ሁለቱ ተዋጊዎች ወደ ሙሉ ጦርነት እየገቡ ይመስላል። ቀጠናዊ ግጭት ሆኖ ሊቀጥል ይችላል ወይ የሚለው አሁንም እያነጋገረ ነው። እስራኤል ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ደቡባዊ ሊባኖስ ላይ ቦምብ ስታዘንብ ነበር። አሁን ደግሞ ‘ውስን፣ ዒላማውን እና ዓላማውን የለየ የእግረኛ ጦር ዘመቻ’ አካሄዳለው ብላለች። ባለፈው ዓርብ መሪው የተገደለበት ሄዝቦላህ አጣብቂኝ ውስጥ ይገኛል። ይሁንና አሁንም ሄዝቦላህ ተዳከመ እንጂ ጨርሶ አልተደመሰሰም። አሁንም ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ያስወነጭፋል። በርካታ ኮማንደሮቹ ተለቅመው የተገደሉበት ድርጅት አልሞት ባይ ተጋዳይ የሆነ ይመስላል።