ዓለምን ሥጋት ላይ የጣሉ የውሸት መድኃኒቶች
የውሸት ወሊድ መቆጣሪያ ሲጠቀሙ ቆይተው ይሆናል፡፡ ሕፃን ልጅዎ ጉንፋን ሲይዘው ለማስታገስ ብለውም ከኦፒኦይድ ማለትም የመድኃኒት ዝርያ ሆኖ አላግባብ ጥቅም ላይ እየዋለ በመሆኑ በተለይ በአሜሪካ ከፍተኛ የጤና ቀውስ እያስከተለ ከሚገኘው ንጥረ ነገር የተሠራ ሲረፕ ሰጥተውት ይሆናል፡፡
ከወባ በሽታዎ ለመዳን ወይም ቀድመው ለመከላከል የወሰዱት መድኃኒት ደግሞ ከድንች ወይም ከበቆሎ ተሠርቶ እርስዎ እንደ መድኃኒት ገዝተውት ይሆናል፡፡ እርስዎ ባይሆኑ እንኳን ዘመድዎ፣ ወዳጆችዎ ብሎም በአገርዎ ያለው መንግሥትም ሆነ መድኃኒት አስመጪዎች እንዲህ የውሸት የተሠሩ መድኃኒቶችን አሊያም ከደረጃ በታች የተፈበረኩትን አገር ውስጥ አስገብተው እርስዎና ሌሎች የዚህ ሰለባ ሆነው ይሆናል፡፡
መድኃኒቱ የውሸት ይሆን? ከደረጃ በታች ይሆን? ብለው ከመጠርጠር ይልቅ በሽታዬ አልተገኘልኝም ብለውም ደምድመውም ይሆናል፡፡ ሆኖም የዓለም ጤና ድርጅት ሰሞኑን ይፋ ያደረገው ሪፖርት በዓለም በተለይም በማደግ ላይ ባሉትና በደሃ አገሮች ሲከፋም በአፍሪካ ከሰሃራ በታች በሚገኙት የውሸት/ተመሳስለው የተሠሩና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድኃኒቶች መንሰራፋታቸውን ሰሞኑን አስታውቋል፡፡
በውሸትና ከደረጃ በታች በሆኑ መድጋኒቶች ምክንያት በአፍሪካ ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች ብቻ 72 ሺሕ ሕፃናት ከሳንባ ምች፣ 69 ሺሕ አዋቂዎች ደግሞ ከወባ ማገገም አቅቷቸው መሞታቸውንም ገምቷል፡፡
በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች ከሚቀርቡ መድኃኒቶች አንድ አሥረኛ ያህሉ የውሸት፣ በሽታን የማይፈውሱ ወይም ከደረጃ በታች ናቸውም ብሏል፡፡
ይህ ደግሞ ግለሰቦችና አገሮች መድኃኒት ለመግዛት ከሚያወጡት ገንዘብ በከፋም ደረጃ ባልጠበቁትና በውሸት መድኃኒቶች ምክንያት ለከፋ ሕመም ወይም ሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ድርጅቱ በጥናቱ አረጋግጧል፡፡
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የውሸት መድኃኒት የዓለም ፈተና ስለመሆኑ የገለጹት ‹‹አንድ እናት ልጇ ታሞባት መድኃኒት ለመግዛት ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶቿን ስታቆም በአዕምሯችሁ ሳሉት፡፡ መድኃኒቱን ገዝታ ለልጇ ሰጠችው፡፡ መድኃኒቱ ከደረጃ በታች ወይም የውሸት መሆኑንም አላወቀችም፡፡ ልጇም በወሰደው የውሸት መድኃኒት ሳቢያ ሞተ›› በማለት ነበር፡፡ ይህ በማንኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ አፅንኦት ቢሰጡትም፣ በገሃዱ ዓለም በተለይ ከ2013 ወዲህ የሚታየው በዓለም በተለይም በደሃ አገሮች የውሸትና ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች ገበያ ላይ ስለመዋላቸውና ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ስለመሆናቸው ነው፡፡
