በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ
Posted 2017-11-13 09:59:25
0
0
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።
:
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
:
ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
በህይወትሁ ማንንም አትውቀሱ
ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል
ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል
ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል።
(ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር)
Search
Categories
- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes
Read More
Why Should Flyloong Spoon Candy Machine Molding Accuracy Be Evaluated
Spoon Candy Machine selection plays an important role in shaping production efficiency, candy...
ወርቃማው ደብዳቤ !
(አሌክስ አብርሃም)
እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው...
ዳይ እየተሰዳደብን ...
«ዘውድአለም ታደሰ»
ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም!...
መጨከክ
መጨከክ(አሳዬ ደርቤ)ከሰባት ሰማይ ስር ካለ ጎጆ መሃልማጣት፣ መንጣት እንጂ… ኦናነት ታቅፎ -አይቻልም መጉደል፡፡.ልክ እንደ ማረሻው-...
አይኔን በሌላ ሰው አይን ሳየው!
(አሌክስ አብርሃም)
ፍቅረኛየ በየቀኑ እንዲህ ትለኛለች“ አብርሽ ‹የ› ” በቃ ‹ የ›...