• Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማይገባውን ቦታ ይዞ እየሠራ የሚገኝ ማንኛውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛ ራሱን እንዲያጋልጥ የተሰጠው የጊዜ ገደብ፣ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ተራዘመ፡፡

    የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ ማንኛውም በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እየሠራ የሚገኝ ኃላፊና ሠራተኛ፣ ከኅዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ራሱን እንዲያጋልጥ አስጠንቅቆ ነበር፡፡

    ነገር ግን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ራሳቸውን ያጋለጡ ሠራተኞች ከ20 የማይበልጡ በመሆናቸው፣ ቢሮው ለመጨረሻ ጊዜ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ማራዘሙ ከሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

    ከዚህ ጊዜ በኋላ በየመሥሪያ ቤቱ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች ምርመራ እንደሚጀምሩና በተሰበሰቡ ጥቆማዎች፣ እንዲሁም በሚካሄደው ምርመራ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ በመመርያው መሠረት ያላግባብ የተጠቀመውን ጥቅም እንዲከፍል ይደረጋል፣ በሕጉ መሠረትም ይቀጣል ተብሏል፡፡

    ነገር ግን በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሥራ ልምድና የሙያ ብቃት ማስረጃዎችን በመጠቀም፣ በመንግሥት ተቋማት በኃላፊነትም ሆነ በፈጻሚነት እየሠራ የሚገኝ ሠራተኛ ይቅርታ ከጠየቀ በሕግ ከመጠየቅም ሆነ ከሥራ ከመታገድ እንደሚድን ተገልጿል፡፡፡

    ‹‹አስተዳደሩ ይቅርታ የሚያደርግላቸው ሠራተኞችና ኃላፊዎች ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃቸውን አቅርበው በሚመጥናቸው የሥራ መደብ ላይ እንደገና ይመደባሉ፤›› ሲል ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

    በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በሥሩ በሚገኙ መሥሪያ ቤቶች በአጠቃላይ ከ105 ሺሕ በላይ ሠራተኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

    ከእነዚህ ሠራተኞች መካከል በትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ ቦታ የያዙ እንዳሉ ሁሉ፣ በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማይገባቸውን ቦታ የያዙ መኖራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

    በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞችና ኃላፊዎች፣ በከተማ አስተዳደሩ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል፡፡
    በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማይገባውን ቦታ ይዞ እየሠራ የሚገኝ ማንኛውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛ ራሱን እንዲያጋልጥ የተሰጠው የጊዜ ገደብ፣ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ተራዘመ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ ማንኛውም በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እየሠራ የሚገኝ ኃላፊና ሠራተኛ፣ ከኅዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ራሱን እንዲያጋልጥ አስጠንቅቆ ነበር፡፡ ነገር ግን በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ራሳቸውን ያጋለጡ ሠራተኞች ከ20 የማይበልጡ በመሆናቸው፣ ቢሮው ለመጨረሻ ጊዜ ያስቀመጠውን ቀነ ገደብ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ማራዘሙ ከሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ በየመሥሪያ ቤቱ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች ምርመራ እንደሚጀምሩና በተሰበሰቡ ጥቆማዎች፣ እንዲሁም በሚካሄደው ምርመራ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ በመመርያው መሠረት ያላግባብ የተጠቀመውን ጥቅም እንዲከፍል ይደረጋል፣ በሕጉ መሠረትም ይቀጣል ተብሏል፡፡ ነገር ግን በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሥራ ልምድና የሙያ ብቃት ማስረጃዎችን በመጠቀም፣ በመንግሥት ተቋማት በኃላፊነትም ሆነ በፈጻሚነት እየሠራ የሚገኝ ሠራተኛ ይቅርታ ከጠየቀ በሕግ ከመጠየቅም ሆነ ከሥራ ከመታገድ እንደሚድን ተገልጿል፡፡፡ ‹‹አስተዳደሩ ይቅርታ የሚያደርግላቸው ሠራተኞችና ኃላፊዎች ትክክለኛ የትምህርት ማስረጃቸውን አቅርበው በሚመጥናቸው የሥራ መደብ ላይ እንደገና ይመደባሉ፤›› ሲል ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና በሥሩ በሚገኙ መሥሪያ ቤቶች በአጠቃላይ ከ105 ሺሕ በላይ ሠራተኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ ሠራተኞች መካከል በትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ ቦታ የያዙ እንዳሉ ሁሉ፣ በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማይገባቸውን ቦታ የያዙ መኖራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞችና ኃላፊዎች፣ በከተማ አስተዳደሩ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ያላቸው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል፡፡
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • ታላቅ ቅናሽ
    ለ15 ቀን የሚቆይ
    ** 100 ብር የሞባይል ካርድ ጋር**
    አዳዲስ
    # ስልኮችን በሚያስገርም ዋጋ # ከሙሉ # ዋስትና እና # ከበቂ አቅርቦት ጋር
    ይዘን ቀርበናል
    ሁሉም ስልኮች በ ቴሌ ኔትዎርክ እንዲሰሩ ተፈቅዷል
    All are tele Registered
    +251910826067
    አዳዲስ ስልኮች
    ( Brand new phones)
    Samsung galaxy s4.........4300br
    Samsung galaxy S5.......5400br
    Samsung galaxy S6........7400br
    Samsung galaxy S6edge ......9200br
    Samsung galaxy s6 edge+ .....11000br
    Samsung galaxy S7edge .....13000br
    Samsung Note serious
    Samsung galaxy Note 3 ........5900br
    Samsung galaxy Note 4........7000br
    Samsung galaxy Note edge......8500br
    Samsung galaxy Note 5........9800br
    0910826067
    ታላቅ ቅናሽ ለ15 ቀን የሚቆይ ** 100 ብር የሞባይል ካርድ ጋር** አዳዲስ # ስልኮችን በሚያስገርም ዋጋ # ከሙሉ # ዋስትና እና # ከበቂ አቅርቦት ጋር ይዘን ቀርበናል ሁሉም ስልኮች በ ቴሌ ኔትዎርክ እንዲሰሩ ተፈቅዷል All are tele Registered +251910826067 አዳዲስ ስልኮች ( Brand new phones) Samsung galaxy s4.........4300br Samsung galaxy S5.......5400br Samsung galaxy S6........7400br Samsung galaxy S6edge ......9200br Samsung galaxy s6 edge+ .....11000br Samsung galaxy S7edge .....13000br Samsung Note serious Samsung galaxy Note 3 ........5900br Samsung galaxy Note 4........7000br Samsung galaxy Note edge......8500br Samsung galaxy Note 5........9800br 0910826067
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስገቡት የስራ መልቀቂያ ተቀባይነት አገኘ።

    የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን በሻህ የአሰልጣኙ የስራ መልቀቂያ በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት ማግኘቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል።

    አሰልጣኝ አሸናፊ በ100 ሺህ ብር ወርኃዊ ደመወዝ ዋልያዎቹን ለማሰልጠን ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር የሁለት ዓመት ኮንትራት የተሰጣቸው።

    ኮንትራቱም ከመጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ የነበረ ሲሆን፥ በቆይታቸው ዋልያዎቹን ካሜሮን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ግዴታ ተጥሎባቸው እንደበረ ይታወሳል።

    አሰልጣኝ አሸናፊ በወቅቱ በሰጡት መግለጫም፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልፀው ነበር።

    "ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቻ አይደለም ለቻን ውድድር ማሳለፍ ካልቻልኩ ሁለት ዓመት አልጠብቅም፤ በራሴ ፍቃድ እለቃለሁ" ማለታቸውም አይዘነጋም።

    አሰልጣኙ 2009 ዓ.ም ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ከመጡ ወዲህ ግን ብሄራዊ ቡድኑ ማሸነፍ የቻለው ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲን ብቻ ነው።

    በብሄራዊ ቡድኑ ቆይታቸው ስኬታማ መሆን ያልቻሉት አሰልጣኝ አሸናፊ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተውት የነበረው የስራ መልቀቂያ በዛሬው እለት ተቀባይነት አግኝቶላቸው ከዋልያዎቹ ጋር ተለያይተዋል።

