• የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር ጥሩ መሻሻል መከሰቱን ገለፀዋል።
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር ጥሩ መሻሻል መከሰቱን ገለፀዋል።
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    ዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር መሻሻልን አሳይቷል
    የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የንግድ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከቻይና ጋር ጥሩ መሻሻል መከሰቱን ገለፀዋል።
    0 Comments 0 Shares
  • (ቢትወድድ መ. ብርሀኔ) በ2008 ዓ/ም ዳንሻ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምህር በርሀ የሚባል የሒሳብ አስተማሪያችን ነበር፡፡እናም ይሄ አስተማሪያችን በሒሳብ ጥሩ ውጤት እንዲኖረን ከመደበኛ ክላስ ውጭ ሁሌም ሀሙስ ሀሙስ ያስተምረን ነበር፡፡ ግዜው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ አማራነቱን የሚያሳይበት ግዜ ስለነበር ለምን አማራ ነኝ ብለህ ለስብሰባ ጎንደር ሄድክ በሚል ሰበብ ሊላይ ብርሃኔን ባፈኑት ግዜ [...]
    (ቢትወድድ መ. ብርሀኔ) በ2008 ዓ/ም ዳንሻ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምህር በርሀ የሚባል የሒሳብ አስተማሪያችን ነበር፡፡እናም ይሄ አስተማሪያችን በሒሳብ ጥሩ ውጤት እንዲኖረን ከመደበኛ ክላስ ውጭ ሁሌም ሀሙስ ሀሙስ ያስተምረን ነበር፡፡ ግዜው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ አማራነቱን የሚያሳይበት ግዜ ስለነበር ለምን አማራ ነኝ ብለህ ለስብሰባ ጎንደር ሄድክ በሚል ሰበብ ሊላይ ብርሃኔን ባፈኑት ግዜ [...]
    KALITIPRESS.COM
    አፓርታይድ በወልቃይት ምድር
    (ቢትወድድ መ. ብርሀኔ) በ2008 ዓ/ም ዳንሻ የ11ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ግዜ አንድ መምህር በርሀ የሚባል የሒሳብ አስተማሪያችን ነበር፡፡እናም ይሄ አስተማሪያችን በሒሳብ ጥሩ ውጤት እንዲኖረን ከመደበኛ ክላስ ውጭ ሁሌም ሀሙስ ሀሙስ ያስተምረን ነበር፡፡ ግዜው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ባገኘው አጋጣሚ አማራነቱን የሚያሳይበት ግዜ ስለነበር ለምን አማራ ነኝ ብለህ ለስብሰባ ጎንደር ሄድክ በሚል ሰበብ ሊላይ ብርሃኔን ባፈኑት ግዜ የዳንሻ ከተማ ህዝብ ከልጅ እስከ አዋቂ
    0 Comments 0 Shares
  •  ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ነው የተባሉት ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የውጪ ብድር መጠን እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፤ የኢትዮጵያና የዛምቢያ የውጪ እዳ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራትን የውጪ ብድር አወሳሰድና የእዳ ምጣኔ የሚዳስሰውና ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የማስጠንቀቂያ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ቀደም ሲል በሃካከለኛ ደረጃ ላይ የነበረው የኢትዮጵያና የዛምቢያ የውጪ እዳ መጠን፣ አሁን በከፍተኛ ደረጃ አስጊ ሆኗል ብሏል። ተቋሙ ቻድ፣ ኤርትራ፣ ሞዛምቢክ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳንና ዚምባቡዌ በእዳ አዙሪት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውንም ጠቁሟል - በሪፖርቱ። የኢትዮጵያ የውጭ እዳ መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት አንፃር የ56.2 በመቶ ድርሻ መያዙን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ይህም ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረው የእዳ ምጣኔ በ2.2 በመቶ መጨመሩን ያመለክታል ብሏል፡፡ ሀገሪቱ ከ2016 አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቷ አንፃር የእዳ ምጣኔዋ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 56 በመቶ ደርሶ ነበር፤ ጫናው ቀጥሎ ገና በ2018 ሩብ ዓመት ላይ 56.2 በመቶ መድረሱ አሳሳቢ ነው ብሏል - ሪፖርቱ፡፡ የእዳ መጠኑ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ አኳኋን እየጨመረ የመጣው በፍጥነት በማደግ ላይ ያለውን የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስቀጠል ሲባል፣ በብድር አዙሪት ውስጥ በመግባቷ ነው ተብሏል፡፡ ሃገሪቱ ኢኮኖሚዋን የውጪ ብድር ላይ ከማንጠልጠል ወጥታ የሃገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን በማዘመንና በማሳደግ፣ ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ማድረግ እንዳለባት ተቋሙ አሳስቧል፡፡ ኢትዮጵያ የውጪ እዳ ጫናዋ በአስጊ ሁኔታ እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር