ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል

0
0

ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል-ታካሚዎች

ዘውዲቱ ሆስፒታል ከአንድ ዓመት በፊት ለአምስት የኩላሊት እጥበት (ዲያሊስስ) መሳሪያዎች ግዥ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ቢያገኝም እስካሁን ግዥ አለመፈፀሙ ታካሚዎች ህክምናውን በቀላሉ እንዳናገኝ አድርጎናል የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።

ከ300 በላይ ታካሚዎች የኩላሊት እጥበት አገልግሎት ለማግኘት በሆስፒታሉ ወረፋ የሚጠብቁ ሲሆን፥ አሁን ላይ ያሉት አምስት የኩላሊት እጥበት ወይም የዲያሊስስ መስጫ ማሽኖች በቀን በአማካይ ለ25 ታካሚዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው።

ሆስፒታሉ ተጨማሪ አምስት የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎች ለመግዛት ከባምቢስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ከአንድ ዓመት በፊት ማግኘቱ ይታወሳል።

በመሳሪያዎች ቁጥር ተገድበው ተራቸውን የሚጠብቁ የኩላሊት ታካሚዎች ግን ዘውዲቱ ሆስፒታል ላይ ቅሬታ ያሰማሉ።

ከአንድ ዓመት በፊት አምስት የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎችን እንዲያስገባ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ቢያገኝም፥ እስካሁን ግዥውን አልፈጸመም፤ በዚህም ህክምናውን በቀላሉ ማግኘት አልቻልንም ነው ያሉት።

የመሳሪያዎች ግዥ በወቅቱ አለመፈጸሙ ሆስፒታሉ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚያገኙ ዜጎች ቁጥርን በእጥፍ ያሳድግ ነበር።

ችግሩን መኖሩን የሚያምነው ዘውዲቱ ሆስፒታል በበኩሉ፥ በድጋፍ የተገኘው ገንዘብ ለአምስት የኩላሊት እጥበት መሳሪያዎች ግዥ እንደማይበቃ በአስመጪዎች በኩል ስለተነገረን አማራጭ መፈለጉ ጊዜ ወስዷል ብሏል።

በሆስፒታሉ የኩላሊት ስፔሻሊስት ዶክተር ተስፋዬ ይልማ፥ ግዥው በአስመጪዎች በኩል ቢያለፍ ገንዘቡ መሳሪያዎቹን እንደማይገዛ ከተነገረን ወዲህ ሆስፒታሉ በልዩ ፈቃድ ራሱ እንዲያስገባ መፈቀዱን ተናግረዋል።

የተጠየቀው ፈቃድ ቢገኝም የብር የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ ሌላ ችግር እንደፈጠረባቸው ነው የገለፁት።

ዶክተር ተስፋዬ የተጨመረው 450 ሺህ ብር ከመንግስት ማግኘት ቀላል ቢሆንም፥ ለሆስፒታሉ የተፈቀደው ልዩ ግዥ ያንን አካሄድ እንደማይፈቅድ ይጠቅሳሉ።

ከባምቢስ ሃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ባለፈው ዓመት የተገኘው የአንድ ሚሊዮን ብር፥ ድጋፍ አሁን ላይ በሮተሪ ክለብ የእርዳታ ድርጅት እጅ እንደሚገኝ የድርጅቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ መላኩ በዛ ገልፀዋል።

ለግዥው መዘግየትም የሆስፒታሉ ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መጓተቱን እንጂ ችግሩ አሳሳቢ ባለመሆኑ የመጣ አይደለም ነው ያሉት።

በሌላ በኩል ሞት በኩላሊት ይብቃ በጎ አድራጎት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ እዮብ ተወልደ መድህን፥ የገንዘብ ድጋፉ የተገኘው በማህበሩ ተደጋጋሚ ጥያቄ ነው፤ ብሩ ቢፈቀድልን ማሽኑን ያለቀረጥ እንድናሰገባ የመንግስት ድጋፍ አለን ይላሉ።

በወቅቱ የሮተሪ ክለብ ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ መላኩ በበኩላቸው፥ ድጋፉ ለዘውዲቱ ሆስፒታል እንጂ ከማህበሩ ጋር አይገናኝም ብለዋል።

አሁን ላይ ዘውዲቱ ሆስፒታል ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በማፈላለግ በተፈቀደው ግዥ ወይም በመንግስት የግዥ አካሄድ መሳሪያዎችን ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑን ዶከተር ተሰፋዬ ጠቁመዋል።

በንብረቴ ተሆነ

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም 
(አሌክስ አብርሃም) ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ...
By binid 2017-11-26 06:31:13 0 0
Uncategorized
the royal
The Royal Collection is the art collection of the British Royal Family. They include a number of...
By Dawitda 2017-11-16 07:18:56 0 0
Uncategorized
_ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር
__ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር “The graveyard is the richest place on earth,...
By Seller 2017-12-01 08:05:09 0 0
Uncategorized
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)፡ፒስ ነው ጋይስ?!ቃሉን የማያጥፈው መንግስታችን "መጪው ዘመን የከፍታ ነው" ባለው መሰረት ከሰሞኑ ዶላሩን...
By andualem 2017-11-12 15:14:07 0 0
Art
How to get escorts in Dubai 0528648070 Verified Bur Dubai Escorts
How to get escorts in Dubai 0528648070 Verified Bur Dubai Escorts She left. She said that Dad...
By heenaparker516 2025-06-06 15:34:33 0 0