን ሀብት በአግባቡ ሳይዙ ተዋክበው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ100 ሺህ ይልቃል። ሳዑዲ አረቢያ እንደ አደጉ ሀገራት የስደተኛ መብት የሚያስጠብቅ ስርአት ባለመኖሩ፥ በፍርድ ቤት ተከራክሮ መብትን ማስከበር የማይታሰብ ነው። የምህረት አዋጅ ጊዜ ካበቃ በኋላ ደግሞ ለህግ አስከባሪዎች የሚሠጠው ስልጣን ገደብ የሌለው በመሆኑ የሰብአዊ መብቶች ይከበራሉ ብሎ መጠበቅም የዋህነት ነው። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ የሰጠችውን የምህረት ጊዜ በልተጠቀመ የየትኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ ላይ እርምጃ እወስደላሁ እያለች ነው። ይህንን ተፈጻሚ እንደምታደረግ ከዚህ በፊት ያደረገችው ድረጊት ማስታወስ ይበቃል። የአሁኑ ደግሞ የባሰ እንደሚሆን መገመት አይከብድም። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከህዳር 4/2013 ጀምሮ የሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ እና የሰራተኞች ሚኒስቴር ባለስልጣናት ሀገር አቀፍ ዘመቻ በማካሄድ ሰደተኞችን በማሰስ፣ በማሰር እና ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ሰራተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርገዋል። በሚያዚያ 2013 ደግሞ የሰራተኛ ህግ አንቀጾች ህጉን በማሻሻል ሰነድ አልባ የውጭ ሀገር ሰራተኞች በማሰር እና በሃይል ከሀገር የማስወጣት ተግባር ጠንካራ እንዲሆን አድርገው ነበር። በወቅቱ በሳዑዲ አረቢያ የተካሄደው ዘመቻ በየሰፈሩ እና በገበያ ስፍራዎች እንዲሁም በልዩ ልዩ የፍተሸ ጣቢያዎች መታወቂያ በመጠየቅ ሲሆን፥ በሁለት ቀናት ብቻ 20 ሺህ ሰራተኞችን እንዳሰረች መረጃዎች ያስረዳሉ። በ2104 ከመላው ሀገሪቱ 427 ሺህ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ከሀገር ማስወጣቷን ሪፖርቶች ይገልፃሉ። በውቅቱ የአረብ ኒውስ እንደዘገበው፥ 108 ሺህ 345 ሰደተኛ ሰራተኞችን በማሰር 90 ሺህ 450 የሚሆኑትን በ40 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው በግዴታ መልሳለች። እ.ኤ.አ በ2017 መጋቢት ወር ጀምሮ ባሉት አምስት ወራት ደግሞ 300 ሺህ የውጭ ሰራተኞችን ያባረረች ሲሆን፥ ይህም በአማካይ በቀን 2 ሺህ ሰዎችን በሃይል ወደ መጡበት መልሳለች ማለት ነው። የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ሀገራቸውም በምንም ሁኔታ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንደማትታገስ እና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሀገሯ የሚኖሩ የውጭ ዜጎችን በምንም ምክንያት በሀገሯ እንደማይኖሩ በጽኑ ተናግረዋል። ይህን አቋሟም በሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሯል። ከሶስት አመት በፊት ሳዑዲ አረቢያ ያወጣችውን ህግ ያላከበሩ ስደተኞች ባከሄደቸው ዘመቻ ሰነድ አልባ የሆኑ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን ሀይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ወደ እስር ቤት ካምፖች እንዲገቡ ማድረጓን ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት ባደረጉት ፍተሸ ኢትዮጵውያንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ የሃይል ጥቃት መድረሱን ይገልጻሉ። በወቅቱ ኢትዮጵያው በብዛት የሚኖሩበት ደቡባዊ ሪያድ በሚገኘው ማንፉሃ በተሰኘ መንደር በፖሊስ እና በኢትዮጵውያን መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ ሶስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፥ በርካቶች ደግሞ አካላቸው ላይ ጉዳት እና ያፈሩት ጥሪት እንዲያጡ ሆኗል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የሀገሪቱን ህግ የተላለፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ያለምንም እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዲስ የምህረት አዋጅ ማውጣቱ ይታወቃል። የምህረት አዋጁ ከመጋቢት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ እና ለ90 ቀናት የሚቆይ እንደሆነ በተደጋጋሚ ተገልጿል። በህግ የሚፈለጉ፣ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች እና በእስር ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጉዳይ በምህረት አዋጁ አልተካተተም። በአዲሱ የሳዑዲ ህግ ውስጥ ከተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦችም የሳዑዲን ህግ የተላለፉ የውጭ ሀገር ዜጎች ያለምንም ቅጣት በ90 ቀናት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲያስቀምጥ ህጋዊ ማዕቀፉን ተከትለው ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ መመለስ የሚፈልጉ የሚመለሱበትን አማራጭ አስቀምጧል። በህግ የሚፈለጉ፣ የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች እና በእስር ቤት የሚገኙ የህግ ታራሚዎች ጉዳይ በ2017 የምህረት አዋጅ አልተካተተም፤ እንደነዚህ አይነት ጉዳዮች ተለይተው በሀገሪቱ ህግ እንደሚስተናገዱ ተገልጿል። በህግ የሚፈለጉ እና የህግ ሂደታቸውን ያልጨረሱ ግለሰቦች ጉዳያቸው በሚመለከታቸው የፖሊስ ተቋማት ተጣርቶ የሚቀርብ ይሆናል። ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ (ኢቃማ) ያላቸው ዜጎች የ2017 የምህረት አዋጅ አይመለከታቸውም የሚሉት ይገኙበታል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያለ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሚኖሩ የማንኛውም ሀገር ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ማሳሰቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልኡካኑ ቡድን ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንቶ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት የሳዑዲ አረቢያን ህግ ተላልፈው በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሳይጉላሉ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር የሚመክር እና አቅጠጫ የሚያስቀምጥ የልኡካን ቡድን ወደ ሪያድ በመሄድ በሁኔታው ዙሪያ ወይይት አድርጓል። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ ያለመጉላላት ወደ ሃገራቸው በሰላም እንዲመለሱ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጓል። በአሁን ወቅትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አስተባባሪ ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ ሲሆን፥ በሀገር አቀፍ ደረጃም ስራውን የሚመራ ግብረ ሃይል መቋቋሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየገለጸ ይገኛል። በዚህ መልኩም በሪያድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ጅዳ ባለው ቆንጽላ ጽህፈት ቤት አማካኘነት ለዜጎች አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ ድጋፍ በማድረግ ዜጎች በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እደረገ ነው። ይህንኑ የመንግስት ማሳሰቢያ ሰምተው ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ቢሆንም፥ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው በዚያች አገር ከሚኖሩ አስከ 300 ሺህ የሚደርስ ኢትዮጵያውያን መካከል በይቅርታ ጊዜው ለመጠቀም የጉዞ ሰነድ የወሰዱት ዜጎች ቁጥር 23 ሺህ ገደማ ብቻ መሆኑ እንዳሳሰበው መንግስት በተደጋጋሚ በመግለፅ ላይ ይገኛል። ሚኒስቴሩ በመንግስት በኩል እስከ 90 ቀናት ወደ ሃገራቸው ለሚመለሱ ዜጎች ወደ የመጡበት አካባቢ የሚመለሱበትና ቀጣይ ህይወታቸውን የሚመሩበት ሁኔታ ላይ ከዚህ ቀደም እንደተደረገው መንግስት አስፈላጊውን ሁኔታ እንደሚመቻች አስታወቋል። በባእድ ሀገር ለፈተው ያፈሯቸው ንብረቶቻቸው በቀረጥ ሳቢያ ችግር እንዳይገጥማቸውም መንግስት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ የፈቀደ ሲሆን፥ መንግስታዊ እና መንግሰታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተመላሾቹን በሚገባ ለማደራጀት እና ቀጣይ ህይወታቸውን የሚመሩበት ብርቱ ድጋፍ እንደሚያደረጉ ቃል ገብተዋል። በዚህ ሁሉ ጥረት መሃል በሳዑዲ አረቢያ መንግስት የተሰጠው የምህረት አዋጅ እና ቀነ ገደብ ግን በዚያች ሃገር በሚገኙ እና ወደ ሃገራቸው በተመለሱ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የተደበላለቀ ስሜት መኖሩን ሰሞኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባናገራቸው አስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ተስተውሏል። ከአመታት ቆይታ በኋላ በአዋጁ ምክንያት ወደ ሃገሯ የተመለሰችው ወጣት መስተዋት ሃገሯ ብትገባም የሌሎችን መመለስ ግን አትደግፍም ። እንደ እርሷ ገለጻ ዓረብ ሃገር ፈተናው የበዛ ቢሆንም ሄዶ ስራ መስራት ያስፈልጋልና ዛሬ ብትመለስም ወደዛው ስለመመለስ እንደምታስብ ትናገራለች። ከመስታወት ጋር ወደ ሃገሯ የተመለሰችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ ከጓደኛዋ በተቃራኒው በዚያች ሃገር መቆየት ካለው ፈተና አንጻር የማይመከር ነው ትላለች። ከአራት ዓመት በፊት በሳዑዲ እስር ቤት ከርሞ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሃብቶም ደግሞ፥ ዓመታት ለፍቶ ያፈራውን ንብረት እዚያው ትቶ ወደ ሃገሩ መግባቱን ያስታውሳል። ይህ የእርሱ እጣ ፋንታ በሌሎች የሃገሩ ልጆች ላይ እንዳይደርስም አዋጁን ተጠቅመው እንዲወጡ ይመክራል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብሰባ ላይ የመኖሪያ ፈቃድ አልባ የሌሎች አገራት ዜጎችን በለማስወጣት ያለውን ጽኑ አቋሙ ይፋ አድርጓል። በመሆኑም በአውሮፓውያኑ 2013 ላይ የይቅርታ ጊዜውን ተጠቅመው ባልወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ዘንድሮ እንዳይደገም ሁሉም ወገን የበኩሉን ሚና እንዲጫወት መንግስት መጎትጎቱን ቀጥሏል። የከፋ ሁኔታ ሲፈጠር የዜጎችን ጉዳት ለማህበራዊ ገፆች ፍጆታ ከመጠቀም ይልቅ አሁን ላይ እነዚህን ገፆችንም ሆነ ሌሎች መንገዶችን ተጠቅሞ ኢትዮጵያውያኑ የይቅርታ ጊዜውን እንዲጠቀሙ እና ሊመጣ ከሚችለው ጥቃት እንዲድኑ ማሳሰብ ለሁሉም ይበጃል። በእስክንድር ከበደ
    0 Comments 0 Shares
  • አቶ ዘላለም ጀማነህ በስድስት ዓመት እስራት ተቀጡ

    አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የቀድሞ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ።

    አቶ ዘላለም የማይታወቅ ሃብት ማከበት እና በክልሉ መንግስትና ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት ወቅት የተጣለባቸውን ሕዝባዊ አደራና ወገንተኝነት ወደ ጎን በመተው በክልሉ በተለያዩ የስልጣን ደረጃ በሰሩባቸው ጊዜያት ለዘመዶቻቸው በርካታ መሬት እንዲወስዱ በማድረግ ሙስና ወንጀል 14 ክሶች ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

    ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ዘላለም በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት እና በ11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።

    በእርሳቸው ስም የተመዘገበ የጭነት ተሽከርካሪ እንዲወረስም ነው ያዘዘው።

    በክስ መዝገቡ ስር ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት እና የሙስና ወንጀሉን ተባብሮ በመፈፀም የተከሰሱት የአቶ ዘላለም ጀማነህ ባለቤት ወይዘሮ ምስራቅ ቂጣታ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እና በ11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።

    በተከሳሿ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአዋሽ ባንክ የተቀመጠ ገንዘብም እንዲወረስ አዟል።

    ፍርድ ቤቱ የ11 ሺህ ብር ቅጣቱ ተከፍሎ የአምስት ዓመት እስራት ሳይፈፀም በሁለት ዓመት ገደብ እንዲታይ ውሳኔ አሳልፏል።

    ሶስተኛ ተከሳሽ ሚርጌሴ ገመዳ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እና 11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ነው ፍርድ ቤቱ የወሰነው።