ለመሰረታዊ ፍጆታ የሚውሉ የአገር ውስጥ ሸቀጦች ዋጋም ከህብረተሰቡ የመግዛት አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ ተጠቁሟል። የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረበት 6.7 በመቶ በአሁኑ ወቅት በእጥፍ ጨምሮ፣ ወደ 13.6 በመቶ ማደጉ ተጠቁሟል፡፡ኢትዮጵያን ጨምሮ 40 በመቶ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የውጭ እዳ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ የጠቆመው አይኤምኤፍ፤ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ አገግሞ ለመውጣት በእጅጉ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ብሏል፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት የአፍሪካ ሃገራት የውጭ እዳ መጠን በአርባ በመቶ መጨመሩም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
     ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ነው የተባሉት ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የውጪ ብድር መጠን እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ)፤ የኢትዮጵያና የዛምቢያ የውጪ እዳ መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራትን የውጪ ብድር አወሳሰድና የእዳ ምጣኔ የሚዳስሰውና ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የማስጠንቀቂያ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ቀደም ሲል በሃካከለኛ ደረጃ ላይ የነበረው የኢትዮጵያና የዛምቢያ የውጪ እዳ መጠን፣ አሁን በከፍተኛ ደረጃ አስጊ ሆኗል ብሏል። ተቋሙ ቻድ፣ ኤርትራ፣ ሞዛምቢክ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ ሱዳንና ዚምባቡዌ በእዳ አዙሪት ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውንም ጠቁሟል - በሪፖርቱ። የኢትዮጵያ የውጭ እዳ መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት አንፃር የ56.2 በመቶ ድርሻ መያዙን የጠቆመው ሪፖርቱ፤ ይህም ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረው የእዳ ምጣኔ በ2.2 በመቶ መጨመሩን ያመለክታል ብሏል፡፡ ሀገሪቱ ከ2016 አጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርቷ አንፃር የእዳ ምጣኔዋ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 56 በመቶ ደርሶ ነበር፤ ጫናው ቀጥሎ ገና በ2018 ሩብ ዓመት ላይ 56.2 በመቶ መድረሱ አሳሳቢ ነው ብሏል - ሪፖርቱ፡፡ የእዳ መጠኑ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ አኳኋን እየጨመረ የመጣው በፍጥነት በማደግ ላይ ያለውን የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማስቀጠል ሲባል፣ በብድር አዙሪት ውስጥ በመግባቷ ነው ተብሏል፡፡ ሃገሪቱ ኢኮኖሚዋን የውጪ ብድር ላይ ከማንጠልጠል ወጥታ የሃገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን በማዘመንና በማሳደግ፣ ችግሩን ለመቋቋም ጥረት ማድረግ እንዳለባት ተቋሙ አሳስቧል፡፡ ኢትዮጵያ የውጪ እዳ ጫናዋ በአስጊ ሁኔታ እየጨመረ ከመምጣቱ ባሻገር ለመሰረታዊ ፍጆታ የሚውሉ የአገር ውስጥ ሸቀጦች ዋጋም ከህብረተሰቡ የመግዛት አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ ተጠቁሟል። የሸቀጦች ዋጋ ግሽበት ከሁለት ዓመት በፊት ከነበረበት 6.7 በመቶ በአሁኑ ወቅት በእጥፍ ጨምሮ፣ ወደ 13.6 በመቶ ማደጉ ተጠቁሟል፡፡ኢትዮጵያን ጨምሮ 40 በመቶ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሃገራት፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ የውጭ እዳ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ የጠቆመው አይኤምኤፍ፤ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ አገግሞ ለመውጣት በእጅጉ ዋጋ ያስከፍላቸዋል ብሏል፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት የአፍሪካ ሃገራት የውጭ እዳ መጠን በአርባ በመቶ መጨመሩም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡
    ADDISADMASSNEWS.COM
    የኢትዮጵያ የውጪ እዳ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተባለ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news
    <p style="text-align: justify;"> ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ነው የተባሉት ከሰሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የውጪ ብድር መጠን እየጨመረ መምጣቱን ያስታወቀው ዓለም አቀፉ የገንዘብ...
    0 Comments 0 Shares
  • አስክሬናቸው ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ ይደርሳል        ታዋቂው የጋዜጠኝነት እና የፊልም ጥበብ ምሁሩ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በ83 ዓመታቸው ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት አሜሪካን ሃገር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን አስክሬናቸው ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ ደርሶ የቀብር ስነ ስርዓታቸውም የቤተሰባቸው መካነ መቃብር በሚገኝበት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል ተብሏል፡፡የአፄ ኃይለ ሥላሴን የ25ኛ ዓመት የዘውድ በዓል ለማክበር ከካሪቢያን መጥተው እዚሁ ኢትዮጵያ ኑሮአቸውን ከመሰረቱት የፎርድ ቤተሰቦች እ.ኤ.አ መጋቢት 5 ቀን 1935 አዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እናታቸው ሚስ ፎርድ ባሰሩትና ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው “ሚስ ፎርድ የአፀደ ህፃናትና የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት” የተማሩ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገ/ማሪያም ተከታትለዋል። አብይ ፎርድ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሜሪካ በፓኔ ውድስ ጁኒየር ኮሌጅ በአንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት” የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አብይ ፎርድ፤ በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በ“ፊልም ጥናት” ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በፊልምና ተያያዥ የትምህርት መስኮች ለ33 ዓመታት በመምህርነት ከአገለገሉ በኋላ ከዝነኛው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም ለረጅም ዓመታት በኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት የጋዜጠኝነት እና የፊልም አሰራር ስነ ጥበብ ትምህርት አስተምረዋል፡፡ ከ26 በላይ ዶክመንተሪ ፊልሞችም ሰርተዋል - ፕሮፌሰሩ፡፡ከፊልም እና ጋዜጠኝነት አስተማሪነታቸው ባሻገር በአሜሪካ አየር ኃይል ኤሮ አክቲቪቲ በፓይለትነት አገልግለዋል፡፡ የዘርፈ ብዙ ሙያዎች ባለቤት የነበሩት ፕሮፌሰሩ፤ ከሙዚቃ መሳሪዎች ጊታር፣ ሳክስፎንና ፒያኖ አሳምረው በመጫወት ይታወቃሉ፡፡ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎች አቀላጥፈው ይናገሩ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ ከኖሩበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ድህረ ምረቃ (የሁለተኛ ዲግሪ) ትምህርት መርሃ ግብር እንዲጀመር አስተዋፅኦ ከማበርከታቸው በተጨማሪ የትምህርት ክፍሉ ዲን በመሆንም አገልግለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የፊልም ጥናት ትምህርት ክፍል ለመክፈት ጥናት ያደረገው ግብረ ኃይል አማካሪም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ አፍቃሪ የነበሩት የፕሮፌሰሩ ወላጆች እዚሁ ኖረው፣ ህይወታቸው ሲያልፍም፣ እዚሁ ነው ያረፉት፡፡ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ ባቀኑበት አጋጣሚ ህይወታቸው ቢያልፍም አስክሬናቸው ወደዚህ መጥቶ ቀብራቸው አዲስ አበባ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይ ወንድማቸው ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ፎርድ በአሜሪካ ህይወታቸው ቢያልፍም ቀብራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈፅሟል፡፡ ከፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ጋር የቀረበ ወዳጅነት የነበራቸው የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ፤ “ፕሮፌሰሩ ባለ ልዩ ተሰጥኦና ባለ ብሩህ አዕምሮ ተመራማሪ ነበሩ” ይላሉ፡፡ “ለኢትዮጵያ ሚዲያ ልዕልና የታገሉ ምሁር ናቸው” ያሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ “እስከ መጨረሻው የነበራቸው እምነትም የሃገሪቱ ሚዲያዎች አራተኛ የመንግስት አካልነታቸውን ሚና ጠንክረው መወጣት አለባቸው” የሚል ነበር ይላሉ፡፡ ለሃገሪቱ የሚዲያ ምህዳር መሻሻልም ቀናኢ የሆኑ ሙግቶችን የሚያቀርቡ የሚዲያው ጠበቃ ነበሩ ይላሉ - ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፡፡ 
    አስክሬናቸው ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ ይደርሳል        ታዋቂው የጋዜጠኝነት እና የፊልም ጥበብ ምሁሩ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በ83 ዓመታቸው ህክምናቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት አሜሪካን ሃገር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን አስክሬናቸው ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ ደርሶ የቀብር ስነ ስርዓታቸውም የቤተሰባቸው መካነ መቃብር በሚገኝበት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ይፈፀማል ተብሏል፡፡የአፄ ኃይለ ሥላሴን የ25ኛ ዓመት የዘውድ በዓል ለማክበር ከካሪቢያን መጥተው እዚሁ ኢትዮጵያ ኑሮአቸውን ከመሰረቱት የፎርድ ቤተሰቦች እ.ኤ.አ መጋቢት 5 ቀን 1935 አዲስ አበባ ውስጥ የተወለዱት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እናታቸው ሚስ ፎርድ ባሰሩትና ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው “ሚስ ፎርድ የአፀደ ህፃናትና የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት” የተማሩ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገ/ማሪያም ተከታትለዋል። አብይ ፎርድ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሜሪካ በፓኔ ውድስ ጁኒየር ኮሌጅ በአንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት” የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አብይ ፎርድ፤ በአሜሪካ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በ“ፊልም ጥናት” ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በፊልምና ተያያዥ የትምህርት መስኮች ለ33 ዓመታት በመምህርነት ከአገለገሉ በኋላ ከዝነኛው ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰነት ማዕረግ አግኝተዋል፡፡ በሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም ለረጅም ዓመታት በኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት የጋዜጠኝነት እና የፊልም አሰራር ስነ ጥበብ ትምህርት አስተምረዋል፡፡ ከ26 በላይ ዶክመንተሪ ፊልሞችም ሰርተዋል - ፕሮፌሰሩ፡፡ከፊልም እና ጋዜጠኝነት አስተማሪነታቸው ባሻገር በአሜሪካ አየር ኃይል ኤሮ አክቲቪቲ በፓይለትነት አገልግለዋል፡፡ የዘርፈ ብዙ ሙያዎች ባለቤት የነበሩት ፕሮፌሰሩ፤ ከሙዚቃ መሳሪዎች ጊታር፣ ሳክስፎንና ፒያኖ አሳምረው በመጫወት ይታወቃሉ፡፡ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎች አቀላጥፈው ይናገሩ ነበር፡፡ ለረጅም ጊዜ ከኖሩበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ድህረ ምረቃ (የሁለተኛ ዲግሪ) ትምህርት መርሃ ግብር እንዲጀመር አስተዋፅኦ ከማበርከታቸው በተጨማሪ የትምህርት ክፍሉ ዲን በመሆንም አገልግለዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የፊልም ጥናት ትምህርት ክፍል ለመክፈት ጥናት ያደረገው ግብረ ኃይል አማካሪም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ አፍቃሪ የነበሩት የፕሮፌሰሩ ወላጆች እዚሁ ኖረው፣ ህይወታቸው ሲያልፍም፣ እዚሁ ነው ያረፉት፡፡ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ ባቀኑበት አጋጣሚ ህይወታቸው ቢያልፍም አስክሬናቸው ወደዚህ መጥቶ ቀብራቸው አዲስ አበባ ተፈፅሟል፡፡ በተመሳሳይ ወንድማቸው ዮሴፍ ኃይለሥላሴ ፎርድ በአሜሪካ ህይወታቸው ቢያልፍም ቀብራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈፅሟል፡፡ ከፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ጋር የቀረበ ወዳጅነት የነበራቸው የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ፤ “ፕሮፌሰሩ ባለ ልዩ ተሰጥኦና ባለ ብሩህ አዕምሮ ተመራማሪ ነበሩ” ይላሉ፡፡ “ለኢትዮጵያ ሚዲያ ልዕልና የታገሉ ምሁር ናቸው” ያሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ “እስከ መጨረሻው የነበራቸው እምነትም የሃገሪቱ ሚዲያዎች አራተኛ የመንግስት አካልነታቸውን ሚና ጠንክረው መወጣት አለባቸው” የሚል ነበር ይላሉ፡፡ ለሃገሪቱ የሚዲያ ምህዳር መሻሻልም ቀናኢ የሆኑ ሙግቶችን የሚያቀርቡ የሚዲያው ጠበቃ ነበሩ ይላሉ - ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፡፡ 
    ADDISADMASSNEWS.COM
    ፕ/ር አብይ ፎርድ (ከ1927-2010 ዓ.ም) - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news
    <p style="text-align: justify;">አስክሬናቸው ረቡዕ ጠዋት አዲስ አበባ ይደርሳል<br /> <br /> ታዋቂው የጋዜጠኝነት እና የፊልም ጥበብ ምሁሩ ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በ83...
    0 Comments 0 Shares
  • የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ታዋቂውን የልብ ሃኪምና የአዲስ የልብ ህክምና ማዕከል ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ትናንት ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ በፍ/ቤት ከተበየነባቸው 38 ተከሳሾች መካከል 26ቱ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ በእነ ማስረሻ ሰጠኝ የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙት 38 ተከሳሾች መካከል አራቱ በሰው መግደል ወንጀል የተከሰሱ በመሆኑ ክሳቸው ባለበት እንዲቀጥል የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል ስምንቱ ያህሉ በነፃ መሰናበታቸው ታውቋል፡፡ ቀሪዎቹ ክሳቸው የተቋረጠላቸው በተለያዩ የሽብር ወንጀሎች ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡  
    የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ታዋቂውን የልብ ሃኪምና የአዲስ የልብ ህክምና ማዕከል ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ትናንት ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ በፍ/ቤት ከተበየነባቸው 38 ተከሳሾች መካከል 26ቱ ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ በእነ ማስረሻ ሰጠኝ የክስ መዝገብ ስር ከሚገኙት 38 ተከሳሾች መካከል አራቱ በሰው መግደል ወንጀል የተከሰሱ በመሆኑ ክሳቸው ባለበት እንዲቀጥል የተባለ ሲሆን ቀደም ሲል ስምንቱ ያህሉ በነፃ መሰናበታቸው ታውቋል፡፡ ቀሪዎቹ ክሳቸው የተቋረጠላቸው በተለያዩ የሽብር ወንጀሎች ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው ሲከታተሉ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡  
    ADDISADMASSNEWS.COM
    ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ተቋረጠ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news
    <p style="text-align: justify;">የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ታዋቂውን የልብ ሃኪምና የአዲስ የልብ ህክምና ማዕከል ባለቤት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ የ62 ተከሳሾች ክስ ትናንት ማቋረጡን አስታወቀ...
    0 Comments 0 Shares
  • በሱዳን የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 1400 ያህል ኢትዮጵያውያን ከእስር የተለቀቁ ሲሆን በኪንያ እስር ቤቶች የሚገኙ 1600 እስረኞችም እንደተፈቱ ታውቋል፡፡በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ በሱዳንና በኬንያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት፣ ከሃገራቱ መሪዎች ጋር በትኩረት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች አንዱ በሃገራቱ ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ሲሆን እስረኞቹ እንዲፈቱ መወሰኑም ይታወቃል፡፡ባለፈው ሐሙስ ግንቦት 2 የሱዳን መንግስት፣ በሃገሪቱ ኢትዮጵያውያን በብዛት ታስረው የሚገኙበት ጅድ አልሁዳ እስር ቤት ጨምሮ ከተለያዩ ወህኒ ቤቶች 1400 ያህል እስረኞችን ፈትቷል፡፡በሱዳን በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብዛት 3 ሺህ እንደሚገመት የጠቆሙት ምንጮች፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሱዳን እስር ቤቶች ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ግብፃውያንና ኤርትራውያን እስረኞች እንደሚገኙ የሚናገሩት ምንጮች፤ ኤርትራውያን ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል፡፡ ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን የሱዳንን ህግና ስርአትን አክብረው በሃገሪቱ መኖርና መስራት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ በተመሣሣይ በኬንያ በእስር ላይ የነበሩ 1600 ያህል ኢትዮጵያውያን የተፈቱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው፣ በሃገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ መጠየቃቸው ተጠቁሟል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለተመሳሳይ አላማዎች በተለያዩ ሃገራት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ባለፈው አንድ ወር በሃገር ውስጥ እና በጎረቤት ሃገራት በርካታ ጉብኝቶችን ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከትናንት በስቲያ ለ48 ባለስልጣናት የሚኒስትር ዴኤታነትና ሌሎች ሹመቶችን መስጠታቸው ታውቋል፡፡
    በሱዳን የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 1400 ያህል ኢትዮጵያውያን ከእስር የተለቀቁ ሲሆን በኪንያ እስር ቤቶች የሚገኙ 1600 እስረኞችም እንደተፈቱ ታውቋል፡፡በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፤ በሱዳንና በኬንያ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት፣ ከሃገራቱ መሪዎች ጋር በትኩረት ከተወያዩባቸው ጉዳዮች አንዱ በሃገራቱ ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የሚመለከት ሲሆን እስረኞቹ እንዲፈቱ መወሰኑም ይታወቃል፡፡ባለፈው ሐሙስ ግንቦት 2 የሱዳን መንግስት፣ በሃገሪቱ ኢትዮጵያውያን በብዛት ታስረው የሚገኙበት ጅድ አልሁዳ እስር ቤት ጨምሮ ከተለያዩ ወህኒ ቤቶች 1400 ያህል እስረኞችን ፈትቷል፡፡በሱዳን በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብዛት 3 ሺህ እንደሚገመት የጠቆሙት ምንጮች፤ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በሱዳን እስር ቤቶች ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ግብፃውያንና ኤርትራውያን እስረኞች እንደሚገኙ የሚናገሩት ምንጮች፤ ኤርትራውያን ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ ብለዋል፡፡ ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን የሱዳንን ህግና ስርአትን አክብረው በሃገሪቱ መኖርና መስራት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡ በተመሣሣይ በኬንያ በእስር ላይ የነበሩ 1600 ያህል ኢትዮጵያውያን የተፈቱ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው፣ በሃገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ መጠየቃቸው ተጠቁሟል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለተመሳሳይ አላማዎች በተለያዩ ሃገራት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ባለፈው አንድ ወር በሃገር ውስጥ እና በጎረቤት ሃገራት በርካታ ጉብኝቶችን ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከትናንት በስቲያ ለ48 ባለስልጣናት የሚኒስትር ዴኤታነትና ሌሎች ሹመቶችን መስጠታቸው ታውቋል፡፡
    ADDISADMASSNEWS.COM
    በሱዳንና በኬንያ 3 ሺ ያህል ኢትዮጵያውያን እስረኞች ተለቀቁ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news
    <p style="text-align: justify;">በሱዳን የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የነበሩ 1400 ያህል ኢትዮጵያውያን ከእስር የተለቀቁ ሲሆን በኪንያ እስር ቤቶች የሚገኙ 1600 እስረኞችም እንደተፈቱ ታውቋ...
    0 Comments 0 Shares
