• Baqattoonni Itoophiyaa fi Ertiraa biyya waldhabdee keessa jirtu Yaman keessaa gargaarsa namoomaa dhabne jedhan.
    Baqattoonni Itoophiyaa fi Ertiraa biyya waldhabdee keessa jirtu Yaman keessaa gargaarsa namoomaa dhabne jedhan.
    WWW.BBC.COM
    Baqattoonni Itoophiyaa fi Ertiraa Yamanitti gargaarsa dhabne jedhan
    Baqattoonni Itoophiyaa fi Ertiraa biyya waldhabdee keessa jirtu Yaman keessaa gargaarsa namoomaa dhabne jedhan.
    0 Comments 0 Shares
  • ዝማዴ . . . የኔ የምትላቸው ሰዎች ሁሌም አብረውህ አይደሉም ። አንዴ ቀን ከጣለህ እንደወደቀ ዛፍ ፈላጭህ ብዙ ነው ፤ ማያ'ን ይሆኑብሃል ። Choose ur friends wisely ! አልያ ትነጫለህ
    ዝማዴ . . . የኔ የምትላቸው ሰዎች ሁሌም አብረውህ አይደሉም ። አንዴ ቀን ከጣለህ እንደወደቀ ዛፍ ፈላጭህ ብዙ ነው ፤ ማያ'ን ይሆኑብሃል ። Choose ur friends wisely ! አልያ ትነጫለህ
    0 Comments 0 Shares
  • #ቅዱስ_ያሬድ_ማን_ነው?
    ኢትዮጵያዊው ርእሰ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ፡ ሚያዝያ ፭ (5) ቀን ፬፻፺፫ (493) ዓ፡ም፡ በአክሱም ከተማ ተወለደ ። አባቱ አዳም የሚባል ሲሆን ፥ እናቱ ታውክሊያ ትባላለች ። የትውልድ ሐረጉም ከአክሱም ካህናት ነው ፡፡ የ፮ ዓመት ሕፃን ሲሆን ፡ አባቱና እናቱ ይስሐቅ ለሚባል ለአክሱማዊው መምህር አስተምርልን ብለው ሰጡት ፡፡ ይሁን እንጂ ትምህር አልገባው ብሎ ስለተቸገረና መምህሩንም ስላስቸገረ መምህሩ ያሬድን መልሶ ወደ አባቱ ዘንድ ላከው ፡፡ በመሐሉም ወላጅ አባቱ ስለሞተበት እናቱ ታውክሊያ ለወንድሜ ለአክሱም ቄሰ ገበዝ ለአባ ጌዴዎን እንዲያሳድገ ውና እንዲያስተምረው ሰጠችው ፡፡ አባ ጌዴዎንም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መምህር ነበርና በግዕዝ ፡ በእብራይስጥ በግሪክና በዓረብ ቋንቋዎች ይተረጉማቸው ነበር ፡፡ አባ ጌዴዎን ያሬድን አብሯቸው እንዲኖር በማድረግ ቢያስተምሩ ትም ለብዙ ዓመታት መዝሙረ ዳዊትን ማጥናት አቅቶት አብረውት ከሚማሩት ሕዓናት ጋር ሊወዳደር ባለመቻሉና ወደኋላ በመቅረቱ አባ ጌዴዎን ያሬድን በየጊዜው ይመክሩትና ይገሥፁት ነበር ፡፡ ያሬድ በትምህርት ደካማ ስለነበረ አስተማሪዎች የሚስጡትን ትምህርት ደጋ ግሞ ቢያጠናም አልሆንለት ስለአለ የትምህርት ጓደኞቹ ሲቀልዱበትና ሲያፌዙበት ይውሉ ነበር ። አጎቱ አባ ጌዴዎን በያሬድ ስንፍና ተማሮ አንድ ቀን ለምን እንደሌሎቹ ጓደኞችህ በደምብ አታጠናምመ ብሎ ያሬድን ክፉኛ ገረፈው ፡፡ ያሬድ በአጋጠመው የትምህርት አለመሳካትት ተስፋ ቆርጦ የትም ሔዶ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ቁርጥ ሐሳብ አደረገ ፡፡
    ያሬድ ከተማሪ ቤቱ ጠፍቶ ወደ አጎቱ አገር ወደ መደባይ ወለል ሲሔድ ኃይለኛ ዝናብ ስለዘነበ ከአክሱም ከተማ ፬ (4) ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ክምትገኝ ማይከራኸ ከምትባል ምንጭ ውኃ አጠገብ ወደአለው ዛፍ ሥር ተጠግቶ መጠለል ግድ ሆነበት ፡፡ ዛፉን ተጠግቶ ደገፍ ብሎ አንደቆመ በምን ምክንያት በትምህርት ከጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሊያስብና ሲያሰላስል ሲያዝንና ሲተክዝ ከቆየ በኋላ ፡ ሐሳቡን የሚያስለውጥ ነገር በድንገት ተመለከተ ፡፡ ይኸውም አንድ ጉንዳን አንድ የእህል ፍሬ ተሸክሞ ወደዛፍ ለመውጣት ከፍተኛ ሙከራ ሲያደርግ አየ። ጉንዳኑ የተሸከመውን ይዞ ስድስት ጊዜ ለመውጣት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ክብዙ ድካምና ጥረት በኋላ በሰባተኛወ ሙከራ የተሸከማትን የእህል ፍሬ ይዞ ወጣ ። በሙሉ አትኩሮት ይመለከተውና ይከታተለው የነበረው ያሬድም በድንገት ስሜቱ ተነካ ፡፡ ይህ አነስተኛ ፍጡር ከብዙ ጥረት በኋላ ያሰበውን ሲፈጽም የእኔ ተስፋ መቁረጥ ምን ይባላል ሲል ራሱን በራሱ ወቀሰ ከጉንዳኑ ያገኘው ትምህርት ልቡን ስለነካው ስሜቱንም ስለቀሰቀሰውና የጉንዳኑን ትጋትም አይቶ ስለ ተደነቀ በራሱ ደካማነት ተጸጽቶ አለቀሰ ፡፡ ያሬድ በዚሁ አነስተኛ ፍጡር ጥረትና ተስፋ አለመቁረጥ ተደንቆ ራሱን እንዲመረምር ስሜቱን ስለሎረኮረው ፥ ወደ አክሱም ተመልሶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ ። የሰው አፈጣጠር ከዚህ አነስተኛ ፍጥረት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ስለተገነዘበ ፡ ያጉቱን ምክርና ተግሣፅ ለሕይወቱ የሚጠቅም እንደሆነ በመረዳት ያለውንም ትምህርት በትጋት ቢማርና ቢያጠና የተሻለ ውጤት ሊያገኝ እንደሚችል በማመን ወደ አጉቱና ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ወደ አባ ጌዴዎን ተመልሶ በመምጣት አባቴ ሆይ ይቅር በለኝና እንደ ቀድሞ አስተምረኝ ብሎ አጉቱ እግር ላይ ወደቀ፡፡ መምህሩ አባ ጌዴዎንም ፈቅደውለት ዳዊቱን ያስተምሩት ጀመር ። ሕፃኑ ያሬድም ትምህርቱን እየተማረ ሁልጊዜ በጽሞና ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲ ያን እየገባ "መሖሪ እግዚአብሔር ዐይነ ልቦናየን አብራልኝ" እያለ በየቀኑ በንጹሕ ልቦና ይጸልይ ነበር ። መሐሪውና የቅር ባዩ እግዚአብሔር ርም ልመናውን ሰምቶ ዐይነ ልቦናውን አበራለትና ትምህርቱ ተገለጸለት። ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ከፍተኛና የማይታሰብ ለውጥ በማምጣቱ ጓደኞቹና መምህራኑ እጅግ በጣም ተደነቁ ፡፡ በዚህ ፈጣን የትምህርት መቀበል ችሎታ የብሉይ ኪዳንንና የአዲስ ኪዳንን ትርጓሜ መጻሕፍት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨረሰ።

    ያሬድ ከፍተኛ የትምህርት ተሰጥዎ ያለው በመሆኑ ትምህርቱን በጣም አስደናቂ በሆነ መንገድ ፈጽሞ ዲያቆን ሆነ ፡፡ ከመምህሩ ከአባ ጌዴዎን በተማረው መሠረት የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ደህና አድርጉ ያውቅ ነበር ይባላል ፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስና እንዲሁም በውጭ አገር ቋንቋዎች የአጉቱን የመምህር ጌዴዎንን ሙያ አጠናቆ ቻለ ፡፡ ያሬድ አጉቱ ሲሞት የዐሥራ አራት አመት ልጅ ቢሆንም የአጉቱን ሙያና የትምህርት ወንበር ተረክቦ ማስተማር ጀመረ። በግንቦት ፲፩ (11) ቀን ስንክሳር በተባለው የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ "ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶና ተነሣሥቶ የዜማ ድርሰቶቹን አዘጋጀ" ይላል። በዚሁ ስንክሳር እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዚች ምድር እንዲመስገን በፈለገ ጊዜ ያሬድን በራሱ ቋንቋ ሰማያዊ ዜማ እንዲያስተምሩት በአእዋፍ አምሳል ሦስት መላእክትን ከገነት ላከለት ይላል ፥፡ እነሱም ያሬድ ካለበት ሥፍራ አንጻር ባለው አየር ላይ ረበው (አንዣብበው) ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ አዲስ ዜማ አሰሙት ፡፡ ያን ጊዜ ያሬድ በጣዕመ ዜማቸው ተመስጦ ቁሞ ሲያዳምጥ ወዲያውኑ ወፎቹ በግዕዝ ቋንቋ "ብጹዕ ወክቡር አንተ ያሬድ ብጽፅት ከርሥ አንተ ጾረተከ ውብጹዓት አጥባት አላ ሐአናከ" ብለው በአንድነት አመስግኑት። ትርጉሙ "የተመሰገንክና የተክበርክ ያሬድ ሆይ ፡ አንተን የተሸከመች ማኅፀን የተመስገነች ናት ፡፡ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው" ብለው አመሰገኑት ፡፡ ከዚያም ሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ወደ ሚዘምሩበት ወጋ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አሳረጉት ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመንበረ ጸባዖት ፊጓ ቁሞ ከሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በፍጥነት የሰማው ማኀሌት ሁቦ በመንፈስ እግዚአብሔር ተገለጸለትና በልቦናው የተሣለበትን ጰዋትዜ ዜማ በቃሉ ያዜም ጀመር ፡፡ ከዚያም ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ አክሱም በተመለሰ ጊዜ ክጥዋቱ በ፫ ሰዓት ወደ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በታቦተ ጽዮን አንጻር ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፡ በከፍተኛ ድምፅ በአራራይ ዜማ ሃሌ ሉያ ለአብ ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፡ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቅዳሜሃ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘክመ ይገብር ግብራ ለደብተራ" ብሉ ሥነፍጥረቱንና ሰማያዊት ጽዮንን አሰመልክቶ ዘመረ ይህችንም ማኅሌት አርያም ብሎ ጠራት ዞ አርያምም ማለት ልዕልና ሰባተኛ ሰማይ መንበረ እግዚአብሔር ማለት ነው ፡፡ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ መላእክት እንደ ከበሮ እንቢልታ፣ ጸናጽል ፣ ማሲንቆና በገና በመሳሰሉት የማኅሌት መሣሪያዎች እየዘመሩ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ስለስማ እነዚህን መሣሪያዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ አደረጋቸው ፡፡

    ምንጭ:-
    - "የኢትዮጵያ ሥልጣኔ"፣ በላይ ግደይ
    #ቅዱስ_ያሬድ_ማን_ነው? ኢትዮጵያዊው ርእሰ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ፡ ሚያዝያ ፭ (5) ቀን ፬፻፺፫ (493) ዓ፡ም፡ በአክሱም ከተማ ተወለደ ። አባቱ አዳም የሚባል ሲሆን ፥ እናቱ ታውክሊያ ትባላለች ። የትውልድ ሐረጉም ከአክሱም ካህናት ነው ፡፡ የ፮ ዓመት ሕፃን ሲሆን ፡ አባቱና እናቱ ይስሐቅ ለሚባል ለአክሱማዊው መምህር አስተምርልን ብለው ሰጡት ፡፡ ይሁን እንጂ ትምህር አልገባው ብሎ ስለተቸገረና መምህሩንም ስላስቸገረ መምህሩ ያሬድን መልሶ ወደ አባቱ ዘንድ ላከው ፡፡ በመሐሉም ወላጅ አባቱ ስለሞተበት እናቱ ታውክሊያ ለወንድሜ ለአክሱም ቄሰ ገበዝ ለአባ ጌዴዎን እንዲያሳድገ ውና እንዲያስተምረው ሰጠችው ፡፡ አባ ጌዴዎንም በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት መምህር ነበርና በግዕዝ ፡ በእብራይስጥ በግሪክና በዓረብ ቋንቋዎች ይተረጉማቸው ነበር ፡፡ አባ ጌዴዎን ያሬድን አብሯቸው እንዲኖር በማድረግ ቢያስተምሩ ትም ለብዙ ዓመታት መዝሙረ ዳዊትን ማጥናት አቅቶት አብረውት ከሚማሩት ሕዓናት ጋር ሊወዳደር ባለመቻሉና ወደኋላ በመቅረቱ አባ ጌዴዎን ያሬድን በየጊዜው ይመክሩትና ይገሥፁት ነበር ፡፡ ያሬድ በትምህርት ደካማ ስለነበረ አስተማሪዎች የሚስጡትን ትምህርት ደጋ ግሞ ቢያጠናም አልሆንለት ስለአለ የትምህርት ጓደኞቹ ሲቀልዱበትና ሲያፌዙበት ይውሉ ነበር ። አጎቱ አባ ጌዴዎን በያሬድ ስንፍና ተማሮ አንድ ቀን ለምን እንደሌሎቹ ጓደኞችህ በደምብ አታጠናምመ ብሎ ያሬድን ክፉኛ ገረፈው ፡፡ ያሬድ በአጋጠመው የትምህርት አለመሳካትት ተስፋ ቆርጦ የትም ሔዶ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ቁርጥ ሐሳብ አደረገ ፡፡ ያሬድ ከተማሪ ቤቱ ጠፍቶ ወደ አጎቱ አገር ወደ መደባይ ወለል ሲሔድ ኃይለኛ ዝናብ ስለዘነበ ከአክሱም ከተማ ፬ (4) ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ክምትገኝ ማይከራኸ ከምትባል ምንጭ ውኃ አጠገብ ወደአለው ዛፍ ሥር ተጠግቶ መጠለል ግድ ሆነበት ፡፡ ዛፉን ተጠግቶ ደገፍ ብሎ አንደቆመ በምን ምክንያት በትምህርት ከጓደኞቹ በታች እንደሆነ ሊያስብና