    በጌታቸው ሙለታ
    አቶ ዘላለም ጀማነህ በስድስት ዓመት እስራት ተቀጡ አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የቀድሞ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጀማነህ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጡ። አቶ ዘላለም የማይታወቅ ሃብት ማከበት እና በክልሉ መንግስትና ድርጅት ውስጥ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት ወቅት የተጣለባቸውን ሕዝባዊ አደራና ወገንተኝነት ወደ ጎን በመተው በክልሉ በተለያዩ የስልጣን ደረጃ በሰሩባቸው ጊዜያት ለዘመዶቻቸው በርካታ መሬት እንዲወስዱ በማድረግ ሙስና ወንጀል 14 ክሶች ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። ጉዳያቸውን ሲመለከት የቆየው የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ዘላለም በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት እና በ11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በእርሳቸው ስም የተመዘገበ የጭነት ተሽከርካሪ እንዲወረስም ነው ያዘዘው። በክስ መዝገቡ ስር ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት እና የሙስና ወንጀሉን ተባብሮ በመፈፀም የተከሰሱት የአቶ ዘላለም ጀማነህ ባለቤት ወይዘሮ ምስራቅ ቂጣታ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እና በ11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል። በተከሳሿ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአዋሽ ባንክ የተቀመጠ ገንዘብም እንዲወረስ አዟል። ፍርድ ቤቱ የ11 ሺህ ብር ቅጣቱ ተከፍሎ የአምስት ዓመት እስራት ሳይፈፀም በሁለት ዓመት ገደብ እንዲታይ ውሳኔ አሳልፏል። ሶስተኛ ተከሳሽ ሚርጌሴ ገመዳ በአምስት ዓመት ከስድስት ወር እስራት እና 11 ሺህ ብር እንዲቀጡ ነው ፍርድ ቤቱ የወሰነው። በጌታቸው ሙለታ
    0 Comments 0 Shares
  • ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየወሩ የሚካሄደውን አዲስ አበባን የማፅዳት ንቅናቄ አስጀመሩ

    አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ በየወሩ የሚካሄድ የፅዳት ስራ ንቅናቄ ተጀመረ።

    መርሃ ግብሩ “እኔ ከተማዬን አፀዳለሁ እናንተስ” የሚል መሪ ቃል ያለው ሲሆን፥ ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የሚያስችሉ እቅዶችን የያዘ ነው ተብሏል።

    የፅዳት ንቅናቄውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ተጀምሯል።

    በንቅናቄው መጀመሪያ ላይ በመዲናዋ የሴቶች መታሰቢያ አደባባይ አካባቢን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች አፅድተዋል።
    የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በማፅዳት ስነስርዓቱ ላይ “በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ አካባቢን ማጽዳት ብቻ ሳይሆን፥ ቆሻሻን በየመንገዱ መጣል የሚፀየፍ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል” ብለዋል።

    ፅዳትን ባህል ለማድረግም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።

    ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማዋ ለኑሮ አዳጋች የምትሆንበት ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዛሬውኑ ለፅዳት መነሳት አለብን የሚል መልእክትንም አስተላልፈዋል።

    የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርአት ቀደም ሲል ያልተዘረጋ መሆኑን የተናገሩት የመዲናዋ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው፥ ይህንን ስርአት ለመዘርጋት የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

    በመዲናዋ የተለያዪ አቅጣጫዎች በተደረገው የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ዛሬ በርካቶች ተምሳሌታዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሲሆን፥ ከዚህ በኋላ በየወሩ የመጨረሻ ቅዳሜ ሁሉም የመንግስት የስራ ሀላፊ እና ነዋሪ በየአካባቢው የፅዳት ዘመቻ ላይ እንደሚሳተፍ ተመልክቷል።


