WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
ፓርላማው በ13 ድምፀ ተአቅቦ የደን ልማት ጥበቃ አዋጅን አፀደቀ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢሕገ መንግሥታዊ ነው የሚል ክርክር የቀረበበትን የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ በ13 ድምፀ ተአቅቦ አፀደቀ፡፡ ኢሕአዴግ በሚመራበት ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ መሠረት የፓርላማ አባላት ከፓርቲው የበላይ አካል የተሰጡ ውሳኔዎችን መቃወም እንደ ዲስፕሊን ጥሰት የሚቆጠር በመሆኑ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቃውሞ ክርክር ያቀረቡ አባላትና ሌሎችም በተቃውሞ ድምፅ ከመስጠት ይልቅ ድምፅ ተአቅቦ ማድረግን መርጠዋል፡፡ አንድ ረቂቅ አዋጅ በ13 የኢሕአዴግ አባላት ድምፅ ተአቅቦ ሲፀድቅም የመጀመርያው ሊሆን እንደሚችል ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
0 Comments 0 Shares