ከ2013 ወዲህ ብቻ ለድርጅቱ 1,500 የውሸት ወይም ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች ስለመገኘታቸው ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ከእነዚህ የውሸት መድኃኒቶች ውስጥ ሕዝብ በአብዛኛው የሚጠቀምባቸው ፀረ ተዋህስያን (አንቲባዮቲክስ) ይገኙበታል፡፡ በተለይ በመካከለኛና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ አገሮችን የሚፈትነውን ወባ ለመቆጣጠር ከሚውሉ መድኃኒቶችም የውሸት ስለመኖሩ ተደጋጋሚ መረጃ ለድርጅቱ ደርሷል፡፡
ለድርጅቱ ከደረሱ ጥቆማዎች ውስጥ 42 በመቶው ከአፍሪካ፣ 21 በመቶው ከአሜሪካ እንዲሁም 21 በመቶው ከአውሮፓ ናቸው፡፡ ድርጅቱ እንደሚለው ሪፖርት የተደረገለት ምናልባትም በዓለም ይሰራጫል ከሚባለው የውሸት መድኃኒት ቅንጣት ያህሉ ብቻ ነው፡፡ ከምዕራብ ፓስፊክ ስምንት በመቶ፣ ከምሥራቅ ሜዲትራኒያን ስድስት በመቶ እንዲሁም ከደቡብ ምሥራቅ እስያ ሁለት በመቶ ብቻ ሪፖርት መደረጉም ችግሩ ግዙፍ ቢሆንም ሪፖርት የማይደረግ መሆኑን ያመለክታል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የመድኃኒትና ክትባት ተደራሽነት ዳይሬክተር ጄኔራል ዶ/ር ማሪኒላ ሲማው እንዳሉት፣ የውሸት መድኃኒቶች የሚያደርሱት ጉዳት በሕሙማኑና በታማሚዎች ላይ ብቻ አይደለም፡፡ በዓለም በሽታን እየተላመደ ያስቸገረውን ባክቴሪያ ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ላይ የተጋረጠ ፈተናም ነው፡፡ መድኃኒቶች የማዳን ኃይላቸውን እየቀነሱ በመጡበት በዚህ ወቅትም የውሸትና ደረጃቸውን ያልጠበቁ መድኃኒቶች እየተሠራጩ መሆናቸው ለጤናው ዘርፍ ፈታኝ ሆኗል፡፡
እውነተኛ ያልሆኑ ወይም ተመሳስለው የተመረቱ መድኃኒቶች ሕገወጥ ንግድ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጦር መሳሪያ ሽያጭ ቀጥሎ ትልቅ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ነው፡፡ በዚህም ዙሪያ አምራቾችና እንደ ጅምላ አከፋፋይ ሆነው የሚንቀሳቀሱ አዘዋዋሪዎች፣ ቸርቻሪዎችና በስተመጨረሻም ተጠቃሚዎች ያሉበት ሲሆን፣ በተለይ የአዘዋዋሪዎች ብዛትና አቅም እንደቀላል የሚወስድ አይደለም፡፡ በየአገሮቹ ፖሊሲና ሕግ እስከማስቀየር ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ወይም አካል በአግባቡ እንዳይንቀሳቀስና እንዲዳከም ማድረግ የሚያስችል አሻጥር የመፈጸም አቅማቸውም ትልቅ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ደካማ የቁጥጥር ሥርዓትና የሕዝብ ድህነት ለሕገወጥ መድኃኒት ዝውውር ምክንያት ናቸው፡፡ ድህነቱም በዋጋ ላይ ብቻ ያተኮረ የሸማቾች አስተሳሰብ እንዲኖር አድርጓል፡፡
ተመሳስሎ የተሠራ መድኃኒት ጨርሶ የሚፈለገውን ኬሚካል ያልያዘ ወይም በአነስተኛ ደረጃ የያዘ ወይም ደግሞ ሊጎዳ የሚችል ኬሚካል የተጨመረበት ሊሆን እንደሚችል ቀድሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋርማኮሎጂ ዲፓርትመንት ሊቀመንርና የፋርማሲ ትምህርት ቤት ዲን አሁን ደግሞ የማኔጅመንት ሳይንስ ፎር ሔልዝ ካንትሪ ዳይሬክተር ንጉሡ መኮንን (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በዓለም ላይ በግምት እስከ 200 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የውሸት