    በትዕግስት ስለሺ
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየወሩ የሚካሄደውን አዲስ አበባን የማፅዳት ንቅናቄ አስጀመሩ አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ በየወሩ የሚካሄድ የፅዳት ስራ ንቅናቄ ተጀመረ። መርሃ ግብሩ “እኔ ከተማዬን አፀዳለሁ እናንተስ” የሚል መሪ ቃል ያለው ሲሆን፥ ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የሚያስችሉ እቅዶችን የያዘ ነው ተብሏል። የፅዳት ንቅናቄውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ተጀምሯል። በንቅናቄው መጀመሪያ ላይ በመዲናዋ የሴቶች መታሰቢያ አደባባይ አካባቢን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች አፅድተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በማፅዳት ስነስርዓቱ ላይ “በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ አካባቢን ማጽዳት ብቻ ሳይሆን፥ ቆሻሻን በየመንገዱ መጣል የሚፀየፍ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል” ብለዋል። ፅዳትን ባህል ለማድረግም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማዋ ለኑሮ አዳጋች የምትሆንበት ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዛሬውኑ ለፅዳት መነሳት አለብን የሚል መልእክትንም አስተላልፈዋል። የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርአት ቀደም ሲል ያልተዘረጋ መሆኑን የተናገሩት የመዲናዋ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው፥ ይህንን ስርአት ለመዘርጋት የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል። በመዲናዋ የተለያዪ አቅጣጫዎች በተደረገው የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ዛሬ በርካቶች ተምሳሌታዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሲሆን፥ ከዚህ በኋላ በየወሩ የመጨረሻ ቅዳሜ ሁሉም የመንግስት የስራ ሀላፊ እና ነዋሪ በየአካባቢው የፅዳት ዘመቻ ላይ እንደሚሳተፍ ተመልክቷል። በትዕግስት ስለሺ
    0 Comments 0 Shares
  • ዋልያዎቹ በሴካፋ ዋንጫ ከዩጋንዳ አቻ ተለያዩ

    አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2017 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ጨዋታውን አድርጓል።
    ከዩጋንዳ ጋር የተደረገው የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታም አንድ አቻ ተጠናቋል።
    ኢትዮጵያ ጨዋታውን 1 ለ 0 እየመራች ብትቆይም፥ በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ዩጋንዳዎች አቻ መሆን ችለዋል።
    ቡድኑ ባለፈው ሃሙስ በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 መሸነፉ የሚታወስ ነው።
    በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ደግሞ ደቡብ ሱዳንን 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።
    ውጤቱን ተከትሎም ዩጋንዳ በ5 ነጥብ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።
    የኢትዮጵያ የማለፍ እድል ደግሞ በነገው ጨዋታ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።
    ነገ ደቡብ ሱዳን ቡሩንዲን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻለች ዋልያዎቹ ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ፤ ይህ ካልሆነ ግን ከውድድሩ የሚሰናበቱ ይሆናል።

    ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
    ዋልያዎቹ በሴካፋ ዋንጫ ከዩጋንዳ አቻ ተለያዩ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2017 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ጨዋታውን አድርጓል። ከዩጋንዳ ጋር የተደረገው የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታም አንድ አቻ ተጠናቋል። ኢትዮጵያ ጨዋታውን 1 ለ 0 እየመራች ብትቆይም፥ በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ዩጋንዳዎች አቻ መሆን ችለዋል። ቡድኑ ባለፈው ሃሙስ በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 መሸነፉ የሚታወስ ነው። በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ደግሞ ደቡብ ሱዳንን 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል። ውጤቱን ተከትሎም ዩጋንዳ በ5 ነጥብ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀሏን አረጋግጣለች። የኢትዮጵያ የማለፍ እድል ደግሞ በነገው ጨዋታ ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ነገ ደቡብ ሱዳን ቡሩንዲን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻለች ዋልያዎቹ ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ፤ ይህ ካልሆነ ግን ከውድድሩ የሚሰናበቱ ይሆናል። ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
    0 Comments 0 Shares
  • What is on your mind? #Hashtag.. @Mention.. Link..hi hi
    What is on your mind? #Hashtag.. @Mention.. Link..hi hi
    0 Comments 0 Shares
  • What is on your mind? #Hashtag.. @Mention.. Link..??
    What is on your mind? #Hashtag.. @Mention.. Link..??
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    2
    1 Comments 0 Shares
  • am feel proud for joining #ethio.me
    am feel proud for joining #ethio.me
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares