የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመሠራረት ምን ይመሥላል?

0
0

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤይርዌይስ/ Transworld Airways (TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን አስተዳደሩ በአሜሪካኖች እጅ ነበር፤ ድርጅቱ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ተመሥርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን መጋቢት ፴ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ካይሮ ድረስ አከናወነ። አየር መንገዱ ሲመሠረት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት ዲ.ሲ. ፫ (DC 3-C47) አውሮፕላኖች ነበሩት። በዓለም ዙሪያ በአፍሪካ፤ በእስያ፤ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ክፍለ አህጉራት ወደ ፶ የመንገደኛና የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ፲፮ መድረሻዎችን ያገለግላል። ዋና የጣቢያው ማዕከል በአዲስ አበባ የሚገኘው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የራሱ የአውሮፕላን አብራሪዎች ማሰልጠኛ ትምሕርት ቤት ሲኖረው የግል አብራሪ እና የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ፈቃድ በመስጠት የሀገር ልጆችንም ሆነ የውጭ ዜጎችን በማሰልጠን እስከ አርባ ዓመት ልምድ አለው። እንዲሁም ለብዙ የአፍሪካ ሀገር ብሔራዊ አየር መንገዶችና የግል አውሮፕላኖች የጥገና አገልግሎት ይሰጣል። አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የተያዘ የኢትዮጵያውያን ሀብት ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ለሽያጭ እና ለግዢ እንዲሁም ለብድር አመቺ እንዲሆን ተብሎ በአየር መንገዱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በኬይማን ደሴቶች የተመሠረተ ድርጅት ባለቤት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለመንገደኞች አገልግሎት አዲሱንና ዘመናዊውን የቦይንግ ፯፻፹፯ (Boeing 787) ድሪምላይነር አውሮፕላን በማዘዝና ጥቅም ላይ በማዋል ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ነው። የመጀመሪያውን ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን በነሃሴ ወር 2012 የተረከበ ሲሆን የተቀሩትን ፰ አውሮፕላኖች በሰኔ ፳፩፬ ተረክባልል። አየር መንገዱ ቦይንግ 777፣ ቦይንግ 787ና ቦይንግ 737ን ጨምሮ 68 ያህል እጅግ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀም፣ በአምስት አህጉሮች ወደሚገኙ 82 አለማቀፍ መዳረሻዎች በረራ እያደረገ የሚገኝ አለማቀፍ ዝናን ያተረፈ ተቋም ነዉ። በ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ዓለማየሁ በቀለ በላይነህ፣ ማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በናይሮቢ በኩል ወደ ቦምቤይ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩ በዓየር ላይ ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ አውስትራሊያ ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ወደምትገኘው የቆሞሮስ ደሴት ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የዓየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ ሞሐመድ አሚን ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከቤይሩት በተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በሜድትራኒያን ባሕር ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር። Sources:- http://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB_%E1%8A%A0%E1%8B%A8%E1%88%AD_%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%8B%B5

Like
1
Search
Categories
Read More
Shopping
Exquisite Hand Work Sherwani: Timeless Craftsmanship and Elegance
An exquisite hand work sherwani is a masterpiece that captures the essence of...
By Stylish12 2024-10-31 10:46:00 0 0
Other
HÀNG BÃI NHẬT: Xe Nâng Điện KOMATSU FB10-12 Bảo hành dài hạn, Giao hàng tận nơi
Bạn đang tìm kiếm một chiếc xe nâng điện mạnh mẽ, tiết kiệm, linh hoạt và an...
By xenangaz 2025-04-17 07:38:45 0 0
Uncategorized
ዳይ እየተሰዳደብን ...
«ዘውድአለም ታደሰ» ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም!...
By Zewdalem 2017-12-07 12:34:35 0 0
Uncategorized
ወርቃማው ደብዳቤ !
(አሌክስ አብርሃም) እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው...
By binid 2017-11-24 19:53:25 0 0
Uncategorized
ተመልሰን ሻሸመኔ!?
ተመልሰን ሻሸመኔ!?፡ይሉ ነበር የጓደኛዬ እናት፡፡ቡና እቤታቸው እየተፈላ እሳቸው አሪፍ ወሬ እያወሩልን ሰብበሰብ ብለን ከምናደምጠው መካከል አንዳችን...
By andualem 2017-11-12 13:17:14 0 0