ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየወሩ የሚካሄደውን አዲስ አበባን የማፅዳት ንቅናቄ አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ በየወሩ የሚካሄድ የፅዳት ስራ ንቅናቄ ተጀመረ።
መርሃ ግብሩ “እኔ ከተማዬን አፀዳለሁ እናንተስ” የሚል መሪ ቃል ያለው ሲሆን፥ ከተማዋን ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የሚያስችሉ እቅዶችን የያዘ ነው ተብሏል።
የፅዳት ንቅናቄውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ተጀምሯል።
በንቅናቄው መጀመሪያ ላይ በመዲናዋ የሴቶች መታሰቢያ አደባባይ አካባቢን ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለሰቦች አፅድተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በማፅዳት ስነስርዓቱ ላይ “በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ከተማዋን ፅዱ ለማድረግ አካባቢን ማጽዳት ብቻ ሳይሆን፥ ቆሻሻን በየመንገዱ መጣል የሚፀየፍ ትውልድ መፍጠር ያስፈልጋል” ብለዋል።
ፅዳትን ባህል ለማድረግም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማዋ ለኑሮ አዳጋች የምትሆንበት ደረጃ ላይ ከመድረሷ በፊት ዛሬውኑ ለፅዳት መነሳት አለብን የሚል መልእክትንም አስተላልፈዋል።
የከተማዋን ፈጣን እድገት የሚመጥን ዘመናዊ የቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ስርአት ቀደም ሲል ያልተዘረጋ መሆኑን የተናገሩት የመዲናዋ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው፥ ይህንን ስርአት ለመዘርጋት የከተማ አስተዳደሩ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።
በመዲናዋ የተለያዪ አቅጣጫዎች በተደረገው የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ዛሬ በርካቶች ተምሳሌታዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሲሆን፥ ከዚህ በኋላ በየወሩ የመጨረሻ ቅዳሜ ሁሉም የመንግስት የስራ ሀላፊ እና ነዋሪ በየአካባቢው የፅዳት ዘመቻ ላይ እንደሚሳተፍ ተመልክቷል።
በትዕግስት ስለሺ

0 Comments
0 Shares