• AMHARIC.VOANEWS.COM
    መንግሥት 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ መሆኑን አስታወቀ
    መንግሥት የኑሮ ውድነትን የማሻሻል እርምጃ አካል በማድረግ 50 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ አያስገባ መሆኑን አስታውቋል አስተያየታቸውን የሰጡን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ መንግሥት እርምጃ መውሰድ ከጀመረ በኋላ በዘይት ላይ የተወሰነ የዋጋ መሻሻል መኖሩን ገልጸው፣ ኾኖም የዋጋ ንረቱ ፈታኝ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ የምጣኔ ኃብት ተንታኝ የኾኑት አቶ አማንይሁን ረዳ፣ በሀገር ውስጥ በበቂ መጠን ማምረት እስኪቻል ድረስ፣ የኑሮ ውድነት ጫናን...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    ቱኒዚያ ህገወጥ የፍልስተኞች ጀልባ ሠርቷል ያለችውን ጣሊያናዊ ያዘች
    የቱኒዚያ ባለሥልጣናት ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚሞክሩ ህገወጥ ፍልሰተኞች የሚጠቀሙበትን ጀልባ በመስራት የተጠረጠረውን የ45 ዓመቱን ጣሊያናዊ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ዛሬ ረቡዕ አስታወቁ፡፡ ግለሰቡ በጀልባ ግንባታ ፋብሪካ ውስጥ የሚሠራ መሆኑን በምስራቅ ቱኒዝያ የምትገኘው የሞናስቲር ከተማ አቃቤ ህግ ቃል አቀባይ ፋሪድ ጃሃ ተናግረዋል። ከሜዲትሬኒያን ባህር ወደ አውሮፓ እንዲያሻግር ከፕላስቲክ የተሰራውን ጀልባ ግንባታ በማቀድ የተሳተፉ ሶስት ቱኒዚያውያንም...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    በአፍሪካ ለኤምፖክስ የተጋለጡ ወደ 4ሺ ሰዎች ተመዘገቡ
    የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል ባለፈው ሳምንት በአህጉሪቱ ወደ 4,000 የሚጠጉ ለኤምፖክስ የተጋለጡ አዳዲስ ሰዎች መመዝገባቸውና ወረረሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታወቀ፡፡ ማዕከሉ በወረረሽኙ እጅግ ወደተጎዳችው ኮንጎ የተላከው የመጀመሪያው ዙር ክትባት በመዘግየቱ አስፈላጊ ክትባቶች በአፋጣኝ እንዲሰጡ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በአፍሪካ ባለፈው ሳምንት ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ 81 ሰዎች ሞተዋል፡፡ ይህ ቀደም ሲል የነበረውን የሟቾች ቁጥር...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    ጄክ ሰለቨን ለባይደንና ሺ ስብሰባ ቻይና ናቸው
    የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሰለቨን በህዳር ወር ከሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት ለማስከን ትላንት ማክሰኞ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር በቤጂንግ ተገናኝተው ተወያይተዋል። ጉብኝቱ ፕሬዝዳንት ባይደን በጥር ወር ስልጣን ከመልቀቃቸው በፊት በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና በቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ መካከል ለሚደረገው የመጨረሻ የመሪዎች ጉባኤ መንገድ ለመክፈት ያለመ ነው።...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    በእስራኤል የዌስት ባንክ ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ተገደሉ
    እስራኤል በዌስት ባንክ ባካሄደችው ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የአካባቢው የጤና ባለስልጣናት ዛሬ ረቡዕ ገለጹ። ፍልስጤማውያኑ የተገደሉት ዋነኛው ጥቃትና ግጭት በተካሄደባቸው እስራኤል በያዘቻቸው የተለያዩ የጄኒን እና ቱባስ አካባቢዎች ነው፡፡ እስራኤል ሃማስ እና እስላማዊ ጂሃድን ጨምሮ በኢራን በሚደገፉ የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድኖች ላይ የምታካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ ጨምሯል፡፡ እኤአ ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በዌስት ባንክ ከ640 በላይ...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    የዳላስ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ የነጻ ክሊኒክን እያቋቋመ ነው
    40ኛ ዓመቱን በዳላስ ያከብራል በዩናይትድ ስቴትሷ የቴክሳስ ክፍለ ግዛት ዳላስ ከተማ የኢትዮጵያውያን ህብረተሰብ ማዕከል ለማህበረሰቡ የነጻ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ እያቋቋመ መሆኑን፣ ለዚህም ከግዛቱ የሕክምና አገልግሎት ተቆጣጣሪ ቦርድ እና ለሕብረተሰብ አገልግሎቶች ፈቃድ የሚሰጠውን የግዛቲቱ አስተዳደር ጽ/ቤት ይሁንታ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የህብረተሰብ ማዕከሉ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አዲስ ጥበቡ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ማዕከሉ በቅርቡ የጤና...
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    የአቶ ታዬ ደንደአ የዋስ መብት ጥያቄ ዳግም ለሳምንት ተቀጠረ
    የዋስትና መብታቸው እንዲከበር የጠየቁት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ ችሎቱ ለሁለተኛ ጊዜ የሳምንት ቀጠሮ ሰጥቷል። ዐቃቤ ሕግ ካቀረበባቸው ሦስት ክሶች ሁለቱ ውድቅ የተደረገላቸው አቶ ታዬ፣ እንዲከላከሉ በተበየነባቸው ማለትም “ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ በመያዝ” በሚለው ሦስተኛው ክስ ላይ የዋስ መብት አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ ባለቤታቸው ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
    0 Comments 0 Shares
  • AMHARIC.VOANEWS.COM
    በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከእስር ማስፈታቱን ተመድ አስታወቀ
    የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በምኅጻሩ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር፣ ባለፈው ሐምሌ ወር፣ ከአጋሮች ጋራ በመተባበር፣ “በዘፈቀደ የታሰሩ” ያላቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ የከተማ ውስጥ ስደተኞችን ማስፈታቱን አስታውቋል፡፡ ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ባወጣው ሪፖርት፣ በዐዲስ አበባ 879 ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ያቀረቧቸውን አስተያየቶች እና ቅሬታዎች መሠረት በማድረግ እና ከኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ጋራ...
    0 Comments 0 Shares