አራዳ ይስፋፋ

0
0

አራዳ ይስፋፋ..!!!ሰገጤ ይነፋ..!!! በሚለው የዘውትር መግቢያ መፈክራችን ከዋናው ስቱዲዮ ሁነን የዛሬው የቅዳሜ ጭውቴአችንን በይፋ ጀምረናል :) በመሐል ለይ ድነገት መብራት ቢጠፋ'ኳን ሀሳብ አይግባችሁ...!!!እንደ አሜሪካ ካሉ ያደጉት ሀገሮች ለይ መብራት እየጠለፍን ቢሆንም ጭውቴውን እናደራዋለን....!! ምን አልባት ይሄን ስል አንዱ ሰገጤ ጭንቄውን ይዞ ምናምን ‹‹ኦዮ አሁኒ ኢኒዴት ቢለክ ኖ ከአሜሪካ ዲረስ መርባት የሚጠልፈው›› ሊል ይችላል..!!! ጀለሴ ለአራዳ ልጅ መጥለፍ ልክ እንጀራ እንደ መጠቅለል ያህል ቀላል ነው...!! እኛ ቡሌ እንጠልፋለን...ቺክ እንጠልፋለን..... አውሮፕላን እንጠልፋለን ....መንኮራኩር እንጠልፋለን..... ስልክ እንጠልፋለን...ፌስቡክ እንጠልፋለን......ጀት እንጠልፋለን.....ታንክ እንጠልፋለን....የተተኮሰ ሚሳኤል እንጠልፋለን... ባጠቃላይ ከዳንቴል በስተቀር ሁሉንም እንጠልፋለን...!!! ዳንቴሉንም ላሽ ያልነው ሰገጤዎች ምን ሰርተው ይበላሉ ብለን በማሰብ ነው እንጂ መጥለፍ አቅቶን አይደለምlol

ለማንኛውም ዛሬ የአራዳ መፍለቂያ የሆኑ የሸገር ሰፈሮችን ለሰገጤዎች ወደ ማስተዋወቁ ስራ ስንሄድ... ከቄራ ቀጥሎ የምናገኘው ጀለስካ አብዱ ኪያር የዘፈነላትን "መርካቶ" ይሆናል ...!! አይ መርካቶ...! ስንቱን አሳለፍንብሽ?....ስላንቺ ምን ተወርቶ ምንስ ይተዋል?......አንቺን ሳስብ አይኔ ለይ ቶሎ የሚከሰተው እንባዬ ሳይሆን... ከሙባይ ህዝብ የማይተናነሱ ጭቁኖቹ ልጆችሽ እና እንደ ሰካራም ተደጋግፈው የቆሙት የቆርቆሮ ቤቶችሽ ናቸው.....!!!

የሚገርመው የመርኬ ሰፈር ቤቶች በጣም የተደጋገፉ ከመሆናቸው የተነሳ ለአንዱ ቤት ማገር ማቆሚያ የተመታ ሚስማር ኔክስት ዶር ትሪ ይሰቀልበታል ...!! በዛ ላይ እዛ ሰፈር ያሉ ቤቶች በጠቅላላ ቀበሌ 10..... ቀበሌ 8....ቀበሌ11 ...እየተባሉ ነው የሚጠሩት...!! ለምን እንደሆነ ነቄ ብላቿል?... 10 ልጅ ያለበት ቤት ከሆነ ...ቀበሌ አስር ተብሎ ይጠራል ...8 ልጅ ያለበት ቤቱ ከሆነ ደግሞ ያው ቀበሌ ስምንት እየተባለ ይጠራል ማለት ነው...!!! በዚህ አይነት የእኛ የቤት ቀበሌ 22 ነበር የሚባለው lol

ሌላው ደግሞ መርካቶ የተከፋፈለችው በጠቅላላ ''ተራ'' በሚባሉ ሰፈሮች ነው....ሱማሌ ተራ.....ቦምብ ተራ....ሸክላ ተራ....ሸራ ተራ.....ብቅል ተራ....ጎማ ተራ.....ሸማ ተራ.. እንትን ተራ....በመጨረሻም ምን አለሽ ተራ...!! ምናለሽ ተራ የሌለ ነገር ቢኖር ''ምንም'' ብቻ ነው...!! በቃ የማይሸጥ ነገር የለም...!!! አሮጌ ማንኪያ....የተጣመመ ሹካ, ጠርሙስ....የጠርሙስ ክዳን ለብቻው....የለስላሳ ጠርሙስ የተሸረፈ,.....የለስላሳ ጠርሙስ ያልተሸረፈ.... ነጠላ ጫማ አንድ እግር .....ባለ ሁለት እግር,.... ባለ ሶስት እግርም...2 አይነት ካልሲ....የተጣፈ ፓንት ሃሃሃሃ የፓንቱማ ነገር አይነሳ...!! እሙሙ መሽፎኛው ቦታ ላይ ያንሶላ ቅዳጅ ተጥፎባት የሆሊውድ አክታሮች የፈረሙባት ነው የሚመስለውlol

በተረፈ ያው "መርካቶ" ሲባል ሁሉም ትዝ የሚለው ጅረራ ነው! አቤት ጅረራ...!! መርካቶ መተህ ካልተጀረርክ በቃ አንተ መንፈስ ነህ...! አብሶ ቅባቶች ሲቀብጡ መኪናቸውን ፓርክ አድርገው ምናምን ለጭቃ ሸኖ ወደ ቶይሌት ይሄዱና ሲመለሱ መኪናዋን የሚያገኟት እስኬለተኗን ብቻ ነው....ሰገጤዎች ራሱ.... ሱሪ በቅናሽ ዋጋ አገኘን ምናምን ብለው ሀፒ ነክሰው ይገዙና ከዛ ቤት ሄደው.... ጏደኛ... ቤተሰብ.. ቤተ ዘመድ.. በተሰበሰበበት የገዙትን ሱሪ ለመለካት ከፈትፈት ሲያደርጉት የተጠቀለለ አሮጌ ጆንያ ሁኖ ያገኙታል...!!! ሃሃሃሃ መርክዬ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ..!!!!

ፍለጋ
Categories
Read More
Shopping
Can Minidumperfactory Electric Garden Loader Manage Materials Across Garden Sites
Electric Garden Loader usage has become increasingly common in daily garden work as landscaping...
By Minidumperfactory Minidumperfactory 2025-12-18 07:00:40 0 0
Uncategorized
ማበድ ደጉ!
«ዘውድአለም ታደሰ» ዳኒ የሰፈራችን ፅድት ያለ እብድ ነው። ቤተሰቦቹ ሃብታሞች ስለሆኑ ምንም ነገር አይቸግረውም። ልብሱም ንፁህ ነው።...
By Zewdalem Zed 2017-12-14 19:33:57 0 0
Uncategorized
ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል
ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል-ታካሚዎች ዘውዲቱ ሆስፒታል ከአንድ ዓመት በፊት ለአምስት...
By Binid Dre 2017-11-26 06:52:11 0 0
Sports
Patriots vs. Dolphins Wednesday problems post: Vederian Lowe in between 4 non-members for Clean England
The Fresh new England Patriots started off AFC East operate upon the Miami Dolphins devoid of...
By BgmntFtball BgmntFtball 2026-02-06 06:35:01 0 0
Uncategorized
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ...
By Andualem Buketo 2017-11-12 15:13:23 0 0