WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ ሠራተኞችን እመነጥራለሁ አለ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጭበርብረው የተቀጠሩ ሠራተኞችን ለመመንጠር አዲስ ዕቅድ አወጣ፡፡ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሁሉም መሥሪያ ቤቶች ይህንን የሚሠራ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን፣ በማዕከል ደረጃ ፖሊስና ፍትሕ ቢሮ ያሉበት ግብረ ኃይል አቋቁሟል፡፡ ቢሮው ሒደቱ የሚመራበትን መመርያ በማዘጋጀት በማዕከል፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ መዋቅሮች ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ቆይቷል፡፡
0 Comments 0 Shares