  •             በ14 ዓመቱ ታዳጊ ላይ የብልት መሰለብና የአካል ጉዳት ያደረሰበት ተጠርጣሪ አልተገኘም          ታዳጊው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ይመጣል                 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን፣ ድባጤ ወረዳ፣ ዝግህ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ በካር ወንዝ በተባለ ቦታ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበረው የ14 ዓመት ታዳጊ አበጠር ወርቁን ብልት በመስለብ ጥቃት ያደረሰበት ተጠርጣሪ እየተፈለገ ነው። የድባጤ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ንጋቱ ኢተፋ፤ ጉዳዩ ገና በምርመራ ላይ መሆኑንና ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከቀኑ ከ7፡00 እስከ 8፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በካር በተሰኘው አካባቢ ታዳጊው ከብት ሲጠብቅ በነበረበት ወቅት አንድ ጫት በመቃም ላይ የነበረ ሰው አጠገቡ ሆኖ ለረዥም ሰዓት ሲያጫውተው እንደቆየና በድንገት ማጅራቱን ከመታው በኋላ ወድቆ ራሱን መሳቱን እንደነገራቸው የታዳጊው አጎት አቶ አያሌው አበረ ገልፀዋል፡፡ በአካባቢው ልማድ መሰረት የሰፈሩ ከብቶች የሚጠበቁት በተራ እንደሆነ የጠቆሙት የተጎጂው አጎት፤ በዕለቱም የከብት ጥበቃ ተራው የታዳጊው አባት እንደነበረና አበጠርም የአካባቢውን ከብቶች በመጠበቅ ላይ እንዳለ ጥቃቱ እንደደረሰበት ተናግረዋል፡፡ የፓዌ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ በየነ በታዳጊው ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠን ጠይቀናቸው ሲመልሱ፤ ህፃኑ ወደ ሆስፒታሉ ሲመጣ ብልቱ ተቆርጦ ፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶና የመንጋጋ ስብራት ደርሶበት እንደነበር አስታውሰው፤ ለሶስት ቀናት በሆስፒታሉ ህክምና ቢደረግለትም በሆስፒታሉ ያለው ራጅ ብቻ በመሆኑና በሲቲ ስካን የጭንቅላቱ ሁኔታ መታዬት ስለነበረበት ወደ አንጎሉ ደም እንዳይፈስ በመስጋት ባህርዳር ወደሚገኘው ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ለተሻለ ህክምና እንደሄደ ነግረውናል፡፡ የጉዳቱን መጠን በተመለከተም “ብልት ተቆርጦ ሲሄድ አንድ አካልን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው፤ ፊቱም ላይ የደረሰው አደጋ ቀላል አይደለም” ያሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፤ ሲቲ ስካን ተነስቶና ሙሉ ምርመራ ተደርጎ የሚገኘው ውጤት ነው በህክምና ሙያ በዋናነት የጉዳቱን መጠን የሚገልፀው ብለዋል፡፡ ታዳጊው በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ በኩል አስፈላጊው ምርመራና ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የልጁን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙት በባህር ዳር ዩኒርቨሲቲ ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ገልፀውልናል፡፡የ14 ዓመቱ አበጠር ወርቁ ለእናቱ የመጀመሪያ ለአባቱ ሶስተኛ ልጅ እንደሆነ የገለፁት አጎቱ አቶ አያሌው አበረ፤ ምንም የማያውቅ ልጅ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ጥቃት ሲደርስበት የወረዳው ፖሊስ የተወሰኑ ሰዎችን እያሰረ ከመፍታት ውጭ የተጠናከረ ምርመራ እያደረገና ትኩረት እየሰጠ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው ገልፀው ጉዳዩ በመንግስት ደረጃ ትኩረት አግኝቶ ህፃኑ ፍትህ እንዲያገኝና አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡ በፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለልጁ ህክምናና ክትትል እያደረጉ የሚገኙት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት የቀዶ ህክምና ተማሪ ዶ/ር ሲሳይ ሙሉቀን በበኩላቸው፤ ህፃኑ የብልት መቆረጥ የጭንቅላትና የአይን ጉዳት እንዲሁም የጥርስ መውለቅና ተደራራቢ ጉዳቶች የደረሰበትና በስለት ፊቱ የተቆረጠ በመሆኑ የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ በአፉና በአንገቱ አካባቢ ኢንፌክሽን የተፈጠረ በመሆኑ የአንቲ ባዮቲክ ህክምና እየተደረገለት ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሲሳይ አክለውም፤ ልጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየነቃ መሄዱን፣ በአተነፋፈሱ በኩል ትንሽ ችግር ስለገጠመው በኦክስጅን ታግዞ እየተነፈሰ መሆኑን ጠቁመው፤ ብልቱ ላይ ካቲተር ተገጥሞለት ህክምናው ቀጥሏል ብለዋል፡፡ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የታዳጊውን ሙሉ ወጪ ሸፍነው ለማሳከም ቃል የገቡ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ህፃኑ ጳውሎስ ሆስፒታል መጥቶ እንዲታከምና ወጪውን ሚኒስቴሩ እንደሚሸፍን መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