መድኃኒት ዝውውር እንዳለ ከዚህ ውስጥ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላዩ የውሸት መድኃኒት ዝውውር በአፍሪካ እንደሆነም አክለዋል፡፡ ተመሳስለው የተሠሩ መድኃኒቶችን ዋጋ ለይቶ ለማወቅ አንዳንድ ጊዜ እንደሚያስቸግር፣ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችና ነጋዴዎችም ዋጋውን እንደማያሳውቁና ታክስ እንደማይከፍሉ በዚህም የተነሳ ዋጋው በግምት ላይ እንዲመሠረት ማድረጉንም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ አንፃር የዓለም ጤና ድርጅት በ1995 ዓ.ም. ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶና ተጨማሪ ጥናቶችም አድርጎ በ2010 ዓ.ም. በዓለም ከሚዘዋወሩ መድኃኒቶች መካከል 10.5 በመቶ ያህሉ የውሸት ናቸው ብሎ አውጇል፡፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ደግሞ፣ በአንዳንድ አፍሪካ አገሮች ውስጥ እስከ 70 በመቶ መድኃኒቶች የውሸት/ተመሳስለው የተሠሩ መሆናቸውን እንደሚያሳዩ አስታውቀዋል፡፡
በተለይ በታንዛኒያና በናይጄሪያ የውሸት መድኃኒቶች ዝውውር ከአሥር በመቶ በላይ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ለማወቅ በአገር አቀፍ ደረጃ የተሠራ ሙሉ መረጃ የለም፡፡ ሆኖም የኮንትሮባንድ ንግድ ከሚዘዋወሩባቸው አገሮች ድንበር ስለምትጋራ የችግሩ ሰለባ ናት፡፡
የምግብ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ ባለሥልጣን የመድኃኒት ተቋማት ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ እንዳለ፣ የተለያዩ መድኃኒቶች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቁጥጥር እንደሚደረግ፣ መድኃኒቱ ገበያ ከመሠራጨቱ በፊት የላቦራቶሪ ጥራት ምርመራ፣ ገበያ ላይ ከዋለ በኋላም የድረ ገበያ ቅኝት እንደሚሠራና በዚህም ተመሳስለው የተመረቱ ወይም ደረጃቸውን ያልጠበቁት እንደሚለዩ ይናገራሉ፡፡
ባለሥልጣኑ ባደረገው ምርመራም፣ በ2008 ዓ.ም. መጨረሻ ጋምቤላ ክልል አንድ የፀረ የወባ መድኃኒት የውሸት ወይም ተመሳሳይ ሆኖ ተገኝቶ ነበር፡፡ በወቅቱ መድኃኒቱ በኮንትሮባንድ አዲስ አበባ ገብቶ ከዚህ እንደተላከም ታውቋል፡፡
የውሸት ተመሳስለው የተሠሩ መድኃኒቶች በብዛት ባይገኙም ከደረጃ በታች የሆኑ ግን ተገኝተዋል፡፡ ባለሥልጣኑ በተለይ ኅብረተሰቡ በብዛት የሚጠቀምባቸው ፀረ ተዋህስያን፣ ፀረ-ወባና ሌሎችም ችግር ሊያመጡ ይችላሉ የሚባሉ መድኃኒቶችን በመለየትና በላቦራቶሪ በመመርመር ገበያ ላይ እንዳይውሉ እያደረገም ነው፡፡ ለዚህም በዓለም ተቀባይነት ያለውን የዩኤስፒ ወይም ብሪትሽ ፋርማኮፒያ (የአንድ መድኃኒት የጥራት ደረጃ የሚለካበት መስፈርት) ይጠቀማሉ፡፡
ባለሥልጣኑ በፀረ-ወባ መድኃኒት በዓይነት ስምንት እንዲሁም ለእናቶችና ሕፃናት የሚውሉ መድኃኒቶችን በዓይነት አምስት በአጠቃላይ 573 መድኃኒቶችን ከገበያ በመሰብሰብ በ2010 ዓ.ም. ባደረገው ምርመራ ከፀረ ወባ መድኃኒቱ ሦስት ዓይነት፣ ከእናቶችና ሕፃናት ደግሞ አንድ መድኃኒት ከደረጃ በታች ሆነው እንዲሰበሰቡ ተደርጓል፡፡ ሁሉም መድኃኒቶችም ከውጭ የገቡ ነበሩ፡፡
