ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ እና የአሁኑን የህዝብ ቁጥር ላላማከሉ 10 የክልል ሆስፒታሎች ማስፋፊያ ሊደረግ ነው።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ ሆስፒታሎች ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ በመሆናቸው በየአካባቢያቸው ያሉ ነዋሪዎችን ቁጥር ከግንዛቤ ያላስገቡ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
ይህም ብቻ ሳይሆን የመሳርያ እና የባለሙያ እጥረት ታክሎባቸው የተለያዩ ታካሚዎቻቸውን በራሳቸው አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ እንደ ሪፈር ያሉ አማራጮችን እንዲጠቀሙ እድርጓቸዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጤና ጥበቃ ሚኒስርትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን፥ አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሎች ጋር በመሆን እድሜያቸው የገፉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት መታሰቡን ነግረዉናል።
“በክልሎች የሚገኙ እና ከ56 እስከ 80 ዓመት ያስቆጠሩ፥ አሁን ያለውን የተገልጋይ ቁጥር ያላማከሉ ሆስፒታሎች መኖራቸውን እኔም በተለያዩ ጊዜያት ባደረኩት ጉብኝት አረጋግጫለሁ” ብለዋል፡፡
በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚቀርቡት ጥያቄዎች አንዱ የነባር ሆስፒታሎች በአሁን ደረጃ የማይመጥኑ በመሆናቸው ማስፋፊያ እንዲደረግ መጠየቅ ነው ያሉት ሚንስትሩ፥ በዘንድሮው ዓመት የ10 ሆስፒታሎች ማስፋፊያ እናከናውናለን ብለዋል።
ለአብነት በአማራ ክልል በደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሀን፣ ደሴ፣ ወልድያ እና ደብረታቦር ያሉ ሆስፒታሎችን ለማስፋፋት ነው የታሰበው።
እነዚህ ሆስፒታሎች የሚስፋፉት ካላቸው ይዞታ በተጨማሪ ባለ ስምንት ፎቅ ማስፋፊያ ተደርጎላቸው አሁን ያላቸውን የአልጋ ቁጥር ወደ 400 ከፍ እንዲል እንደሚደረግ እና የአገልግሎት ጥራትና ደረጃቸውም ከፍ ይደረጋል ተብሏል።
ለማስፋፊያ ስራ የሚውለው በጀት 50 በመቶው በሚኒስቴር መሰሪያ ቤቱ፣ ቀሪው ደግሞ በክልሎች የሚሸፈን እንደሚሆን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን ተናግረዋል።
የሆስፒታሎቹን ወጪ በተመለከተም የሚወጣ ጨረታን ተመርኩዞ የሚወሰን ይሆናል ተብሏል።
የማስፋፊያው ስራ ግን በዚህ ዓመት እንደሚጀመር ነው ፕሮፈሰር ይፍሩ የተናገሩት።
የሆስፒታሎቹ ግንባታም በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የማስፋፊያ ስራዎቹ በሚኒስቴሩ እና በክልል ጤና ቢሮዎች ከሚገነቡት በተጨማሪ፥ ዩኒቨርሲቲዎችም በራሳቸው በጀት ሆስፒታሎች ለመገንባት የጠየቁ መኖራቸው ነው የተገለፀው።