ሲያሰላስል ሲያዝንና ሲተክዝ ከቆየ በኋላ ፡ ሐሳቡን የሚያስለውጥ ነገር በድንገት ተመለከተ ፡፡ ይኸውም አንድ ጉንዳን አንድ የእህል ፍሬ ተሸክሞ ወደዛፍ ለመውጣት ከፍተኛ ሙከራ ሲያደርግ አየ። ጉንዳኑ የተሸከመውን ይዞ ስድስት ጊዜ ለመውጣት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ክብዙ ድካምና ጥረት በኋላ በሰባተኛወ ሙከራ የተሸከማትን የእህል ፍሬ ይዞ ወጣ ። በሙሉ አትኩሮት ይመለከተውና ይከታተለው የነበረው ያሬድም በድንገት ስሜቱ ተነካ ፡፡ ይህ አነስተኛ ፍጡር ከብዙ ጥረት በኋላ ያሰበውን ሲፈጽም የእኔ ተስፋ መቁረጥ ምን ይባላል ሲል ራሱን በራሱ ወቀሰ ከጉንዳኑ ያገኘው ትምህርት ልቡን ስለነካው ስሜቱንም ስለቀሰቀሰውና የጉንዳኑን ትጋትም አይቶ ስለ ተደነቀ በራሱ ደካማነት ተጸጽቶ አለቀሰ ፡፡ ያሬድ በዚሁ አነስተኛ ፍጡር ጥረትና ተስፋ አለመቁረጥ ተደንቆ ራሱን እንዲመረምር ስሜቱን ስለሎረኮረው ፥ ወደ አክሱም ተመልሶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ ። የሰው አፈጣጠር ከዚህ አነስተኛ ፍጥረት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ስለተገነዘበ ፡ ያጉቱን ምክርና ተግሣፅ ለሕይወቱ የሚጠቅም እንደሆነ በመረዳት ያለውንም ትምህርት በትጋት ቢማርና ቢያጠና የተሻለ ውጤት ሊያገኝ እንደሚችል በማመን ወደ አጉቱና ወደ መንፈሳዊ መምህሩ ወደ አባ ጌዴዎን ተመልሶ በመምጣት አባቴ ሆይ ይቅር በለኝና እንደ ቀድሞ አስተምረኝ ብሎ አጉቱ እግር ላይ ወደቀ፡፡ መምህሩ አባ ጌዴዎንም ፈቅደውለት ዳዊቱን ያስተምሩት ጀመር ። ሕፃኑ ያሬድም ትምህርቱን እየተማረ ሁልጊዜ በጽሞና ወደ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲ ያን እየገባ "መሖሪ እግዚአብሔር ዐይነ ልቦናየን አብራልኝ" እያለ በየቀኑ በንጹሕ ልቦና ይጸልይ ነበር ። መሐሪውና የቅር ባዩ እግዚአብሔር ርም ልመናውን ሰምቶ ዐይነ ልቦናውን አበራለትና ትምህርቱ ተገለጸለት። ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ከፍተኛና የማይታሰብ ለውጥ በማምጣቱ ጓደኞቹና መምህራኑ እጅግ በጣም ተደነቁ ፡፡ በዚህ ፈጣን የትምህርት መቀበል ችሎታ የብሉይ ኪዳንንና የአዲስ ኪዳንን ትርጓሜ መጻሕፍት በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨረሰ። ያሬድ ከፍተኛ የትምህርት ተሰጥዎ ያለው በመሆኑ ትምህርቱን በጣም አስደናቂ በሆነ መንገድ ፈጽሞ ዲያቆን ሆነ ፡፡ ከመምህሩ ከአባ ጌዴዎን በተማረው መሠረት የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ደህና አድርጉ ያውቅ ነበር ይባላል ፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስና እንዲሁም በውጭ አገር ቋንቋዎች የአጉቱን የመምህር ጌዴዎንን ሙያ አጠናቆ ቻለ ፡፡ ያሬድ አጉቱ ሲሞት የዐሥራ አራት አመት ልጅ ቢሆንም የአጉቱን ሙያና የትምህርት ወንበር ተረክቦ ማስተማር ጀመረ። በግንቦት ፲፩ (11) ቀን ስንክሳር በተባለው የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ "ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶና ተነሣሥቶ የዜማ ድርሰቶቹን አዘጋጀ" ይላል። በዚሁ ስንክሳር እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዚች ምድር እንዲመስገን በፈለገ ጊዜ ያሬድን በራሱ ቋንቋ ሰማያዊ ዜማ እንዲያስተምሩት በአእዋፍ አምሳል ሦስት መላእክትን ከገነት ላከለት ይላል ፥፡ እነሱም ያሬድ ካለበት ሥፍራ አንጻር ባለው አየር ላይ ረበው (አንዣብበው) ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ አዲስ ዜማ አሰሙት ፡፡ ያን ጊዜ ያሬድ በጣዕመ ዜማቸው ተመስጦ ቁሞ ሲያዳምጥ ወዲያውኑ ወፎቹ በግዕዝ ቋንቋ "ብጹዕ ወክቡር አንተ ያሬድ ብጽፅት ከርሥ አንተ ጾረተከ ውብጹዓት አጥባት አላ ሐአናከ" ብለው በአንድነት አመስግኑት። ትርጉሙ "የተመሰገንክና