ትንሹ ማርሌይ ‹‹ጁንየር ጎንግ›› በአዲስ አበባ
✈ግንቦት 29 በአዲስ አበባ ከዚያም ወደ ታላላቅ የአውሮፓ ከተሞች በመጓዝ ኮንሰርቶቹን ያቀርባል፡፡
✈ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ለ2ኛ ጊዜ ይሆናል፡፡
★15 ዓመታትን በሙዚቃው ሲሰራ ከ20 ሚ.ዶላር በላይ ሃብት አካብቷል፡፡
★2 የግራሚ ሽልማቶች የወሰደ ብቸኛው ጃማይካዊ ነው፡፡
✈በዓለም ዙርያ ከ421 በላይ ኮንሰርቶችን ሰርቷል፡፡
#Aurora_Production #Sigma_Entertainment_Zack
★★★
#One_LOVE_CONCERT
#Damian_Marley
#Zeleke_Gesesse #Jonny_Ragga
☞2017 ከገባ በኋላ በተለያዩ አገራት በተካሄዱ ግዙፍ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች 17 ኮንሰርቶችን ያቀረበው የ38 ዓመቱ፤ የሬጌና ዳንስ ሆል እውቅ አርቲስት ዴሚያን ማርሌይ ግንቦት 29 ቀን በጊዮን ሆቴል ከታዋቂዎቹ የኢትዮጵያ ሬጌ ሙዚቀኞች ዘለቀ ገሰሰ እና ጆኒ ራጋ ጋር ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት ይኖረዋል፡፡
☞ዴሚያን ✡ ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ የተመለሰው ለ7 ሳምንታት በአፍሪካ እና በአውሮፓ አገራት በተከታታይ ለሚያቀርባቸው ኮንሰርቶች ነው፡፡ ከወር በኋላ
#Stone_Hill ‹‹ስቶን ሂል›› በሚል ርእስ በጌቶ ዩዝ ኢንተርናሽናል አሳታሚነት ለገበያ የሚበቃውን አምስተኛ የስቱድዮ አልበም በሚያስተዋውቅበት ዘመቻ ገብቷል፡፡ ስለሆነም ባለፈው አርብ የመጀመርያ ዝግጅቱን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ያቀረበ ሲሆን ፤ ከዚያም ግንቦት 20 በደርባን ደቡብ አፍሪካ፤ ግንቦት 23 በናይሮቢ ኬንያ፤ ግንቦት 26 በሴንትፒዬር ዩኒዬን አይስላንድ፤ ግንቦት 27 በፖርት ሊዊስ ሞሪሽዬስ እንዲሁም ግንቦት 29 በአዲስ አበባ ኮንሰርቶቹን ይሰራል፡፡ የአፍሪካ ጉዞውን በአዲስ አበባ ካበቃ በኋላ በቀጥታ ወደ አውሮፓ በማቅናት በእንግሊዝ፤ በሆላንድ፤ በስዊዘርላንድ፤ በፈረንሳይ እና በጀርመን ሌሎች ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡
☞ዴሚያን ✡ወደ አፍሪካ ምድር ከ12 ዓመታት በኋላ የተመለሰ ሲሆን
#Africa_unite አፍሪካ ዩናይት በሚል መሪ ርእስ በ2005 እኤአ ላይ በአዲስ አበባ እና በ2006 እኤአ ላይ በጋና የተካሄዱ ሁለት ኮንሰርቶች ነበሩት፡፡ ስለሆነም አዲስ አበባ ለኮንሰርት የሚረግጠው ለ2ኛ ጊዜ ይሆናል፡፡ በ2005 እኤአ ላይ በአዲስ አበባ የቦብ ማርሌይ 60ኛ ዓመት በተከበረበት እና በመስቀል አደባባይ ከ250 ሺ በላይ በታደሙት ኮንሰርት ላይ ከወንድሞቹ ጋር ‹‹ኩድ ዩ ቢለቭድ››
#Could_you_Beloved ሙዚቃን በሪሚክስ በከፍተኛ የመድረክ ብቃት ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡
☞ዴሚያን ✡ሮበርት ኔስታ ማርሌ ተብሎ በሙሉ ስሙ ይጠራል፡፡ ‹‹ጁኒየር ጎንግ›› ወይም ‹‹ጎንግዚላ›› የተባሉ ቅፅል ስሞችም ተሰጥተውታል፡፡ ጁኒዬር ጎንግ የተባለው በታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ ንጉስ ቦብ ማርሌይ ቅፅል ስም ‹ታፍ ጎንግ›› መነሻነት የወጣለት የመድረክ ስም ነው፡፡ የቦብ ማርሌይ ትንሹ ልጅ ወይም የመጨረሻ ልጅ ሲሆን የተወለደው በ1978 እኤአ ላይ በኪንግስተን ጃማይካ ነበር አባቱ ቦብ ማርሌይ ከሞት የተለየው ገና የ2 ዓመት ህፃን ሳለ ነው፡፡ እናቱ ሲንዲ ብሬክስፒር ትባላለች፤ በ1976 እኤአ ላይ የዓለም ቁንጅና ውድድርን አሸንፋ አክሊል የተቀዳጀች ጃማይካዊት ውብ ሴት እና የጃዝ ሙዚቀኛ ናት፡፡ በአባቱ በኩል 11 በእናቱ በኩል ደግሞ 2 እህቶች እና ወንድሞች አሉት፡፡
☞ዴሚያን ✡በሙዚቃ ህይወት በተሞላ ቤተሰብ እንደመወለዱ ገና በልጅነቱ ነው ወደ ሙያው የተሳበው፡፡ በ13 ዓመቱ ከታዋቂ የሬጌ ሙዚቀኞች ልጆች ጋር ‹‹ዘ ሼፕርድ›› የተባለ የሙዚቃ ቡድን መስርቶ ነበር፡፡ ከአባላቱ መካከከል የፍሬዲ ማክሪጎር እና የሰርድ ዎርልድ ጊታሪስት ካትኮሬ ልጆች ይገኙበታል፡፡ በዚሁ የሙዚቃ ቡድን በ1992 እኤአ ላይ በታዋቂው የሬጌ ሙዚቃ ፌስቲቫል ሰንስፕላሽ ላይ ሊሰሩችለዋል፡፡
☞ዴሚያን✡ ዘ ሼፕርድ በተባለው የሙዚቃ ቡድኑ ብዙ አልገፋበትም፡፡ ጃማይካዊያን ዲጄይ ብለው በሚጠሩት የራፕ ስልት እየሰራ ብቻውን መንቀሳቀስ ቀጥሎ በድምፃዊነት፤ በራፕርነት፤ በዳንስሆል አርቲስትነት፤ በሙዚቃ ደራሲነት እንዲሁም በሙዚቃ አቀናባሪነት እያገለገለ ሲሆን፤ ሬጌ ዳንስ ሆል፤ ሩት ሬጌ፤ ሬጌ ፊውዥ፤ ሂፕሆፕ ሌሎች የተካነባቸው የሙዚቃ ስልቶች ናቸው፡፡
☞ዴሚያን ✡በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ለ15 ዓመታት ያህል ቆይቷል፡፡ ሴለብሪቲ ኔትዎርዝ በድረገፁ እንዳሰፈረው የሃብት መጠኑ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡ በ2006 እኤአ ላይ ከዓለማችን ከፍተኛ የሙዚቃ ሽልማቶች ግንባር ቀደም የሆነውን የግራሚ ሽልማት በሁለት ዘርፎች በማሸነፍ ብቸኛውና የመጀመርያው የጃማይካ ሬጌ ሙዚቀኛ ሊሆን በቅቷል፡፡ ለ2 የግራሚ ሽልማቶቹ የበቃው በ2005 እኤአ ላይ በዩኒቨርሳል አሳታሚነት ለገበያ ባበቃው ‹‹ዌል ካም ቱ ጃምሮክ›› የተባለው አልበም ሲሆን በምርጥ የሬጌ ሙዚቃ አልበምና በምርጥ ቤትስ ኦልተርኔቲቭ ፕርፎርማንስ ዘርፎች በማሸነፉ ነው፡፡
☞ዴሚያን ✡ በሶንግኪክ ድረገፅ ላይ በሰፈሩ መረጃዎች መሰረት ባለፉት 15 ዓመታት በመላው ዓለም ከ362 ሺ ማይሎች በላይ በመጓጓዝ ከ421 በላይ ኮንሰርቶችን ሰርቷል፡፡ በተለይ በብራዚል እና በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት ትልልቅ ፌስቲቫሎች በሚያቀርባቸው ኮንሰርቶች ከ100ሺ እስከ 200 ሺ ታዳሚዎችን ያገኛል፡፡ ብቻውን ከሚሳተፍባቸው ትልልቅ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች ባሻገር አብዛኛዎቹን ኮንሰርቶች ከወንድሞቹ እና ከታዋቂ ሙዚቀኞች ጋር ያቀርባል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት 421 ኮንሰርቶች መካከል 35 በሎስ አንጀለስ፤ 19 በኒውዮርክ፤ በዴንቨር 14 እንዲሁም በሳንዲያጎ በተባሉ የአሜሪካ ከተሞች ደጋግሞ የሰራ ሲሆን፤ ከስቴፈን ማርሌይ ጋር 120 ጊዜ፤ ከአሜሪካዊ ራፕር ናስ ጋር 78 ጊዜ፤ ከኤምፓየር ጋር 55 ጊዜ፤ ከማርሌይ ወንድማማቾች ጋር 38 ጊዜ እንዲሁም ‹‹ዲስታንት ሪሊቲቭ›› በሚል ከአሜሪካዊው ራፕር ናስ ጋር 30 ጊዜ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ምርጥ ኮንሰርቶችን ሰርቷል፡፡ ቡርኖ ማርስ እና ስከርሌክስ አብረውት የሰሩ ሌሎች ታዋቂ ሙዚቀኞች ናቸው፡፡