                በ14 ዓመቱ ታዳጊ ላይ የብልት መሰለብና የአካል ጉዳት ያደረሰበት ተጠርጣሪ አልተገኘም          ታዳጊው ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ይመጣል                 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን፣ ድባጤ ወረዳ፣ ዝግህ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ በካር ወንዝ በተባለ ቦታ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበረው የ14 ዓመት ታዳጊ አበጠር ወርቁን ብልት በመስለብ ጥቃት ያደረሰበት ተጠርጣሪ እየተፈለገ ነው። የድባጤ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ንጋቱ ኢተፋ፤ ጉዳዩ ገና በምርመራ ላይ መሆኑንና ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም በግምት ከቀኑ ከ7፡00 እስከ 8፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በካር በተሰኘው አካባቢ ታዳጊው ከብት ሲጠብቅ በነበረበት ወቅት አንድ ጫት በመቃም ላይ የነበረ ሰው አጠገቡ ሆኖ ለረዥም ሰዓት ሲያጫውተው እንደቆየና በድንገት ማጅራቱን ከመታው በኋላ ወድቆ ራሱን መሳቱን እንደነገራቸው የታዳጊው አጎት አቶ አያሌው አበረ ገልፀዋል፡፡ በአካባቢው ልማድ መሰረት የሰፈሩ ከብቶች የሚጠበቁት በተራ እንደሆነ የጠቆሙት የተጎጂው አጎት፤ በዕለቱም የከብት ጥበቃ ተራው የታዳጊው አባት እንደነበረና አበጠርም የአካባቢውን ከብቶች በመጠበቅ ላይ እንዳለ ጥቃቱ እንደደረሰበት ተናግረዋል፡፡ የፓዌ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ በየነ በታዳጊው ላይ ስለደረሰው የጉዳት መጠን ጠይቀናቸው ሲመልሱ፤ ህፃኑ ወደ ሆስፒታሉ ሲመጣ ብልቱ ተቆርጦ ፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶና የመንጋጋ ስብራት ደርሶበት እንደነበር አስታውሰው፤ ለሶስት ቀናት በሆስፒታሉ ህክምና ቢደረግለትም በሆስፒታሉ ያለው ራጅ ብቻ በመሆኑና በሲቲ ስካን የጭንቅላቱ ሁኔታ መታዬት ስለነበረበት ወደ አንጎሉ ደም እንዳይፈስ በመስጋት ባህርዳር ወደሚገኘው ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ለተሻለ ህክምና እንደሄደ ነግረውናል፡፡ የጉዳቱን መጠን በተመለከተም “ብልት ተቆርጦ ሲሄድ አንድ አካልን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው፤ ፊቱም ላይ የደረሰው አደጋ ቀላል አይደለም” ያሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፤ ሲቲ ስካን ተነስቶና ሙሉ ምርመራ ተደርጎ የሚገኘው ውጤት ነው በህክምና ሙያ በዋናነት የጉዳቱን መጠን የሚገልፀው ብለዋል፡፡ ታዳጊው በአሁኑ ሰዓት በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ በኩል አስፈላጊው ምርመራና ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የልጁን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተሉ የሚገኙት በባህር ዳር ዩኒርቨሲቲ ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ገልፀውልናል፡፡የ14 ዓመቱ አበጠር ወርቁ ለእናቱ የመጀመሪያ ለአባቱ ሶስተኛ ልጅ እንደሆነ የገለፁት አጎቱ አቶ አያሌው አበረ፤ ምንም የማያውቅ ልጅ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ጥቃት ሲደርስበት የወረዳው ፖሊስ የተወሰኑ ሰዎችን እያሰረ ከመፍታት ውጭ የተጠናከረ ምርመራ እያደረገና ትኩረት እየሰጠ አለመሆኑ እንዳሳዘናቸው ገልፀው ጉዳዩ በመንግስት ደረጃ ትኩረት አግኝቶ ህፃኑ ፍትህ እንዲያገኝና አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡ በፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለልጁ ህክምናና ክትትል እያደረጉ የሚገኙት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት የቀዶ ህክምና ተማሪ ዶ/ር ሲሳይ ሙሉቀን በበኩላቸው፤ ህፃኑ የብልት መቆረጥ የጭንቅላትና የአይን ጉዳት እንዲሁም የጥርስ መውለቅና ተደራራቢ ጉዳቶች የደረሰበትና በስለት ፊቱ የተቆረጠ በመሆኑ የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ በአፉና በአንገቱ አካባቢ ኢንፌክሽን የተፈጠረ በመሆኑ የአንቲ ባዮቲክ ህክምና እየተደረገለት ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር ሲሳይ አክለውም፤ ልጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየነቃ መሄዱን፣ በአተነፋፈሱ በኩል ትንሽ ችግር ስለገጠመው በኦክስጅን ታግዞ እየተነፈሰ መሆኑን ጠቁመው፤ ብልቱ ላይ ካቲተር ተገጥሞለት ህክምናው ቀጥሏል ብለዋል፡፡ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የታዳጊውን ሙሉ ወጪ ሸፍነው ለማሳከም ቃል የገቡ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ህፃኑ ጳውሎስ ሆስፒታል መጥቶ እንዲታከምና ወጪውን ሚኒስቴሩ እንደሚሸፍን መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • “ሥራ አስኪያጁ ለማምለጥ ሞክረው ነበር”    ባለፈው ረቡዕ በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ህንዳዊው ዲፒ ካማራ ገዳዮች እየተፈለጉ ሲሆን ሥራ አስኪያጁ ከገዳዮቹ ለማምለጥ ሞክረው እንደነበር ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ በኢትዮጵያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሽያጭ ገበያ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ታሪኩ ዓለማየሁን ማነጋገሩን የጠቆመው ብሉምበርግ፤ የሥራ አስኪያጁ፣ ፀሐፊያቸውና ሹፌራቸው ግድያ የተፈፀመው ፋብሪካው አጠገብ መሆኑን እንደገለፁለት ዘግቧል፡፡ በናይጀሪያ ሌጎስ የሚገኙት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዳይሬክተር ኢድዊን ዲቫኩማር በኢሜይል ለብሉምበርግ እንደገለፁትም፤ ሥራ አስኪያጁ ግድያው ሲፈፀምባቸው ሮጠው ለማምለጥ ሙከራ አድርገው ነበር፤ ገዳዮቹ የመኪናውን አሽከርካሪ በድንጋይ መተው አቅጣጫውን እንዲስት ባደረጉበት ወቅት ሥራ አስኪያጁ ከመኪናው ላይ ወርደው ሮጠው ለማምለጥ ሲሞክሩ ገዳዮቹ እግራቸውን በጥይት መተው ከጠሏቸው በኋላ በተደጋጋሚ ተኩሰው እንደገደሏቸው ገልፀዋል፡፡ ገዳዮቹ ሶስቱን ሟቾች በ15 ያህል ጥይቶች ደብድበው መግደላቸውን ቢቢሲ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የሥራ አስኪያጁ አስክሬን ወደ አገራቸው የተላከ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግለሠቦቹ ገዳዮች በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ያገኛሉ ብለዋል፡፡የህንድ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የናይጄሪያዊ ቢሊየነር ንብረት የሆነውን ዳንጎቴ ሲሚንቶን ከአንድ አመት ተኩል በላይ ሲያስተዳድሩ የቆዩትና ባለፈው ረቡዕ አመሻሽ ላይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ደፒ ካማራ አስክሬን ከትናንት በስቲያ ለቀብር  ወደ ሃገራቸው ህንድ ተልኳል፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ግድያውን በፅኑ አውግዞ በስራ አስኪያጁ ዲፒ ካማራ፣ በፀሃፊያቸው ወ/ሮ በአካል አለልኝና በሹፌራቸው አቶ ፀጋዬ ግደይ ላይ ግድያ የፈፀሙትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ ነው ብሏል፡፡ ወንጀለኞቹን ተከታትሎ ለመያዝ ሠፊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በበኩሉ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል፡፡ ግድያ የተፈፀመባቸው የስራ አስኪያጁ ፀሃፊ የሶስት ልጆች እናት እንደነበሩ ታውቋል፡፡ዳንጎቴ ሲሚንቶ ከአካባቢው ማህበረሠብ ጋር የገባውን ውዝግብ በቅርቡ በሃገር ሽማግሌዎች አማካይነት በእርቅ የፈታ ሲሆን ደፒ ካማራ በአካባቢ ሽማግሌዎች “ገለታ” የሚል ስም ወጥቶላቸው እንደነበር ታውቋል፡፡
    “ሥራ አስኪያጁ ለማምለጥ ሞክረው ነበር”    ባለፈው ረቡዕ በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ ህንዳዊው ዲፒ ካማራ ገዳዮች እየተፈለጉ ሲሆን ሥራ አስኪያጁ ከገዳዮቹ ለማምለጥ ሞክረው እንደነበር ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ በኢትዮጵያ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሽያጭ ገበያ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ታሪኩ ዓለማየሁን ማነጋገሩን የጠቆመው ብሉምበርግ፤ የሥራ አስኪያጁ፣ ፀሐፊያቸውና ሹፌራቸው ግድያ የተፈፀመው ፋብሪካው አጠገብ መሆኑን እንደገለፁለት ዘግቧል፡፡ በናይጀሪያ ሌጎስ የሚገኙት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ዳይሬክተር ኢድዊን ዲቫኩማር በኢሜይል ለብሉምበርግ እንደገለፁትም፤ ሥራ አስኪያጁ ግድያው ሲፈፀምባቸው ሮጠው ለማምለጥ ሙከራ አድርገው ነበር፤ ገዳዮቹ የመኪናውን አሽከርካሪ በድንጋይ መተው አቅጣጫውን እንዲስት ባደረጉበት ወቅት ሥራ አስኪያጁ ከመኪናው ላይ ወርደው ሮጠው ለማምለጥ ሲሞክሩ ገዳዮቹ እግራቸውን በጥይት መተው ከጠሏቸው በኋላ በተደጋጋሚ ተኩሰው እንደገደሏቸው ገልፀዋል፡፡ ገዳዮቹ ሶስቱን ሟቾች በ15 ያህል ጥይቶች ደብድበው መግደላቸውን ቢቢሲ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የሥራ አስኪያጁ አስክሬን ወደ አገራቸው የተላከ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግለሠቦቹ ገዳዮች በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ያገኛሉ ብለዋል፡፡የህንድ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የናይጄሪያዊ ቢሊየነር ንብረት የሆነውን ዳንጎቴ ሲሚንቶን ከአንድ አመት ተኩል በላይ ሲያስተዳድሩ የቆዩትና ባለፈው ረቡዕ አመሻሽ ላይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት ደፒ ካማራ አስክሬን ከትናንት በስቲያ ለቀብር  ወደ ሃገራቸው ህንድ ተልኳል፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ግድያውን በፅኑ አውግዞ በስራ አስኪያጁ ዲፒ ካማራ፣ በፀሃፊያቸው ወ/ሮ በአካል አለልኝና በሹፌራቸው አቶ ፀጋዬ ግደይ ላይ ግድያ የፈፀሙትን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ ነው ብሏል፡፡ ወንጀለኞቹን ተከታትሎ ለመያዝ ሠፊ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በበኩሉ የህብረተሰቡን ትብብር ጠይቋል፡፡ ግድያ የተፈፀመባቸው የስራ አስኪያጁ ፀሃፊ የሶስት ልጆች እናት እንደነበሩ ታውቋል፡፡ዳንጎቴ ሲሚንቶ ከአካባቢው ማህበረሠብ ጋር የገባውን ውዝግብ በቅርቡ በሃገር ሽማግሌዎች አማካይነት በእርቅ የፈታ ሲሆን ደፒ ካማራ በአካባቢ ሽማግሌዎች “ገለታ” የሚል ስም ወጥቶላቸው እንደነበር ታውቋል፡፡
    ADDISADMASSNEWS.COM
    የዳንጎቴ ሥራ አስኪያጅና ባልደረቦቻቸው ገዳዮች እየተፈለጉ ነው - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news
    <p style="text-align: justify;">“ሥራ አስኪያጁ ለማምለጥ ሞክረው ነበር”<br /><br /> ባለፈው ረቡዕ በጠራራ ፀሐይ በጥይት ተደብድበው የተገደሉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ...
    0 Comments 0 Shares