ከ57 ዓመታት በኋላ የንግድ ሕግ ረቂቅ ማሻሻያ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic
በተደጋጋሚ ውድቅ የተደረገው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ረቂቅ ሕግ በድጋሚ ቀርቧል
ከ1952 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘውን የንግድ ሕግ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን፣ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም ከ1954 ዓ.ም. ጀምሮ በተግባር ላይ የቆየውንና ተሞክሮ በተደጋጋሚ ውድቅ ተደርጎ የነበረው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉንም ለማሻሻል፣ ድጋሚ ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ መቅረቡንም ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ረቡዕ ኅዳር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት የመሥሪያ ቤታቸውን የሩብ ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