የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ ሾመ።
ዶክተር ደብረፅዮን የምክር ቤቱ አባል ባለመሆናቸው በክልሉ ህገመንግስት መሰረት ርእሰ መስተዳድር ሆነው መሾም ስለማይችሉ ነው በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት የተሾሙት።
ሆኖም የክልሉን መንግስት ካቢኔ የመምራት እና የርእሰ መስተዳድሩን ሀላፊነት ተክተው መስራት እንደሚችሉ ተመልክቷል።
ዶክተር ደብረፅዮን በምክትል ርእሰ መስተዳደርነት በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ በስንብት ንግግራቸው አብረዋቸው የሰሩ የተለያዩ አካላትን አመስግነው፥ አሁን ከተሾመው አስተዳደር ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
ዶክተር ደብረፅዮን አዳዲስ የክልሉ መንግስት ካቢኔ አባላት ሹመትን ለምክር ቤቱ አቅርበው አስፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት፦
ዶክተር አዲስዓለም ባሌማ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የካቢኒ አባል
ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ዳንኤል አሰፋ የፋይናንስና እቅድ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ተክላይ ገብረመድህን የሰሜናዊ ምእራብ ትግራይዞን ዋና አስተዳዳሪ
አቶ ማሞ ገብረእግዚአብሄር የማዕከላዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።