በ2009 ዓ.ም. ላይ አገር ውስጥ ከሚመረቱ እንደ አልኮል፣ ሃይድሮጅን ፐር ኦክሳይድና ሌሎች ሪኤጀንቶች በመሳሰሉ ሦስት ምርቶች ላይ በተደረገ ምርመራ 21 ባቾች ከገበያ እንዲሰበሰቡ ተደርጓል፡፡ ለቤተሰብ ምጣኔ የሚውል አንድ መድኃኒትም እንዲሁ፡፡
በ2010 ዓ.ም. በ12 ዓይነት የፀረ ወባ፣ የፀረ ኤችአይቪና የፀረ ቲቢ መድኃኒቶች ላይ የቁጥጥር ሥራ ተደርጎ ሙሉ ለሙሉ ደረጃ ጠብቀው መገኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡
አቶ ገዛኸኝ እንደሚሉት፣ እንደ አገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች የተላመዱ ባክቴሪያዎች እንዲበረክቱ ምከንያትም ሆነዋል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚለው፣ ተመሳስለውም ሆነ ከደረጃ በታች የሚሠሩት መድኃኒቶች ሰፊው ሕዝብ ይጠቀምባቸዋል ተብለው የሚገመቱት መድኃኒቶች ብቻ ሳይሆኑ የካንሰር መድኃኒቶችን ጨምሮ በውድ ዋጋ የሚገዙትንም ያካትታል፡፡ ስለሆነም ለአንድ አገር ሁሉንም መድኃኒቶች የመፈተሽ አቅም ያለው የጤና ሥርዓትና ተቋም ወሳኝ ነው፡፡ የባለሥልጣኑን አቅም አስመልክተን ለአቶ ገዛኸኝ ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ የመድኃኒቶችን ትክክለኛነትና ፈዋሽነት ማረጋገጥ እንደ አገር ትልቅ ኢኮኖሚና ባለሙያ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣኑ ለመንግሥት ጥያቄ እያቀረበ እየሠራ ይገኛል፡፡ የሚያዘው በጀት ይህን ሥራ ለመከወን ክፍተት ቢኖረውም፣ ከተለያዩ መንግሥታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በመሆንም ሥራው ይሠራል፡፡
ሥራው ከፍተኛ የኬሚካል ግብዓት የሚጠይቅ ሲሆን፣ በባለሥልጣኑ ከሚፈተሸው በተጨማሪ መድኃኒቶችን ወደ ውጭ በመላክ እንዲመረመር ይደረጋልም ብለዋል፡፡
በዓለም ከደረጃ በታች ወይም የውሸት መድኃኒት ከሚመረትባቸው አገሮች ህንድ አንዷ ናት፡፡ በዓለም ላይ ካለው የውሸት ወይም ደረጃውን ያልጠበቀ መድኃኒት ከ60 እስከ 65 በመቶ ምንጩ ህንድ ውስጥ እንደሚገኝ፣ በሁለተኛ ደረጃ ቻይና፣ ሦስተኛ ደግሞ ግብፅ ከዚያም ፓኪስታንና ሌሎችም አገሮች እንደሚገኙበት ዶ/ር ንጉሡ ተናግረዋል፡፡
የሐሰተኛ መድኃኒቶች ዝውውር ባደጉም ሆነ በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች የሚከሰት ቢሆንም ይዞታው፣ ስፋቱና የመድኃኒቶቹም ዓይነት ይለያያል፡፡ አፍሪካ ውስጥ በተለይ በምዕራብ አፍሪካ የወባ በሽታ መድኃኒቶች እስከ 65 በመቶ ድረስ የሚሆኑት ተመሳስለው በመሠራታቸው በየዓመቱ ከ100 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሊድኑ ሲችሉ ፈዋሽ ያልሆነ ነገር እየወሰዱ ለህልፈተ ሕይወት ይዳረጋሉ፡፡
በዓለም ደረጃ በወባ በሽታ ብቻ እስከ 450 ሺሕ ሰዎች በየዓመቱ እንደሚሞቱ ሲገመት፣ ይህም ብዙ ትኩረት ያልተሰጠው ችግር ነው፡፡ በታዳጊ አገሮች የወባ መድኃኒት፣ ለባክቴሪያ ኢንፌክሽን የሚያገለግሉ ፀረ ተዋህሲያን እና የወሊድ መከላከያዎች፣ በአሜሪካ ደግሞ የኮሌስትሮል መድኃኒቶች ተመሳሳለው ተገኝተዋል፡፡ የአሜሪካው የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር በ1995 ዓ.ም. በውጭ አገር ተመርተው ወደ አሜሪካ ከገቡት መድኃኒቶች 18 ሚሊዮን ኪኒን የውሸት ሆነው መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር፡፡ ለካንሰር፣ ለአካል መቆጣት፣ ለአለርጂ፣ ለአስም የሚያገለግሉ መድኃኒቶችንም እንዲሁ፡፡
