በሞጆ ደረቅ ወደብ የተከማቹ ኮንቴይነሮችን መውረስ ተጀመረ

በሞጆ ደረቅ ወደብ ታክስ እና ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የተከማቹ 8 ሺህ 100 ኮንቴይነሮችን በቀነ ገደባቸው መሰረት መውረስ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሞጆ ደረቅ ወደብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አየለ እንደተናገሩት ቀነ ገደባቸው ከማለፉ በፊት ንብረታቸውን እንዲያነሱ ለባለሃብቶች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ሆኖም ግን ንብረታቸውን እንዲያነሱ ለባለሃብቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው በአፋጣኝ እያነሱ አይደለም ብለዋል።
በዚህም ከሁለት ወራት በላይ የተከማቹትን ኮንቴይነሮች የመውረሱ ሂደት መጀመሩን የሞጆ ደረቅ ወደብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ ተናግረዋል።

የተከማቹትን ኮንቴይነሮች የመውረሱ ስራም ቀጣይነት እንዳለው ነው ዋና ስራ አስኪያጁ ያስታወቁት።
የተወረሱ ንብረቶቹን በጨረታ በመሸጥ ታክስ እና ቀረጡ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

እንደ አቶ አዲስ ገለፃ፥ በመንግስት ተቋማት የሚከማቹ ኮንቴይነሮች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ወቅት 84 ኮንቴይነሮች ያለአግባብ መከማቸታቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን የመንግስት ኮንቴይነሮች በዚህ ሳምንት ለማስነሳት ጥረት እንደሚደርግም ነው ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት።
ታህሳስ 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
በሞጆ ደረቅ ወደብ የተከማቹ ኮንቴይነሮችን መውረስ ተጀመረ በሞጆ ደረቅ ወደብ ታክስ እና ቀረጥ ሳይከፈልባቸው የተከማቹ 8 ሺህ 100 ኮንቴይነሮችን በቀነ ገደባቸው መሰረት መውረስ ተጀመረ። በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሞጆ ደረቅ ወደብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አየለ እንደተናገሩት ቀነ ገደባቸው ከማለፉ በፊት ንብረታቸውን እንዲያነሱ ለባለሃብቶች በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል። ሆኖም ግን ንብረታቸውን እንዲያነሱ ለባለሃብቶች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው በአፋጣኝ እያነሱ አይደለም ብለዋል። በዚህም ከሁለት ወራት በላይ የተከማቹትን ኮንቴይነሮች የመውረሱ ሂደት መጀመሩን የሞጆ ደረቅ ወደብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ ተናግረዋል። የተከማቹትን ኮንቴይነሮች የመውረሱ ስራም ቀጣይነት እንዳለው ነው ዋና ስራ አስኪያጁ ያስታወቁት። የተወረሱ ንብረቶቹን በጨረታ በመሸጥ ታክስ እና ቀረጡ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል። እንደ አቶ አዲስ ገለፃ፥ በመንግስት ተቋማት የሚከማቹ ኮንቴይነሮች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም በአሁኑ ወቅት 84 ኮንቴይነሮች ያለአግባብ መከማቸታቸውን ገልፀዋል። እነዚህን የመንግስት ኮንቴይነሮች በዚህ ሳምንት ለማስነሳት ጥረት እንደሚደርግም ነው ዋና ስራ አስኪያጁ የተናገሩት። ታህሳስ 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)
0 Comments 0 Shares