☞ዴሚያን ✡ የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ስራ የሆነውን ‹‹የከርሞ ሠው›› በዲስታንት ሪሌቲቭ አልበም ከአሜሪካዊው ራፕር ናስ ጋር ‹‹አስ ዊ ኢንተር›› በሚል ርእስ በልዩ የራፕና ሂፕሆፕ ስልት ተጫውተውታል፡፡
ትንሹ ማርሌይ ‹‹ጁንየር ጎንግ›› በአዲስ አበባ
✈ግንቦት 29 በአዲስ አበባ ከዚያም ወደ ታላላቅ የአውሮፓ ከተሞች በመጓዝ ኮንሰርቶቹን ያቀርባል፡፡
✈ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ ለ2ኛ ጊዜ ይሆናል፡፡
★15 ዓመታትን በሙዚቃው ሲሰራ ከ20 ሚ.ዶላር በላይ ሃብት አካብቷል፡፡
★2 የግራሚ ሽልማቶች የወሰደ ብቸኛው ጃማይካዊ ነው፡፡
✈በዓለም ዙርያ ከ421 በላይ ኮንሰርቶችን ሰርቷል፡፡
#Aurora_Production #Sigma_Entertainment_Zack
★★★
#One_LOVE_CONCERT
#Damian_Marley
#Zeleke_Gesesse #Jonny_Ragga
☞2017 ከገባ በኋላ በተለያዩ አገራት በተካሄዱ ግዙፍ የሙዚቃ ፌስቲቫሎች 17 ኮንሰርቶችን ያቀረበው የ38 ዓመቱ፤ የሬጌና ዳንስ ሆል እውቅ አርቲስት ዴሚያን ማርሌይ ግንቦት 29 ቀን በጊዮን ሆቴል ከታዋቂዎቹ የኢትዮጵያ ሬጌ ሙዚቀኞች ዘለቀ ገሰሰ እና ጆኒ ራጋ ጋር ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት ይኖረዋል፡፡
☞ዴሚያን ✡ ከ12 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ የተመለሰው ለ7 ሳምንታት በአፍሪካ እና በአውሮፓ አገራት በተከታታይ ለሚያቀርባቸው ኮንሰርቶች ነው፡፡ ከወር በኋላ #Stone_Hill ‹‹ስቶን ሂል›› በሚል ርእስ በጌቶ ዩዝ ኢንተርናሽናል አሳታሚነት ለገበያ የሚበቃውን አምስተኛ የስቱድዮ አልበም በሚያስተዋውቅበት ዘመቻ ገብቷል፡፡ ስለሆነም ባለፈው አርብ የመጀመርያ ዝግጅቱን በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ያቀረበ ሲሆን ፤ ከዚያም ግንቦት 20 በደርባን ደቡብ አፍሪካ፤ ግንቦት 23 በናይሮቢ ኬንያ፤ ግንቦት 26 በሴንትፒዬር ዩኒዬን አይስላንድ፤ ግንቦት 27 በፖርት ሊዊስ ሞሪሽዬስ እንዲሁም ግንቦት 29 በአዲስ አበባ ኮንሰርቶቹን ይሰራል፡፡ የአፍሪካ ጉዞውን በአዲስ አበባ ካበቃ በኋላ በቀጥታ ወደ አውሮፓ በማቅናት በእንግሊዝ፤ በሆላንድ፤ በስዊዘርላንድ፤ በፈረንሳይ እና በጀርመን ሌሎች ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡
☞ዴሚያን ✡ወደ አፍሪካ ምድር ከ12 ዓመታት በኋላ የተመለሰ ሲሆን #Africa_unite አፍሪካ ዩናይት በሚል መሪ ርእስ በ2005 እኤአ ላይ በአዲስ አበባ እና በ2006 እኤአ ላይ በጋና የተካሄዱ ሁለት ኮንሰርቶች ነበሩት፡፡ ስለሆነም አዲስ አበባ ለኮንሰርት የሚረግጠው ለ2ኛ ጊዜ ይሆናል፡፡ በ2005 እኤአ ላይ በአዲስ አበባ የቦብ ማርሌይ 60ኛ ዓመት በተከበረበት እና በመስቀል አደባባይ ከ250 ሺ በላይ በታደሙት ኮንሰርት ላይ ከወንድሞቹ ጋር ‹‹ኩድ ዩ ቢለቭድ›› #Could_you_Beloved ሙዚቃን በሪሚክስ በከፍተኛ የመድረክ ብቃት ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