    አሰልጣኝ አሸናፊ በቀጣይም ኢትዮ-ኤሌክትሪክን እንደሚያሰለጥኑ ተሰምቷል።

    በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ባለፈው ሳምንት ከስመምነት ደርሰዋል።

    ይህንን ተክተሎም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ፤ አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩን ተክተው በ2ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ቡድኑን እንደሚመሩ ይጠበቃል።
    የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስገቡት የስራ መልቀቂያ ተቀባይነት አገኘ። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን በሻህ የአሰልጣኙ የስራ መልቀቂያ በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት ማግኘቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል። አሰልጣኝ አሸናፊ በ100 ሺህ ብር ወርኃዊ ደመወዝ ዋልያዎቹን ለማሰልጠን ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር የሁለት ዓመት ኮንትራት የተሰጣቸው። ኮንትራቱም ከመጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ የነበረ ሲሆን፥ በቆይታቸው ዋልያዎቹን ካሜሮን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ግዴታ ተጥሎባቸው እንደበረ ይታወሳል። አሰልጣኝ አሸናፊ በወቅቱ በሰጡት መግለጫም፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልፀው ነበር። "ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቻ አይደለም ለቻን ውድድር ማሳለፍ ካልቻልኩ ሁለት ዓመት አልጠብቅም፤ በራሴ ፍቃድ እለቃለሁ" ማለታቸውም አይዘነጋም። አሰልጣኙ 2009 ዓ.ም ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ከመጡ ወዲህ ግን ብሄራዊ ቡድኑ ማሸነፍ የቻለው ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲን ብቻ ነው። በብሄራዊ ቡድኑ ቆይታቸው ስኬታማ መሆን ያልቻሉት አሰልጣኝ አሸናፊ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተውት የነበረው የስራ መልቀቂያ በዛሬው እለት ተቀባይነት አግኝቶላቸው ከዋልያዎቹ ጋር ተለያይተዋል። አሰልጣኝ አሸናፊ በቀጣይም ኢትዮ-ኤሌክትሪክን እንደሚያሰለጥኑ ተሰምቷል። በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ባለፈው ሳምንት ከስመምነት ደርሰዋል። ይህንን ተክተሎም አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ፤ አሰልጣኝ ብርሃኑ ባዩን ተክተው በ2ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ቡድኑን እንደሚመሩ ይጠበቃል።
    0 Comments 0 Shares
  • ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና የአሁኑን የህዝብ ቁጥር ላላማከሉ 10 የክልል ሆስፒታሎች ማስፋፊያ ሊደረግ ነው።

    በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ሆስፒታሎች ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ በመሆናቸው በየአካባቢያቸው ያሉ ነዋሪዎችን ቁጥር ከግንዛቤ ያላስገቡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

    ይህም ብቻ ሳይሆን የመሳርያ እና የባለሙያ እጥረት ታክሎባቸው የተለያዩ ታካሚዎቻቸውን በራሳቸው አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ እንደ ሪፈር ያሉ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እድርጓቸዋል።

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ጥበቃ ሚኒስርትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን፥ አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሎች ጋር በመሆን እድሜያቸው የገፉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት መታሰቡን ነግረዉናል።

    “በክልሎች የሚገኙ እና ከ56 እስከ 80 ዓመት ያስቆጠሩ፥ አሁን ያለውን የተገልጋይ ቁጥር ያላማከሉ ሆስፒታሎች መኖራቸውን እኔም በተለያዩ ጊዜያት ባደረኩት ጉብኝት አረጋግጫለሁ” ብለዋል፡፡

    በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚቀርቡት ጥያቄዎች አንዱ የነባር ሆስፒታሎች በአሁን ደረጃ የማይመጥኑ በመሆናቸው ማስፋፊያ እንዲደረግ መጠየቅ ነው ያሉት ሚንስትሩ፥ በዘንድሮው ዓመት የ10 ሆስፒታሎች ማስፋፊያ እናከናውናለን ብለዋል።

    ለአብነት በአማራ ክልል በደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሀን፣ ደሴ፣ ወልድያ እና ደብረታቦር ያሉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት ነው የታሰበው።

