የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

0
0

ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90 ስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ለጋዜጣዊ መግለጫ የቀረቡት ጄነራል ኮንስታንቲኖ ቺዌንጋ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የማንንም ስም አልጠቀሱም። የሙጋቤን ቦታ ሊተኩ ይችላሉ ሲባል የነበሩት ምናንጋግዋ ሸሽተው ሃገሪቱን ጥለው ወጥተዋል። አሁን የፕሬዝዳንት ሙጋቤ ባለቤት ግሬስ ሙጋቤ ባለቤታቸውን ለመተካት ቅድሚያውን አግኝተዋል። ምናንጋግዋንም "ጭንቅላቱ ሊደበደብ የሚገባ እባብ" ሲሉ ገልጸዋቸዋል። ባላቸው ብልህ አስተሳሳብ "አዞው" በሚል ስም የሚታወቁት ምናንጋግዋ "ዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ያንተና የሚስትህ እንደፈለጋችሁ የምታደርጉት የግል ንብረታችሁ አይደለም" ሲሉ ሙጋቤን ተችተዋል። በጦሩ ዋና መስሪያ ቤት መግለጫ የሰጡት ጄነራል ቺዌንጋ፤ በነጻነት ትግሉ ውስጥ የነበሩ እና እንደምናንጋግዋን ያሉ ሰዎችን ማባረር በትዕግስት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም ብለዋል። "በነጻነት ትግሉ ውስጥ ያለፉና እና የፓርቲው አባላት የሆኑት ሰዎች ላይ ያነጣጠረው የማባረር ስራ መቆም አለበት" ብለዋል። "ከአሁኑ ስራ ጀርባ ያሉ ሰዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ አብዮታችንን በተመለከተ ጦሩ ጣልቃ ከመግባት ወደኋላ አይልም" ብለዋል። ምናንጋግዋ ቀደም ሲል የመከላከያ እና የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። ሙጋቤ በበኩላቸው "ጀነሬሽን 40" (የአርባዎቹ ትውልድ) የሚባለው የዚምባብዌ ወጣት ፖለቲከኞች ድጋፍ አላቸው። በፖለቲከኞች መካከል ያለው እሰጣ አገባ "ሃገሪቱ ላላፉት አምስት ዓመታት የተጨበጠ ዕድገት እንዳታስመዘግብ አድርጓታል" ሲሉ ጄነራል ቺዌንጋ ተናግረዋል። በችግሩ ምክንያት ዚምባብዌ "በገንዘብ እጥረት፣ ግሽበትና በሸቀጦች ዋጋ መጨመር" እንድትሰቃይ አድርጓታል።

Like
1
Search
Categories
Read More
Uncategorized
አራዳ ይስፋፋ
አራዳ ይስፋፋ..!!!ሰገጤ ይነፋ..!!! በሚለው የዘውትር መግቢያ መፈክራችን ከዋናው ስቱዲዮ ሁነን የዛሬው የቅዳሜ ጭውቴአችንን በይፋ ጀምረናል...
By binid 2017-11-26 06:39:12 0 0
Uncategorized
እስፖርት ጀምረናል
እስፖርት ጀምረናል! «ዘውድአለም ታደሰ» ዛሬ ለምን እንደሁ እንጃ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ስገላበጥ አላሁ አክበር አለ! ቢቸግረኝ...
By Zewdalem 2017-11-15 05:22:44 0 0
Uncategorized
ተመልሰን ሻሸመኔ!?
ተመልሰን ሻሸመኔ!?፡ይሉ ነበር የጓደኛዬ እናት፡፡ቡና እቤታቸው እየተፈላ እሳቸው አሪፍ ወሬ እያወሩልን ሰብበሰብ ብለን ከምናደምጠው መካከል አንዳችን...
By andualem 2017-11-12 13:17:14 0 0
Uncategorized
አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም 
(አሌክስ አብርሃም) ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ...
By binid 2017-11-26 06:31:13 0 0
Uncategorized
የብርሃኑ ፍሬ
እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን...
By Seller 2017-11-24 08:29:50 0 0