በታዳጊም ሆነ በበለጸጉት አገሮች ለስኳር በሽታ የሚሆኑ ኢንሱሊኖችን ጨምሮ ለከፍተኛ የደም ግፊት የሚሆኑ መድኃኒቶች ሁሉ በብዛት የውሸት እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሽታዎች እየሰፉ ስለመጡ የውሸት መድኃኒቶችም ገበያ በዛው ልክ እየበዛ እንደመጣም ዶ/ር ንጉሡ ይናገራሉ፡፡ ለወንዶች የስንፈተ ወሲብ ማነቃቂያ ተብሎ የሚመረተው ‹‹ቫያግራ›› የተባለው መድኃኒት የውሸት ተመሳስለው ከሚሠሩ መድኃኒቶች ተርታ ነው፡፡ ይህን ጨምሮ ሌሎችም መድኃኒቶች በሠለጠኑት የምዕራብ አገሮች በኢንተርኔት ኦን ላይን እንደሚሸጡ፣ በዚህ መልኩ የሚሸጡ መድኃኒቶች ደግሞ እስከ 50 በመቶ የውሸት እንደሆኑ ዶክተሩ አስረድተዋል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ከቾክ፣ ከስታርች፣ ከበቆሎ ዱቄት ወይም ከድንች መድኃኒት ተብሎ ተሠርቶ መግለጫው ግን የእውነት እንደሚመስል ይህም በሽታን መከላከል ሳይቻል ቀርቶ ለሞት ወይም ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚዳርግ ገልጸዋል፡፡
አንዳንድ የውሸት መድኃኒቶች ላይ ጎጂ ኬሚካሎች እንደሚጨመሩ ይህም ጉበት እንደሚያቃጥል፣ ኩላሊትን እንደሚያውክ፣ አዕምሮን እንደሚያቃውስና የደም ሴሎችን እንደሚያበላሽ ገልጸዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴት ፋርማኮፒያ ኮንቬንሽን ቺፍ ኦፍ ፓርቲ አቶ ኃይሉ ታደግ የውሸትና ከደረጃ በታች መድኃኒቶችን ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን (ኤፌማካ) በሠለጠነ የሰው ኃይል፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂና በማቴሪያል መጠናከር እንዳለበት ይናገራሉ፡፡ የኤፌማካ ብቻውን መጠናከር የትም ሊያደርስ ስለማይችልም የጎረቤት አገሮችም ተቆጣጣሪ አካል በዚህ መልኩ መጠናከር እንሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል አገሮች በቁጥጥሩ ላይ ትኩረት ያደረገ ጥምረት መፍጠራቸውን፣ በአንድ ላይ ሆነው ምን ዓይነት ሥራ በጋራ ልንሠራ እንችላለን? መረጃ እንዴት ልንለዋወጥ እንችላለን? በሚለው ላይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ እየተወያዩበት መሆኑንና ይህም እየጎለበተና እየተጠናከረ ሲሄድ ራሱን የቻለ አንድ ዋስትና ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ሰፊ ድንበር እንደምትጋራ፣ በዚህም ለአደጋ የተጋለጡ ተብለው የተለዩት ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን እንዳሉና በእነዚህም አገሮች የሚካሄደው ቁጥጥር በጥንቃቄና በተጠናከረ መልኩ እንዲከናወን ኢትዮጵያ የራሷን ሚና መጫወት እንዳለባትም አክለዋል፡፡
በምሕረት ሞገስና በታደሰ ገብረማርያም

0 Comments
0 Shares