በወርመራ ወረዳ ትናንት ምሽት ያገጠመ የመኪና አደጋ በ6 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡
ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ገደማ ከአዲስ አበባ ወደ አምቦ ሲጓዝ የነበረ የጭነት አይሱዙ ከአምቦ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ከነበረ ዶልፊን የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጋር ተጋጭቶ በሚኒባሱ ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች አንዱ ከባድ 5ቱ ተሳፋሪዎች ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡
ይህ አደጋ በወርመራ ወረዳ መድፈኛ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ያጋጠመ ሲሆን በዚሁ ስፍራ ትናንት ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ20 ደቂቃ በተመሳሳይ የጭነት አይሱዙና የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን ተጋጭተው ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል፡፡
ትናንት ከቀኑ 7 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ደግሞ የጭነት ኤንትሬ እና ቶዮታ ላንድ ክሩዘር መኪና ተጋጭተው 80 ሺህ ብር የተገመተ ንብረት ወድሟል በማለት የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ፖሊስ የመረጃ ባለሙያ ኢንስፔክተር አዲሱ አበራ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
በወልመራ መድፈኛ የተባለው ስፈራ ጠመዝማዛ በመሆኑ የትራፊክ አደጋ ይደጋገምበታል አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል፡፡
(ወንድሙ ኃይሉ)