የተክበርክ ያሬድ ሆይ ፡ አንተን የተሸከመች ማኅፀን የተመስገነች ናት ፡፡ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸው" ብለው አመሰገኑት ፡፡ ከዚያም ሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ወደ ሚዘምሩበት ወጋ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አሳረጉት ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመንበረ ጸባዖት ፊጓ ቁሞ ከሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በፍጥነት የሰማው ማኀሌት ሁቦ በመንፈስ እግዚአብሔር ተገለጸለትና በልቦናው የተሣለበትን ጰዋትዜ ዜማ በቃሉ ያዜም ጀመር ፡፡ ከዚያም ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ አክሱም በተመለሰ ጊዜ ክጥዋቱ በ፫ ሰዓት ወደ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በታቦተ ጽዮን አንጻር ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፡ በከፍተኛ ድምፅ በአራራይ ዜማ ሃሌ ሉያ ለአብ ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፡ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቅዳሜሃ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘክመ ይገብር ግብራ ለደብተራ" ብሉ ሥነፍጥረቱንና ሰማያዊት ጽዮንን አሰመልክቶ ዘመረ ይህችንም ማኅሌት አርያም ብሎ ጠራት ዞ አርያምም ማለት ልዕልና ሰባተኛ ሰማይ መንበረ እግዚአብሔር ማለት ነው ፡፡ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ መላእክት እንደ ከበሮ እንቢልታ፣ ጸናጽል ፣ ማሲንቆና በገና በመሳሰሉት የማኅሌት መሣሪያዎች እየዘመሩ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ስለስማ እነዚህን መሣሪያዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ አደረጋቸው ፡፡ ምንጭ:- - "የኢትዮጵያ ሥልጣኔ"፣ በላይ ግደይ
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • የሚቀጥለው ግጥም የሃገርን ትርጉም በደምብ የሚገልጽ ይመስለኛል። ተጻፈ በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ።
    ---------------------
    ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
    እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣ የተወለድሽበት አፈር፤
    እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤
    ብቻ እንዳይመስልሽ።
    ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
    አገር ውስብስብ ነው ውሉ።

    ሀገር ማለት ልጄ ፣
    ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤
    ከማማ መህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤
    በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣
    በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤
    በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣
    በተሻገርሽው ዥረት ፤
    በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤
    በእውቀትሽና በህይወትሽ፣
    በእውነትሽና በስሜትሽ ፣
    የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤
    ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡
    ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው።

    ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣
    ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤
    በጆሮ አያዳምጡት፤
    አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤
    ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ።

    የኔ ልጅ፣
    አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣ ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤
    ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ።
    የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤
    ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡
    ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤
    ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ።

    የኔ ልጅ ፣
    አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣
    ሲያቀና ወረቱን፤
    ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤
    ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤
    ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . . ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣
    አጥንቱን እየማገረ፤
    ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣ ሲያቆይልሽ፤
    በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ!

    እና የእኔ ልጅ፣
    ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ የሚያስፈልግሽ፤
    ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤
    ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው እድገትሽ።
    እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበት አይናገሩት፤
    በጆሮ አያዳምጡት።

    ከሁሉም በላይ ልጄ ፣
    ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤
    ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ።
    ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤
    የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡
    ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ።

    መሬትማ የእኔ ልጅ፣
    በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤
    ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ ካልተመገብሽው፤
    መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤
    ለተስማማው የሚስማማ።
    ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል
    ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል።
    መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሃገርሽ፤
    ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ አፈር ሚያለብስሽ።
    በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤
    ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ።

    እና የኔ ልጅ፣
    ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
    ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።
    የሚቀጥለው ግጥም የሃገርን ትርጉም በደምብ የሚገልጽ ይመስለኛል። ተጻፈ በዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ። --------------------- ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣ እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ ፣ የተወለድሽበት አፈር፤ እትብትሽ የተቀበረበት ፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤ ብቻ እንዳይመስልሽ። ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤ አገር ውስብስብ ነው ውሉ። ሀገር ማለት ልጄ ፣ ሀገር ማለት ምስል ነው ፣በህሊና የምታኖሪው፤ ከማማ መህጸን ከወጣሽበት ቀን ጀምሮ ፤ በጠባሽው ጡት፣ ወይም ጡጦ ፣ በዳህሽበት ደጃፍ፣ በወደቅሽበት ፈፋ፤ በተማርሽበት ትምህርት ቤት፣ በተሻገርሽው ዥረት ፤ በተሳልሽበት ታቦት ፣ወይ በተማፀንሽው ከራማ ፤ በእውቀትሽና በህይወትሽ፣ በእውነትሽና በስሜትሽ ፣ የምትቀበይው ምስል ነው ፣ በህሊናሽ የምታኖሪው፤ ስትወጅ ሰንደቅ ታደርጊው፡፡ ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው። ሀገር ማለት የኔ ልጅ ፣ ሀገር ማለት ቋንቋ ነው በአንደበት አይናገሩት፤ በጆሮ አያዳምጡት፤ አማርኛ ኦሮሞኛ ፣ አፋርኛ ቅማንተኛ፤ ጉራግኛ ወይ ትግርኛ፣ ብለው የማይፈርጁት ። የኔ ልጅ፣ አማራውና አፋሩ፣ ኦሮሞው ሲዳማው ፣ ጉራጌኛሽን ባይሰማ፤ ያለገባው እንዳይመስልሽ ፣ ሀዘን ደስታሽን ያልተጋራ። የየልቦናችንን ሀቅ፣ ፍንትው አድርጎ እያሳየ፤ ህዝቦችን ከሰንደቃቸው፣ አስተሳስሮ ያቆየ፡፡ ሀገር ቋንቋ ነው ልጄ፣ የሁለንተናሽ መስታወት፤ ሲከፋሽ ትሽሽጊበት ፣ ሲደላሽ ትኳኳየዪበት ። የኔ ልጅ ፣ አያት ቅም አያትሽ ፣ሰላም ሲሆን ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ሸቅጦ፣ ሲያቀና ወረቱን፤ ለእኔና ለአንቺ መኖሪያ፣ ሲያቀና ቀዬና ቤቱን፤ ሀገር ጠላት ሲደፍራትም፣ ጦሩን ሰብቆ እየፎከረ፤ ከኦሮሞው ከትግሬው፣ ከአፋሩ ከወላይታው፣ . . . ከሁሉም የጦቢያ ልጆች ፣ አጥንቱን እየማገረ፤ ሀገር ይሉት መግባቢያ ፣ሰንደቅ ይሉት መለያ ፣ ሲያቆይልሽ፤ በጉራግኛ ማትገልጭው፣ በጎጥ የማትገድቢው፣ ስንት አለ ታሪክ መሰለሽ! እና የእኔ ልጅ፣ ለዚህ ነው ሀገር ይሉት ቋንቋ፣ ላንቺ የሚያስፈልግሽ፤ ከወልቂጤ አድማስ ማዶ፣ ለተሳሰረ ታሪክሽ፤ ከወልቂጤ አድማስ ማዶ ፣ ለተወጠነው እድገትሽ። እና ልብ በይ ልጄ ! ሀገር ማለት ቋንቋ ነው፣ ባንደበት አይናገሩት፤ በጆሮ አያዳምጡት። ከሁሉም በላይ ልጄ ፣ ተፈጥሮ ከቸረው በረከት ፣ የላቡን ፍሬ የሚበላ፤ ሀገር ማለት ወገን ነው፣ የእኔ የምትይው ከለላ። ትመኪበት ጥሪት፣ ትደምቂበት ብርሃንሽ፤ የሰብዕናሽ ግማሽ ውል ፣ወገን ነው ማሕተምሽ፡፡ ዜጋው ነው ልጄ ሀገርሽ። መሬትማ የእኔ ልጅ፣ በእምነትሽና እውቀትሽ፣ ከልለሽ ካላበጀሽው፤ ለእድገትሽ ውጥን ካልሆነ ፣ለተስፋሽ ካልተመገብሽው፤ መሬትማ ባዳ ነው፣ ላለማው የሚለማ፤ ለተስማማው የሚስማማ። ዥረቱም ግድ የለውም ፣ ቦይ ለማሰለት ይፈሳል ተራራውም ደንቆሮ ነው ፣ ለቦረቦረው ይበሳል። መሬቱ አደለም የኔ ልጅ፣ እድርተኛው ነው ሃገርሽ፤ ስትቸገሪ ታድጎ፣ ስትታመሚ አስታሞ፣ ስትሞቺ አፈር ሚያለብስሽ። በእጅሽ ያለ ብሩህ ጽጌ ፣ ሰው ነው ልጄ ሀገርሽ፤ ወገን ነው ልጄ ሀገርሽ። እና የኔ ልጅ፣ ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤ ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    2 Comments 0 Shares