    እነዚህ ሆስፒታሎች የሚስፋፉት ካላቸው ይዞታ በተጨማሪ ባለ ስምንት ፎቅ ማስፋፊያ ተደርጎላቸው አሁን ያላቸውን የአልጋ ቁጥር ወደ 400 ከፍ እንዲል እንደሚደረግ እና የአገልግሎት ጥራትና ደረጃቸውም ከፍ ይደረጋል ተብሏል።

    ለማስፋፊያ ስራ የሚውለው በጀት 50 በመቶው በሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ፣ ቀሪው ደግሞ በክልሎች የሚሸፈን እንደሚሆን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ተናግረዋል።

    የሆስፒታሎቹን ወጪ በተመለከተም የሚወጣ ጨረታን ተመርኩዞ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።

    የማስፋፊያው ስራ ግን በዚህ ዓመት እንደሚጀመር ነው ፕሮፈሰር ይፍሩ የተናገሩት።

    የሆስፒታሎቹ ግንባታም በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

    የማስፋፊያ ስራዎቹ በሚኒስቴሩ እና በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚገነቡት በተጨማሪ፥ ዩኒቨርሲቲዎችም በራሳቸው በጀት ሆስፒታሎች ለመገንባት የጠየቁ መኖራቸው ነው የተገለፀው።
    ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና የአሁኑን የህዝብ ቁጥር ላላማከሉ 10 የክልል ሆስፒታሎች ማስፋፊያ ሊደረግ ነው። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ሆስፒታሎች ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ በመሆናቸው በየአካባቢያቸው ያሉ ነዋሪዎችን ቁጥር ከግንዛቤ ያላስገቡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን የመሳርያ እና የባለሙያ እጥረት ታክሎባቸው የተለያዩ ታካሚዎቻቸውን በራሳቸው አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ እንደ ሪፈር ያሉ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እድርጓቸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ጥበቃ ሚኒስርትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን፥ አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሎች ጋር በመሆን እድሜያቸው የገፉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት መታሰቡን ነግረዉናል። “በክልሎች የሚገኙ እና ከ56 እስከ 80 ዓመት ያስቆጠሩ፥ አሁን ያለውን የተገልጋይ ቁጥር ያላማከሉ ሆስፒታሎች መኖራቸውን እኔም በተለያዩ ጊዜያት ባደረኩት ጉብኝት አረጋግጫለሁ” ብለዋል፡፡ በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚቀርቡት ጥያቄዎች አንዱ የነባር ሆስፒታሎች በአሁን ደረጃ የማይመጥኑ በመሆናቸው ማስፋፊያ እንዲደረግ መጠየቅ ነው ያሉት ሚንስትሩ፥ በዘንድሮው ዓመት የ10 ሆስፒታሎች ማስፋፊያ እናከናውናለን ብለዋል። ለአብነት በአማራ ክልል በደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሀን፣ ደሴ፣ ወልድያ እና ደብረታቦር ያሉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት ነው የታሰበው። እነዚህ ሆስፒታሎች የሚስፋፉት ካላቸው ይዞታ በተጨማሪ ባለ ስምንት ፎቅ ማስፋፊያ ተደርጎላቸው አሁን ያላቸውን የአልጋ ቁጥር ወደ 400 ከፍ እንዲል እንደሚደረግ እና የአገልግሎት ጥራትና ደረጃቸውም ከፍ ይደረጋል ተብሏል። ለማስፋፊያ ስራ የሚውለው በጀት 50 በመቶው በሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ፣ ቀሪው ደግሞ በክልሎች የሚሸፈን እንደሚሆን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ተናግረዋል። የሆስፒታሎቹን ወጪ በተመለከተም የሚወጣ ጨረታን ተመርኩዞ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል። የማስፋፊያው ስራ ግን በዚህ ዓመት እንደሚጀመር ነው ፕሮፈሰር ይፍሩ የተናገሩት። የሆስፒታሎቹ ግንባታም በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። የማስፋፊያ ስራዎቹ በሚኒስቴሩ እና በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚገነቡት በተጨማሪ፥ ዩኒቨርሲቲዎችም በራሳቸው በጀት ሆስፒታሎች ለመገንባት የጠየቁ መኖራቸው ነው የተገለፀው።
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares