አንዳንድ ቅዳሜዎች

0
0

አንዳንድ ቅዳሜዎች

በጣም ጠፋሁ አይደል!!; አይ ኖው…. አይ ኖው….አይ ሚስ ዩ ቱ ጋይስ፡፡
ያው መጥፋቴ የቢዴና ነገር ሆኖብኝ ነው….አለ አይደል ኑሮን ለማሸነፍ ባይቻል እንኳን አቻ እንኳን ለመውጣት ለአንዲ ማኛ አይነቱ ከጀርባውም ሆነ ከፊቱ ከፖሊስ በቀር ምንም ለሌለው ለፍቶ አዳሪ ከጥዋት እስከ ማታ መዋተት ግድ ነው፡፡አለበለዚያ እንደ ወ/ሮ አዜብ መስፍን ምስኪን ደሃ ሆኖ መቅረትም አለ፡፡ብቻ ሰርቶ ለማደርም ቢሆን ጤና እና ጉልበት የሰጠን አምላክ ተመስገን ከማለት ውጪ ምን ይባላል !;…በነገራችን ላይ ተመስገን ስል ጋዜጠኛው ተመስገን ደስአለኝ ትዝ አለኝ….. ተሜ እንኳን ለቤትህ አበቃህ!…(ያው ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፊው እስርቤት እንኳን ደህና መጣህ$ እንደማለት ነው…በነገራችን ላይ እስከዛሬ ድረስ ካየኋቸው በትክክለኛ ስማቸው እየፃፉ መቀመጫቸውን እዚሁ ሀገር ውስጥ ካደረጉ ጸሃፊዎች የተሜን ያህል ደፋር እና ቀጥተኛ ተቃውሞ ማሰማት የሚችል ሰው አላየሁም…ሂ ኢዝ ጀስት ዋን ኦፍ ሂዝ ኦውን ካይንድ (…በድፍረትም የሚበልጠኝ እሱ ብቻ ይመስለኛል….ያው አለ አይደል አንዳንዴ የአንዲ ማኛን ፖስቶች ዞር ብዬ ሳነብ ሃሳቧን ለመግለጽ ፍርሃት ሸብቧት ስትንበጫበጭ ያጋጥመኝና …#አሁን እንዲህ ከመንተባተብ ባይጸፍስ!;$ ብዬ ሙድ እይዝባታላሁ….)
፡ 
እሺ ምን አዲስ ነገር አለ ጋይስ;…በቀደም ጠሚያችን ለፓርላማው ያቀረቡትን #ሞሽን$ በራዲዮና ተከታተልኩት…በርግጥ ያንን ወሬ ሞሽን ከሚሉት ኢሞሽን ቢሉት የበለጠ ይገልጸዋል…ጠሚው ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሙሉ የሚሰጡት መልስ ሰውዬው የሟቹን ጠሚ የድርቅና ሌጋሲ ለማስቀጠል ተግተው እየሰሩ እንደሆነ ብቻ ነው የሚያሣየው…ዘ ኦንሊ ቲንግ ሚሲንግ ኢዝ ዘ ፎርመር ሃድ አት ሊስት አ ዩኒክ ሴንስ ኦፍ ሂውመር….ዘ ሬስት ኢዝ ኦል ዘ ሴም… ተመልሰን ሻሸመኔ$ ነገር ነው፡፡ለምሳሌ የፓርላማው አባላት ከኢሃዲግ ጽ/ቤት ጠሚውን እንዲጠይቁ ከተላከላቸው እና እየተንባተቡ ካቀረቧቸው ጥያቀዌች ውስጥ ሰሞኑን በሶማሌ #ክልል$(ሀገር ብል ደስ ይለኛል) ስለተነሳው ግጭት እና የግጭቱ ሰለባ ስለሆኑ የኦሮሞ ብሄሬሰብ ኢትዮጲያውያን ይመለከት ነበር…አንደኛው የተከበረ ኣባል$ ከቺኳ አፈ ጉባኤ እድሉን እንዳገኘ( ወ/ሮ ሽታዬ የውሃ ሽታ ሆነው በቀሩት አቶ አባዱላ ምትክ ዋናውን ወንበር ጋማ ብለዋል) ጠሚው ፓርላማ መጥተው በሚነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ ለመመለስ ፍቃደኛ በመሆናቸው እንደአብዛኞቹ ጠያቂዎች አላስፈላጊ ውዳሴውን ከደረደረ በኋለ(ቆይ ግን ጠቅላይ ሚኒስቴር ፓርላማ መጥቶ ማብራሪያ ካልሰጠ ደሞዝ የምንከፍለው ዱቅ ብሎ ጥሬ ስጋውን እየለበለበ ጨጓራውን እንዲያረካ ነው እንዴ ጋይስ!; …ከዛሬ ወዲህ አንድም የፓርላማ አባል ይሄን ከንቱ ውዳሴ ሲያቀርብ እንዳልሰማ!...(አራት ነጥብ)…(አክቹዋሊ ነጥቦቹን ብትቆጥሯቸው ሶስት ናቸው)…እና ጥያቄው ምን መሰላችሁ….#መከላከያ ሰራዊታችን በግጭቱ ቦታ በጊዜ ቢደርስ ኖሮ ይሄ ሁሉ ጣጣ አይመጣም ነበር! ለምን ዘገየ;$ አይነት ነገር ነው…ያው ጠሚው ድርቅና እና ፋላሲን ሞያዬ ብለው ይዘውታልና …አይናቸውን እንደሽፈራው ሽጉጤ ፍጥጥ አድርገው (ይሄ እንኳን ግምቴ ነው…ኢሞሽኑን በራዲዮ ነው የተከታተልኩት).መከላካያችን እኮ በህዝቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅና ተናፋቂ ነው….አንዳንድ ጸረ ሰላም ሃይሎች ስሙን ሊያጠፉ ቢሞክሩም(ስልችት ያለ ፉሊሽ ማሳበቢያ)…. ወደ ግጭቱ ቦታም በጊዜው ነው የደረሰው$ ብለው ግግም አሉ… አሁን ማ ይሙት መከላከያ በጊዜ ቢደርስ(ላይቤሪያ እና ብሩንዲ በሚደርስበት ፍጥነት እንኳን) አንድስ ኦሮሞ ከቀየው ይፈናቀል ነበር;;ነው ወይስ የክልሉ ህዝብ ለመከላከያ ሰራዊት አበል ዩኤን ላይቤሪያ እና ሩዋንዳ ላይ እንደከፈላቸው በዶላር መክፈል ነበረበት;!…ጠሚው እንደሚሉት መከላከያ ሰራዊታችን ልክ ግጭቱ እንደተጀመረ ወደ ስፍራው እንዲያቀና ታዞ ከሆነና ሁለት መቶሺ ሰው ከተፈናቀለ በኋላ ከደረሰ እርግጠኛ ነኝ በሰራዊቱ ውስጥ #የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የኤሊ ተወርዋሪ ብርጌድ የሚባል ይኖራል ማለት ነው..አንድ ሻለቃ የታጠቀ ጦር ኤሊ እየጋለበ ወደስፍራው እንዲያቀና ካልታዘዘማ ……ተውት ብቻ ማወቁን እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን$ ያለው ሰውዬ የት ሄደ;! ሰሞኑን አይቼው አላውቅም!

እና ትናንት(ትላንት) የሆነች ጓደኛዬ ልደት ነበር ..አቢጊያል ትባላለች…ያው እንደዚህ አይነት ሴርሞኒዎች ባይመቹኝም..ባለልደቷ ከባድ ጀለሴ ስለነበረች ሄድኩኝ…ጓደኛዬ ብትሆንም በእድሜ በጣም እበልጣታለሁ..(3 አመቷ ነው)…..እዛው ልደት ላይ ወ/ሮ ኣባይነሽ ብሩን (የቀድሞ የእሁድ ጥዋት የራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ነች….(ከነ ታደሰ ሙሉነህ ጋር ማለት ነው)አገኘኋት..ዊ ሃድ አ ቬሪ ናይስ ዲስከሽን….ግን የገረመኝ ነገር ምን መሰላችሁ..የኔን ፌቡ ስታተስ ታነባለች…..በልጅነታችሁ በጣም የምታደንቁት ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነ ሰው በአካል አግኝቷችሁ ያንተን ታይም ላይን አነባለሁ$ ሲላችሁ የሆነ ሞራላችሁ አይመጣም;!አንዳንድ ቅዳሜዎች$ ካስባሉኝ ምክንያቶች አንደኛው ይሄ ነው፡፡….ለካ እንደዚህ አይነት ዲሰንት ሰዎችም ፌቡ ያነባሉ….!; አ ቢግ ሪስፖንሲቢሊቲ ፎር ሚ…..

ከዛ ደግሞ ኮንሰርት ገበኋ!ሀዘን ላይ ሆነን ለምን ኮንሰርት ገባህ ለሚሉ መልስ አለኝ..(በርግጥ ምክንያታዊ አይደለም) አንድ የጆርካ ኢቨንት አባል የሆነ ልጅ (ዳኒ ይባላል) አንዲ ማኛ አንቺማ ይሄንን ኮንሰርት ካልገባሽ ምን ሰው ገባ ይባላል;!$ አለኝና(በርግጥ ትኬት ብሰጥህ ደስ ይለኛል gብቻ ነው ያለኝ)ያው |#ጠሪ አክባሪ ብዬ ሚስቴን ሳላስፈቅድ ዘው አልኩ…..በጣም በጣም የማደንቀው እና የምወደው አርቲስት አሊ ቢራን # ፍሮም አ ቬሪ ክሎዝ ሬንጅ ሲዘፍን አይቼው ደስ አለኝ…ግን አንዳንድ ቅዳሜዎች$ ያስባለኝ እሱን ማየቴ አይደለም…አሊ እየዘፈነ እያለ ድንገት አብርሃም ገ/መድህን(ተጋሩ… ዘፋኝ) አሊን ጆይን አደረገው …አንድ የኦሮሞ ኤሊት ዘፋኝ ከአንድ የትግርኛ ተወዳጅ ዘፋኝ ጋር ተቃቅፎ ኒንዴማ ኒንዴማን ሲጨፍር ህዝቡም ይህን አይነቱን ፍቅር በደስታ ሲቀበለው ከማየት በላይ (በተለይ ዚስ ዴይስ ከነበረን ሙድ አንጻር) …አንዳንድ ቅዳሜዎች የሚያስብል ምን አለ….!;
ሀገሬ አሁንም ላለመፍረስ ተስፋ አለሽ ..ይመችሽ!
በነገራችን ላይ ቺኳ(ዘ ዋይፍ) ብቻዬን ኮንሰርት በመግባቴ ጓ ሳትል አት ቀርም…አንዳንድ ሚስቶች ስሜታዊ ናቸው ሰው 7 ሰአት ገባ ተብሎ እንዲህ ይነጀሳል…!.ኖ ብሬክፋስት ኢን ዘሞርኒንግ … ኖ ያ ነገር ላስት ናይት ….አንዲ ማኛ ሃርድ ላይ ነች…ጆርካ ኢቨንቶች እግዜር ይይላችሁ!…ኔክሰት ታይም ኢፍ ዩ ወንት ቱ ኢንቫይት ሚ ፕሊስ ሜክ ኢት ቱ…እስቲ ፆም ከመዋል አትሊስት ከአሁን በኋላ ፀባዬን ላሳምር…!
ሌሎቻችሁ 
ይመቻችሁ

Search
Categories
Read More
Uncategorized
አስገራሚ ቃለ ምልልስ -ሙጋቤ
”መቼም ሙጋቤ መልካም ሰው ነው” ይላል- መንግስቱ ሃይለማርያም የክፉ ቀን ደራሹን ማመስገን ሲጀምር።በርግጥ የሙጋቤን መልካምነት...
By binid 2017-11-26 06:36:34 0 0
Art
Jumeirah Park Call Girls +971589930402 Indian Call Girls in Jumeirah Park By Dubai Call Girls
Jumeirah Park Call Girls +971589930402 Indian Call Girls in Jumeirah Park By Dubai Call Girls She...
By heenaparker516 2025-06-06 15:41:51 0 0
Art
+971589930402 Pakistani Verified Call Girls Service in Jvc Dubai UAE | Pakistani call Girls agency
+971589930402 Pakistani Verified Call Girls Service in Jvc Dubai UAE | Pakistani call Girls...
By heenaparker516 2025-06-06 14:59:37 0 0
Uncategorized
Ethiopia Travel Guide for Curious Travelers
For those seeking something different, here’s my Ethiopia travel guide that will hopefully...
By binid 2017-11-26 06:56:18 0 0
Art
Dubai International Airport Call Girls 0528604116 Call Girls in Dubai International Airport
Dubai International Airport Call Girls 0528604116 Call Girls in Dubai International Airport She...
By heenaparker516 2025-06-06 15:35:31 0 0