ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣን እንደማይለቁ ገለፁ

0
0

በራሳቸው ፍቃድ ከፕሬዚዳንትነታቸው እንዲወርዱ ጫና እየተደረገባቸው ያሉት የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ትናንት በሰጡት መግለጫ ስልጣን እንደማይለቁ ተናግረዋል።

በቀጥታ የተሌቪዥን ስርጭት በተላለፈው መግለጫቸው በቀጣይ ታህሳስ ወር በሚደረገው የዛኑ ፒ ኤፍ አጠቃላይ ስበሰባ ላይም ፓርቲያቸውን በመምራት እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ግን በትናነትናው እለት ሮበርት ሙጋቤን ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ማንሳቱ ይታወሳል።

ሮበርት ሙጋቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ፤ ካልሆነ ግን ስልጣናቸው እንደሚነጠቅ ፓርቲው በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

የዚምባቡዌ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ በሀገሪቱ ስልጣን ላይ ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ የፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሀይል መቀነሱ እየተነገረ ይገኛል።

ሮበት ሙጋቤ የሀገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ኤሚርሰን ማኛንጋዋን ከስልጣን ማንሳታቸውን ተከትሎ ነው ይህ ሁሉ ቀውስ የተከሰተባቸው።

ይህንን ተከትሎም በራሳቸው ፍቃድ ከፕሬዚዳንትነታቸው እንዲወርዱ ጫና እየተደረገባቸው ሲሆን፥ በርካታ የሀገሪቱ ዜጎችም ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው መግለጫቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ይፋ ያደርጋሉ በሚል በመጠባበቅ ላይ ነበሩ።

በአንጻሩ ግን ሮበርት ሙጋቤ በጦር ጀነራሎች ታጅበው በሰጡት መግለጫ፥ “ስልጣኔን አልለቅም፤ ከሳምንታት በኋላ የሚደረገ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ኮንግረስን እመራለው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከፓርቲያቸው፣ ከሀገሪቱ ጦር እና ከሀገሪቱ ህዝብ እየቀረበ ያለውን ቅሬታ እንደሚቀበሉ እና ዚምባቡዌን ወደ ቀድሞ ሰማሏ እንደሚመልሱ ተናግረዋል።

ለ20 ደቂቃ በቆየው መግለጫቸው እየቀረበላቸው ስላለው የስልጣን መልቀቅ ጥያቄና ስለ ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ የተናገሩት ነገር የለም ነው የተባለው።

“ጦሩ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠሩ እና እኔን በቤት ውስጥ በማሰሩ የሰራው ስህተት የለም” ሲሉም ተደምጠዋል።

ይሁን እንጂ ፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ኤፍ ፕሬዚዳንቱ አስከ ዛሬ 7 ሰዓት ድረስ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የማይለቁ ከሆነ ፕሬዚዳንትነቱን እንደሚነጥቃቸው አስታውቋል።

ዛኔ ፒ ኤፍ ፓርቲ በትናንትናው እለት ባደረገው ስብሰባ ሮበርት ሙጋቤን ከፓርቲው ሊቀ መንበርነት ማንሳቱን አስታውቋል።

ባለቤታቸው ቀዳማዊ እመቤት ግሬስ ሙጋቤም ከፓርቲ አባልነታቸው መባረራቸውንም ፓርቲብ በትናንትናው እለት አሳውቋል።

ፓርቲው በፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን የተባረሩት የቀድመሞውን ምክትል ፕሬዚዳንት ኤመርሰን መኛንጋዋን ሊቀ መንበር ማድረጉን እየተነገረ ነው።

Like
1
Search
Categories
Read More
Uncategorized
Macaafa Qulqulluu!!
Ergaa jireenya dhugaa fi Amantii.
By T002 2017-11-15 04:43:20 0 0
Uncategorized
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ...
By andualem 2017-11-12 15:13:23 0 0
Uncategorized
አንዳንድ ነገሮች ስለ ግማደ መስቀሉ
(ዳንኤል ክብረት) ስለ ግማደ መስቀሉ አመጣጥ ግሼን በሚገኘው በመጽሐፈ ጤፉት የተጻፈውን ባለፉት ዘመናት ስናነበውና ስንሰማው ኖረናል፡፡ እስኪ ዛሬ ደግሞ...
By binid 2017-11-25 13:26:59 0 0
Uncategorized
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››(አሳዬ ደርቤ)‹‹ምሳዬን የት...
By Assaye 2017-11-12 07:31:32 0 0
Uncategorized
ከነጠላው ስር !!
(አሌክስ አብርሃም) የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ሁሉ በግ መስሎን ተበላን ጓዶች !!እኛ ኢትዮጲዊያን በተለይ በዚህ ሰአት ‹‹ፈጠራ...
By binid 2017-11-26 06:32:11 0 0